Surveillance
Self-Defense

መሰረታዊያን

ስለ ደጂታል ውሂብዎ ወይም ከሌሌሎች ጋር ስላደረጉት ንግግር ግለኝነት መጠበቅ ተጨንቀው የሚያውቁ ከሆኑ እኛ እዚህ ያለነው እርስዎን ለመርዳት ነው፡፡

ሰርቪሊያንስ ሰልፍ ዲፌንስ የዲጂታል ደኅንነት መመሪያ ሲሆን በግልዎ ለመስመር ላይ ስለላ ምን ያህል እንደተጋለጡ እንዴት መገምገም እንደሚችሉ እርስዎን ያስተምራል፡፡ ከኪስ ሌቦች እስከ ብሔራዊ ደኅንነት ያሉ የእርስዎን ሚስጥሮች ለማግኘት ክትትል ከሚያደርጉ ራስዎን እንዲጠብቁ ይረዳዎታል፡፡ ግለኝነትን ስለሚያሳድጉ ምርጥ መሣሪያዎች መመሪያዎችን ለእርስዎ እናቀርባለን፡፡ ራስዎን ከክትትል  መጠበቅን ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ጋር እንዴት ማካተት  እንደሚችሉ እናብራራለን፡፡

 የመጀመሪያ እርምጃዎችን ለመጀመር ዝግጁ ከሆኑ ተከታታይ መሰረታዊ መመሪያዎች (ከዚህ በታች) ዲጂታል ክትትል ምን ማለት እንደሆነና እንዴት እርሱን መዋጋት እንደሚቻል እንዲገነዘቡ ይረዳዎታል፡፡ የሚያጋጥምዎ አደጋዎችን መገምገም መመሪያ እንዲጀምሩ እንጠቁማለን

JavaScript license information