Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ከሌሎች ጋር ስለመገናኘት

Last Reviewed: June 08, 2020

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

የቴሌኮሚኒኬሽን ኔትወርኮች እና ኢንተርኔት ከሌሎች ሰዎች ጋር የምናደርገውን ግንኙነት ከምንጊዜውም በተሻለ ቀላል እንዲኾን ቢያደርጉም ክትትል ይበልጥ እንዲበረታ አድርገዋል። ግላዊነትዎን ለመጠበቅ ተጨማሪ እርምጃዎችን ካልወሰዱ እያንዳንዱ የስልክ ጥሪ፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክቾች፣ ኢሜል ምልልሶች፣ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎቶች፣ የድምጽ እና ቪዲዮ ጥሪዎች እና የማኀበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች በሙሉ ለሌሎች አድማጮች ተጋላጭ ናቸው።

በአብዛኛውን እና እጅግ በጣም የተሻለው ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት የማድረጊያው መንገድ የመገናኛ አውታሮችን፣ ኮምፒውተሮችን ወይም ሰልኮችን ሳይጠቀሙ በአካል መገናኘት ነው። ነገር ግን ሁልጊዜም መገናኘት ስለማይቻል ቀጣዩ የተሻለ አማራጭ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን መጠቀም ነው፡፡

ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ እንዴት ይሰራል? anchor link

ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ መረጃው በዋናው መልእክት ላኪ (የመጀመሪያው "ጥግ") ሚስጥራዊ መልዕክት እንዲሆን መደረጉን እና የመጨረሻው ተቀባይ (ሁለተኛ "ጥግ") ብቻ ምስጢራዊው መልዕክት መፈታቱን ያረጋግጣል፡፡ ይህ ማለት ማንም ሰው በመሀል ገብቶ መስማት አይችልም፤ መልዕክትዎን አይፈታምም፡፡ ይህ የኢንተርኔት ካፌዎችን፣ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢው፣የሚጠቀሙት መካነ ድር እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያዎንም ይጨምራል፡፡ በተወሰነ መልኩ በተቃራኒው በስልክዎ ላይ ባለመተግበሪያ የተመለከቱት መልዕክት ወይም በኮምፕዩተርዎ የጎበኙት መካነ ድር ራሳቸው የመተግበሪያው ወይም የመካነ ድሩ ባለቤት ያዩታል ማለት አይደለም፡፡ የጥሩ ምስጠራ ሁነኛ መለያው ምስጠራውን የነደፉት እና የተገበሩት ሰዎች ራሳቸውን እንኳን ሰብረው መግባት የማይችሉት ነው፡፡

በኤስኤስዲ መካነ ድር ላይ መመሪያ የተዘጋጀላቸው መሣሪያዎች በሙሉ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ይጠቀማሉ፡፡ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ለማንኛውም አይነት ግንኙነትዎ የድምጽ እና ቪዲዮ ጥሪዎች፣ የጽሑፍ ውይይት እና ኢሜልን ጨምሮ መጠቀም ይችላሉ፡፡

(ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ከንብርብር ማጓጓዣ ምስጠራ ጋር መምታታት የለብዎትም፡፡ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ መልዕክትዎን ከእርስዎ እስከ ተቀባዩ ድረስ ሲጠብቅ ንብርብር ማጓጓዣ ምስጠራ ደግሞ መልዕክትዎ ከእርስዎ መሣሪያ ወደ መተግበሪያው ሰርቨር ወይም መካነ ድር እና ከመተግበሪያው ሰርቨር ወደ መልዕክት ተቀባዩ መሣሪያ ሲጓጓዝ ብቻ ነው ጥበቃ የሚያደርገው፡፡ በመሀል የእርስዎ መልዕክት መለዋወጫ አገልግሎት አቅራቢ ወይም የጎበኙት መካነ ድር ወይም የተጠቀሙት መተግበሪያ ያልተመሰጠረ የመልዕክትዎን ቅጂ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

ከበስተጀርባ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የሚሰራው እንዲህ ነው፡፡ ሁለት ግለሰቦች ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ተጠቅመው መገናኘት ሲፈልጉ(ለምሳሌ አበበ እና ጫልቱ) እያንዳንዳቸው ቁልፎች የሚባሉትን ውሂቦች ማመንጨት አለባቸው። እነዚህ ቁልፎች ማንም ማንበብ የሚችለውን ውሂብ አዛማጅ ቁልፉን ከያዘው ሰው በቀር ማንም ማንበብ ወደማይችለው ውሂብ ይቀይራሉ፡፡ አበበ ለጫልቱ መልዕክትን ከመላኩ በፊት ጫልቱ ብቻ መልዕክቱን መፍታት እንድትችል በእርሷ ቁልፍ መልዕክቱን ያመሰጥረዋል። የተመሰጠረውን መልዕክትም በኢንተርኔት ይልከዋል። ማንኛውም ግለሰብ የአበበ እና የጫልቱን ግንኙነት ቢሰልል እና አበበ መልዕክቱን ለመላክ የተጠቀመውን አገልግሎት (ለምሳሌ የአበበን የኢሜል መለያ) መጠቀም ቢችል እንኳን ሰላዩ የሚያየው የተደበቀውን መልዕክት እንጂ የመልዕክቱን ይዘት አይደለም። ጫልቱ መልዕክቱን በምትቀበልበት ወቅት የራሷን ቁልፍ በመጠቀም ይዘቱን ወደ ሚነበብ መልዕክት መፍታት አለባት።

እንደ ጎግል ሐንጋውት ያሉ አንዳንድ አገልግሎቶች «ምስጠራን» ያስተዋውቃሉ፤ ነገር ግን የሚጠቀሙት በጎግል የተፈጠሩ እና ቁጥጥር ስር ያሉ ቁልፎችን ነው፡፡ ይህ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ አይደለም፡፡ ውይይቱ የምር ደኀንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን "ጥግ"ዎች ብቻ ማመስጠር እና መፍታት የሚችሉበት ቁልፎች ሲኖራቸው ነው፡፡ የሚጠቀሙት አገልግሎት ቁልፎችን የሚቆጣጠር ከሆነ ያ አገልግሎት የማጓጓዣ ንብርብር-ምስጠራ ነው፡፡

ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ማለት ተጠቃሚዎች ቁልፎቻቸውን በሚስጢር የሚይዙበት ነው። በሌላ አገላለጽ ለመመስጠር እና ለመፍታት የሚያገለግሉት ቁልፎችን ትክክለኛ ሰዎችንብረታቸውን ሲያደርጓቸው ማለት ነው። ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን መጠቀም ቁልፎችን በትጋት የሚያረጋግጡ መተግበሪያዎችን መርጦ ከማውረድ ጀምሮ ሰፊ ጥረት ይጠይቃል።ነገር ግን ለተጠቃሚዎች ደኅንነታችን እጅግ በጣም የተሻለው ሁለቱም የሚጠቀሙበትን አገልግሎት ሰጪ አለማመን ነው።

ስለ ምስጠራ ምን አውቃለው?የምስጠራ መሠረታዊ ጽንሰ ሐሳቦች እና የተለያዩ የምስጠራ አይነቶች በሚሉት ክፍሎች ስለምስጠራ የበለጠ ይማሩ፡፡

የስልክ ጥሪዎች እና የጽሑፍ መልዕክቶች ከተመሰጠሩ የኢንተርኔት መልዕክቶች ጋር anchor link

በመደበኛም ሆነ ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲደውሉ ንግግርዎ ከጥግ እስከ ጥግ አልተመሰጠረም፤ አጭር ጽሑፍ መልዕክት( SMS) ሲልኩ ደግሞ መልዕክቱ ጭራሽ አልተመሰጠረም፡፡ ሁለቱም መንግሥታት ወይም ስልኩ ላይ ስልጣን ያለው ማንኛውም ሰው መልዕክቶችዎን እንዲያነብ ወይም ጥሪዎችዎን እንዲመዘግብ ይፈቅዳሉ፡፡ እርስዎ የተጋላጭነት አዝማሚያ ትንተና መንግስትን የሚያጠቃልል ከሆነ በበይነመረብ የሚንቀሳቀሱ ምስጠራዎችን አማራጮችን ይመርጡ ይሆናል፡፡ እንደ ጉርሻ፣ በአብዛኛው ከእነዚህ የምስጠራ አማራጮች ቪዲዮም ያቀርባሉ፡፡

አንዳንድ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ የጽሑፍ፣ የድምጽ እና ምስል ጥሪዎችን የሚያቀርቡ አገልግሎቶች ወይም ሶፍትዌሮች ምሳሌዎች እነዚህን ይጨምራሉ፡-

አንዳንድ በነባሪነት ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አገልግሎት የማይሰጡ አገልግሎቶች ምሳሌዎች እነዚህን ይጨምራሉ፡-

  • ጉግል ሐንጋውት
  • ካካዎ ቶክ
  • ላየን
  • ስናፕቻትt
  • ዊቻት
  • ኪውኪው
  • ያሁ ሜሴንጀር

እንደ ፌስቡክ ሜሴንጀር እና ቴሌግራም ያሉ አገልግሎቶች ሆን ብለው ካበሯቸው ብቻ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አግልግሎት ይሰጣሉ፡፡ እንደ አይሜሴጅ ያሉ ደግሞ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አገልግሎት የሚሰጡት ሁሉቱም ተጠቃሚዎች ተመሳሳይ መሣሪያዎች ሲጠቀሙ ነው፡፡(አይሜሴጅ የሚሰራው ለአይፎን ተጠቃሚዎች ብቻ ነው፡፡)

የመላላኪያ አገልግሎቶችን እስከምን ድረስ ያምኗቸዋል? anchor link

ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ከመንግሥታት፣ ጠላፊዎች እና የመልዕክት አገልግሎቱን ከሚሰጠው ድርጅት ከራሱ እርስዎን ሊከላከል ይችላል። ነገር ግን እነዚያ ቡድኖች በሙሉ የምንጠቀምባቸው ሶፍትዌሮች ምሥጢራዊ ለውጦችን ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል። ። ስለዚህ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን እንደሚጠቀሙ ቢናገሩም እንኳን ባልተመሰጠረ ወይም በተዳከመ ምስጠራ ሊልኩ ይችላሉ።

ኢኤፍኤፍን ጨምሮ ብዙ ቡድኖች የታወቁ አገልግሎት ሰጪዎች (ንብረትነቱ የፌስቡክ እንደሆነው ዋትስአፕ ወይም ሲግናል ያሉ) ቃል የገቡትን ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የምር እየሰጡ መሆናቸውን ጊዜ ወስደው ይፈትሻሉ። ነገር ግን ለእነዚህ አደጋዎች አሳሳቢ ከሆኑ, በይፋ የሚታወቁ እና ምስጢራዊ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ መሳሪያዎችን መጠቀም እና ከሚጠቀሙባቸው የትራንስፖርት ስርዓቶች ነጻ እንዲሆኑ የሚረዱ መሳሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ። ኦቲአር እና ፒጂፒ ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህ ስርዓቶች ለመተግበር በተጠቃሚ ችሎታ ላይ የሚመረኮዙ ሲሆኑ በአብዛኛው ጊዜ ለተጠቃሚዎች ምቹ አይደሉም። እና ሁሉንም ዘመናዊ የላቁ የምስጠራ ቴክኖሎጂዎችን የማይጠቀሙ የቆዩ ፕሮቶኮሎች ናቸው።

ኦፍ ዘሪከርድ(ኦቲአር) ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን የሚጠቀም ፕሮቶኮል ሲሆን የወዲያው መላላኪያ አገልግሎቶች ላይ ተደርቦ መስራት የሚችል ነው። ኦቲአርን ያካተቱ መሣሪያዎች እነዚህን ይጨምራሉ።

ፒጂፒ (ወይም ፐሪቲ ጉድ ፕራይቬሲ) ለኤሜይል ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የሚሰጥ መደበኛ አገልግሎት ነው። ፒጂፒ ምስጠራን እንዴት መጫን እና መጠቀም እንደሚችሉ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፡-

ፒጂፒ ኢሜይል እጅግ ተመራጭ የሚሆነው ቴክኒካዊ ልምድ ላላቸው እና ቴክኒካዊ ልምድ ካላቸው ሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር መልዕክት ለሚለዋወጡ እና የፒጂፒን ውስብስብነት እና ውስንነቶችን ለሚያውቁ ነው።

ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ማድረግ የማይችለው anchor link

ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የመስመር ላይ ግንኙነት ይዘትን ብቻ መደበቅ ይችላል። ነገር ግን ግንኙነት ማድረግዎን መደበቅ አይችልም። ይህ ማለት ዲበ ውሂብ አይጠብቅም ማለት ነው። ይህም የኢሜይል ርዕሰ ጉዳይ፣ ከማን ጋር ግንኙነት እያደረጉ እንዳሉ እና ግንኙነቱን መቼ እንደደረጉ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ያሉበት ስፍራ ራሱ ዲበ ውሂብ ነው።

የግንኙነትዎ ይዘት ሚስጥር በኾነበት ወቅት እንኳን ዲበ ውሂብ ወይም ስለ እርስዎ እጅግ በጣም ገላጭ መረጃን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል።

የስልክ ጥሪዎ ዲበ ውሂብ አንዳንድ በጣም ሚስጥራዊ እና ስሱ የኾኑ መረጃዎችን አሳልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። ለምሳሌ፦

  • ከሌሊቱ 8:24 ላይ በስልክ የወሲብ አገልግሎት ወደሚሰጡ እንደደወሉ እና ለ18 ደቂቃ እንዳወሩ ያውቃሉ ነገር ግን ስለ ምን እንዳወሩ አያውቁም።
  • ከራስ መኮንን ድልድይ ለእሳት አደጋ መከላከል መደወልዎን ያውቃሉ ነገር ግን የደወሉበት የመነጋገሪያ ርዕስ ሚስጥር እንደኾነ ይቆያል።
  • ከኤችአይቪ ምርመራ አገልግሎት ጋር፣ በመቀጠልም ከዶክተርዎ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት እንደተነጋገሩ ያውቃሉ ነገር ግን ምን እንደተወያዩ አያውቁም።
  • ከአገር ውስጥ የወረዳ ጽሕፈት ቤት ጠመንጃ ህግን በተመለከተ ዘመቻ እያደረጉ እያለ ጥሪ እንደደረሱ ያውቃሉ:: እና ከዚያ በኋላ ሴናተሮች እና ኮንግሬሽን ተወካዮቻቸውን ወዲያውኑ ይደውላሉ። ነገር ግን የእነዚህ ጥሪዎች ይዘት ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ይጠብቃል::
  • የማህጸን ስፔሻሊስት ጋር ደውለው ለግማሽ ሰዓት እንዳወሩ እና በመቀጠልም በአካባቢዎ የሚገኝ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ጋር እንደደወሉ ያውቃሉ ነገር ግን ምን እንዳወሩ ማንም አያውቅም።

ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች anchor link

ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ለእርስዎ ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ለማድረግ አስፈላጊ ከሆኑ ብዙ አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ ነው። ከላይ እንደተገለፀው ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ኩባንያዎች እና መንግስታት መልዕክቶችዎ ጋር እንዳይደርሱ ለመከላከል ጥሩ ነው። ነገር ግን ለብዙ ሰዎች, ኩባንያዎች እና መንግስታት ትልቁ ስጋት የሚባሉት አይደሉም። ስለዚህም ጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ምናልባት ከፍተኛው ቀዳሚ ጉዳያቸው ላይሆን ይችላል።

ለምሳሌ አንድ ሰው ስለ ትዳር አጋሩ፣ ወላጆቹ ወይም አሠሪው መሣሪያቸውን የማግኘት ዕድል ከተጨነቀ ፣ በአጭር ጊዜ “የሚጠፉ” መልዕክቶችን የመላክ አቅም መላኪያውን አገልግሎት ለመምረጥ የመወሰኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ሌላ ሰው የስልክ ቁጥሩን ስለመስጠት ሊጨነቅ ይችላል፤ እናም የስልክ ቁጥር የሌለው "ቅጽል" መጠቀም መቻል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

በአጠቃላይ ሲታይ የደኅንነት እና የግላዊነት ገጽታዎች ደኅንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ ዘዴን ለመምረጥ ብቸኛ ምክንያቶች አይደሉም። ጓደኞችዎ እና እውቅያዎችዎ የማይጠቀሙት ከሆነ ከፍተኛ የደኅንነት ባህሪያት ያለው መተግበሪያ ዋጋ የለውም። በጣም ታዋቂ እና በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ መተግበሪያዎች በአገር እና በማህበረሰብ እጅግ የተለያየ ተደራሽነት ሊኖራቸው ይችላል። ደካማ የአገልግሎቱ ጥራት ወይም መተግበሪያውን ለመጠቀም ክፍያ ለተወሰኑ ሰዎች የማይመች ሊያደርግው ይችላል።

ከደኅንነቱ በተጠበቀ የመግባቢያ ዘዴ ውስጥ ምን ማግኘት እንደሚፈልጉ እና እንደሚያስፈልግዎ ይበልጥ በግልጽ በተረዱ ቁጥር ሰፊ፣ እርስ በርስ የሚጋጩ፣ አንዳንዴም ጊዜ ያለፈባቸው መረጃዎችን ለመለየት ይበልጥ ቀላል ይሆናል።