Surveillance
Self-Defense

ለዊንዶውስ የPGP አጠቃቀም

በአሁን ሰዓት በስርዓቱ ላይ ባጋጠሙ ተጋላጭነቶች ምክንያት ኢኤፍኤፍ PGPን እንዲጠቀሙ አይመክርም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ጦማራችንን ማንበብ ይችላሉ፡፡ ሌሎች አማራጭ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠሩ አገልግሎቶችን ማግኘትም ይችላሉ፡፡ የትኛው ለእርስዎ እጅግ ምርጡ እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆኑ ሲግናል ለአንድሮይድ እና ሲግናል ለአይኦኤስን በመጠቀም እንዲጀምሩ እንጠቁማለን፡፡

በአሁን ሰዓት በስርዓቱ ላይ ባጋጠሙ ተጋላጭነቶች ምክንያት ኢኤፍኤፍ PGPን እንዲጠቀሙ አይመክርም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ጦማራችንን ማንበብ ይችላሉ፡፡ ሌሎች አማራጭ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠሩ አገልግሎቶችን ማግኘትም ይችላሉ፡፡ የትኛው ለእርስዎ እጅግ ምርጡ እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆኑ ሲግናል ለአንድሮይድ እና ሲግናል ለአይኦኤስን በመጠቀም እንዲጀምሩ እንጠቁማለን፡፡

Last reviewed: 
2018-05-12
ይህ ገጽ ከእንግሊዘኛው ቅጂ የተተረጎመ ነው፡፡ የእንግሊዘኛው ቅጂ ምን አልባት የበለጠ የዘመነ ይሆናል፡፡

እጅግ መልካም የኾነ ግላዊነት ወይም ፕሪቲ ጉድ ፕራይቬሲ (PGP) የተባለው የኢሜል ግንኙነትዎ ከታቀደለት ተቀባይ ሰው በስተቀር በማንም እንዳይነበብ የሚከላከል ስርዓት ነው። በተጨማሪም በትንሹ ኮምፒውተርዎ ቢሰረቅ ወይም ቢሰበር በኮምፒተርዎ ላይ የተጠራቀሙት ኢሜሎችዎ እንዳይነበቡ ከአደጋ ይጠብቃል።

ከአንድ ግለሰብ የተላከልዎት ኢሜል በትክክል ከተጠቀሰው ሰው የመጣ እንደኾነ እና ከሦስተኛ ወገን የተላከ የሀሰት መልዕክት አለመኾኑን ለማረጋገጥ ሊያገለግል ይችላል (ይህ ካልኾነ እውነተኛ የሚመስል ኢሜል በቀላሉ ሊፈጠር ይችላል)። ለስለላ እና ለማሳሳት ጥቃት ዒላማ የሚኾኑ ከኾነ እነዚህ ሁለቱም በጣም አስፈላጊ መከላከያ ናቸው።

PGPን ለመጠቀም አሁን ካለዎት የኢሜል ፕሮግራም ጋር አብረው የሚሠሩ ተጨማሪ ሶፍትዌሮችን መጫን ይጠበቅብዎታል። በተጨማሪም በግልዎ የሚይዙት የግል ቁልፍ መፍጠር አለብዎት። ይህ የግል ቁልፍ የተላከልዎትን ምስጢራዊ ኢሜል ለመፍታት እና የሚልኳቸውን ኢሜልዎች በእውነት እርሶ እንደላኳቸው ለማሳየት የዲጂታል ፊርማ ለመፈረም የሚጠቀሙበት ነው። በመጨረሻም የአደባባይ ቁልፍዎን እንዴት እንደሚያከፋፍሉ ይማራሉ። የአደባባይ ቁልፍ ሌሎች ሰዎች ለእርስዎ ምስጢራዊ ኢሜል ከመላካቸው በፊት ሊያውቁት የሚገባ እና እርስዎ የሚልኩትን ኢሜል የሚያረጋግጡበት ቅንጣቢ መረጃ ነው።

 

አጠቃላይ ምልከታ Anchor link

PGPን በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ ኢሜሎችን ለመላላክ GPG4Win (የGNU የግላዊነት ጥበቃ ለዊንዶውስ GnuPG ይባላል)፣ ሞዚላ ተንደርበርድ እና ኤኒግሜል የተባሉትን ሦስት ፕሮግራሞችን በአንድ ላይ መጠቀም ያስፈልጋል። GnuPG የኢሜልዎን ይዘት የሚያመስጥረው እና የሚፈታው ፕሮግራም ነው። ሞዚላ ተንደርበርድ የድር ማሰሻን ሳይጠቀሙ ኢሜልን ማንበንብ እና መጻፍ የሚያስችል የኢሜል አገልግሎት ደምበኛ ሲኾን ኤኒግሜል ደግሞ ሁሉንም በአንድነት የሚያስር የሞዚላ ተንደርበርድ ቅጥያ ነው።

ማስታወሻ! ይህ መመሪያ የሚያስተምረው ከአውትሉክ ጋር ተመሳሳይ ተግባር ያለው የኢሜል ደምበኛ ፕሮግራም የኾነው ሞዚላ ተንደርበርድን ከPGP ጋር እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ነው። የሚመርጡት የኢሜል ሶፍትዌር ፕሮግራም (ወይም ልክ እንደ ጎግል ሜል ወይም አውትሉክ ያለ የዌብ ሜል አግልግሎት) ሊኖርዎት ይችላል። ይህ መመሪያ እነዚህን ፕሮግራሞች በመጠቀም PGPን እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚያውሉ አያሳይም። ስለዚህ ተንደርበርድን በመጫን PGPን በአዲስ የኢሜል ደምበኛ መጠቀም መሞከርን መምረጥ ወይም እርስዎ በሚፈልጉት ሶፍትዌር PGPን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ሌሎች መንገዶችን መፈለግ ይችላሉ። እስከአሁን በእነዚህ ፕሮግራሞች ላይ የሚሠራ አመርቂ ውጤት አላገኘንም።

PGPን መጠቀም ሙሉ በሙሉ ኢሜልዎን አያመስጥርም። የላኪውን እና የተቀባዩን መረጃ እንዲሁም የኢሜሉን ርዕሰ ጉዳይ ጨምሮ አያመሰጥርም!

አሁን ባለው የኢሜል ስርዓት የላኪ እና የተቀባይ መረጃን ማመስጠር አይቻልም። ሞዚላ ተንደርበርድን ከኤኒግሜል ቅጥያ ጋር መጠቀም ሊያጎናጽፍዎት የሚችለው የኢሜልዎን ይዘት የማመስጠር ቀላሉን መንገድ ነው። በእርስዎ ኢሜል ላይ ስለላን የሚያካሂድ ማንኛውም ሰው ግንኙነት የሚፈጽሟቸውን ሰዎች ማንነት እና ኢሜል መቼ እንደሚልኩላቸው ማወቅ ይችላል።

በመጀመሪያ የሚያስፈልጉትን ሁሉንም ሶፍትዌሮች ያውርዱ፣ በኮምፒውተርዎ ላይ ይጫኑ። በመቀጠል በማዋቀር እና በአጠቃቀም ይጨርሱ።

 

GPG4Winን ማግኘት Anchor link

የዊንዶውስ ስሪት የኾነውን የGnuPG (GPG በመባል የሚታወቀውን) መጫኛን ከGPG4Win የማውረጃ ገጽ ላይ በማውረድ ማግኘት ይችላሉ።

የGPG መጫኛውን ለማውረድ GPG4Win ከGnuPG ጋር የመጨረሻ ስሪት የሆነው ምንዝር ላይ ብቻ (ቫኒላ ወይም ላይት) ጠቅ ያድርጉ።

ይህ የGPG ስሪት ደህንነቱ የተጠበቀ የ“HTTPS” ማውረጃ ላይ ሳይኾን የ“HTTP” ማውረጃ አገልግሎት የሚሰጡ ድረ ገጾች ላይ ብቻ የሚገኝ ነው። የኢንተርኔት ግንኙነትዎን ሊነካኩ በሚችሉ የተለያዩ አካላት ስለላ ያደርስብኛል ብለው የሚጠረጥሩ ከኾነ ጠበቅ ያሉ መፍትሄዎችን መፈለግ ሊኖርብዎት ይችላል። ለምሳሌ ዊንዶውስን የሚተካ ደህንነቱ የተጠበቀ ቴልስን የሚባለውን ስርዓተ ክወና ማውረድ እና መጫን።

አብዛኞቹ የድር ማሰሻዎች ይህንን ሰነድ ማውረድ እንደሚፈልጉ ማረጋገጫ ይጠይቅዎታል። የኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 11ኛው ስሪት በድር መዳሰሻው ገጽ የታችኛው ክፍል ላይ ብርቱካናማ ክፈፍ ያለው አሞሌ ያሳያል።

ለማንኛውም የድረ ማሰሻ እጅግ በጣም ተመራጭ የሚኾነው ወደሚቀጥለው እንቅስቃሴ ከመግባትዎ በፊት ያወረዱትን ሰነድ ማስቀመጥ ነው። ስለዚህ “ሴቭ” የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ። በነባሪ አብዛኞቹ የድር ማሰሻዎች የወረደውን ሰነድ በማውረጃ ማህደር ውስጥ ያስቀምጣሉ።

 

ሞዚላ ተንደርበርድን ማውረድ Anchor link

ወደ ሞዚላ ተንደርበርድ ድረ ገጽ ይሂዱ።

“ተንደርበርድ ፍሪ ዳውንሎድ” በሚለው አረንጓዴ አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ።

የሞዚላ ተንደርበርድ ድረ ገጽ ተመራጭ ቋንቋዎን ያውቀዋል። ተንደርበርድን በሌላ ቋንቋ መጠቀም የሚፈልጉ ከኾነ “አዘር ሲስተምስ &አምፕ; ላንጉጅስ” የሚለው አገናኝ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና እርሱ ላይ ያኑሩ።

አብዛኞቹ የድር ማሰሻዎች ይህንን ሰነድ ማውረድ እንደሚፈልጉ ማረጋገጫ ይጠይቅዎታል። የኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 11ኛው ስሪት በድር መዳሰሻው ገጽ የታችኛው ክፍል ላይ ብርቱካናማ ክፈፍ ያለው አሞሌ ያሳያል።

ለማንኛውም የድር ማሰሻ እጅግ በጣም ተመራጭ የሚኾነው ወደሚቀጥለው እንቅስቃሴ ከመግባትዎ በፊት ያወረዱትን ሰነድ ማስቀመጥ ነው። ስለዚህ “ሴቭ” የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ። በነባሪ አብዛኞቹ የድር ማሰሻዎች የወረደውን ሰነድ በማውረጃ ማህደር ውስጥ ያስቀምጣሉ።

 

ኤኒግሜልን ማውረድ Anchor link

ኤኒግሜልን ከኤኒግሜል ድረ ገጽ ማግኘት ይችላሉ።

አብዛኞቹ የድር ማሰሻዎች ይህንን ሰነድ ማውረድ እንደሚፈልጉ ማረጋገጫ ይጠይቅዎታል። የኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 11ኛው ስሪት በድር መዳሰሻው ገጽ የታችኛው ክፍል ላይ ብርቱካናማ ክፈፍ ያለው አሞሌ ያሳያል።

ለማንኛውም የድር ማሰሻ እጅግ በጣም ተመራጭ የሚኾነው ወደሚቀጥለው እንቅስቃሴ ከመግባትዎ በፊት ያወረዱትን ሰነድ ማስቀመጥ ነው። ስለዚህ “ሴቭ” የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ። በነባሪ አብዛኞቹ የድር ማሰሻዎች የወረደውን ሰነድ በማውረጃ ማህደር ውስጥ ያስቀምጣሉ።

ኤኒግሜልን፣ GPG4Win እና ሞዚላ ተንደርበርድን ካወረዱ በኋላ በማውረጃ ማህደርዎ ውስጥ ሦስት አዳዲስ ሰነዶች ሊኖርዎት ይገባል፦

 

GPG4Winን መጫን Anchor link

የዊንዶውስ ኤክስፕሎረር መስኮት ክፍት ያድርጉ እና gpg4win-xxx-x.x.x.exe የሚለው ፋይል ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ። በመቀጠልም ይህ ፕሮግራም እንዲጫን እንደሚፈቅዱ ይጠየቃሉ። ከዚያም “የስ” የሚለውን አዝራራ ጠቅ ያድርጉ።

ምን ምን እንደሚጫን አጠር ያለ አጠቃላይ ክለሳ የሚሰጥ መስኮት ይከፈታል። በመቀጠል “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የፍቃድ ስምምነትን የያዘ መስኮት ይከፈታል። “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

GPG4Win ቫኒላ ጥቅል ምንም የሚመረጥ ምንዝር ስለሌለው በድጋሚ “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። ለGPG4Win-ላይት ጥቅል GnuPGን ብቻ ለመጫን ሁሉንም አማራጭ ምንዝሮች አይምረጡ።

በመቀጠል GPG የት እንደሚጫን መምረጥ ይችላሉ። የነባሪ ቅንብሩን እንዳይቀይሩት። “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የሚቀጥሉት ሁለት መስኮቶች ጥቂት የአጫጫን አማራጮች አላቸው። “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ካደረጉ በኋላ “ኢንስቶል” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ፦

የአጫጫን ሂደቱን የሚያሳይ አሞሌ ያለው መስኮት ያያሉ። ሲጨርስ “ኢንስታሌሽን ኮምፕሊት” ይላል። እንደገና “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አሁን የመጫን ሂደቱን ሊያጠናቅቁ ነው።፡። ከ“ሾው ዘ ሪድሚ ፋይል” ቀጥሎ ያለውን ምልክት ያስወግዱ እና “ፊኒሽ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ይህ በዚህ ላይ ያበቃል። አሁን ወደ ሞዚላ ተንደርበርድ አጫጫን እንሂድ።

 

ሞዚላ ተንደርበርድን መጫን Anchor link

ከGPG4Win ጋር በተመሳሳይ ኹኔታ Thunderbird Setup 24.6.0.exe የሚለው ፋይል ላይ ሁለቴ ጠቅ በማድረግ ሞዚላ ተንደርበርድን ይጭናሉ። እንደተለመደው ይህን ፋይል ማሮጥ እንደሚፈልጉ ይጠይቅዎታል። “ራን” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ሶፍትዌሩን በመጫን ሞዚላ ተንደርበርድ በኮምፒውተርዎ ላይ ለውጥ ያደርጉ እንደኾን ፈቃድ ይጠይቅዎታል። “የስ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የሞዚላ ተንደርበርድ ሴትአፕ መስኮት ያያሉ። “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

በመቀጠል ከመደበኛ ውቅር እና ከብጁ ውቅር መካከል እንዲመርጡ ምርጫ ይሰጥዎታል። የመደበኛ ውቅር ምርጫውን ይጠብቁ እና “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የሞዚላ ተንደርበርድ ፋይሎች በኮምፒውተርዎ ላይ የት እንደሚጫኑ የሚያሳይ አጭር ክለሳ ይስጥዎታል። “ኢንስቶል” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የመጫን ሂደቱ ሲጠናቀቅ ሞዚላ ተንደርበርድን ማስጀመር የሚያስችል የመጨረሻ መስኮት ይመጣልዎታል። “ፊኒሽ” የሚለውን አዝራራ ጠቅ ያድርጉ።

 

ኤኒግሜልን ለመጫን የሚደረግ ዝግጅት Anchor link

ሞዚላ ተንደርበርድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያስጀምሩት ስለ አንዳንድ የነባሪ መዋቅሩ የሚጠይቅ ይህንን ትንሽ የማረጋገጫ መስኮት ያያሉ። “ሴት አስ ዲፎልት” የሚለውን አዝራር ጠቅ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

በመቀጠል አዲስ የኢሜል አድራሻ መፍጠር ይፈልጉ እንደኾን ይጠይቅዎታል። “ስኪፕ ዚስ ኤንድ ዩዝ ማይ ኤዚስቲንግ ኢሜል” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። አሁን ሞዚላ ተንደርበርድን ኢሜል ለመላክ እና ለመቀበል ያዋቅሩታል። ኢሜል ማንበብ እና መላክ የለመዱት በጂሜል.ኮም፣ ያሁ.ኮም ወይም አውትሉክ.ኮም አማካኝነት ብቻ ከኾነ ሞዚላ ተንደርበርድ አዲስ ልምምድ ቢኾንም በአጠቃላይ ግን ያን ያህል የተለየ አይደለም።

 

የሜል አድራሻን በሞዚላ ተንደርበርድ ላይ ማከል/መጨመር Anchor link

አዲስ መስኮት ይከፈታል።

ስምዎን፣ የኢሜል አድራሻዎን እና ለኢሜልዎ የማለፊያ ቃል ያስገቡ። የማለፊያ ቃልዎን ወይም የኢሜል አድራሻዎን ሞዚላ አያገኘውም። “ኮንቲኔው” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አብዛኛውን ጊዜ ሞዚላ ተንደርበርድ አስፈላጊውን ቅንብር ለይቶ ያውቃል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሞዚላ ተንደርበርድ የተሟላ መረጃ ስለማይኖረው ይህንን እራስዎ እንዲያስገቡ ያስፈልጋል። ጎግል ለጂሜል የሚሰጠው የአወቃቀር መመሪያዎችን ምሳሌ እዚህ ይመልከቱ፦

ኢንካሚንግ ሜል (IMAP) ሰርቨር - ሪኳየርስ SSL

 • imap.ጂሜል.ኮም
 • ፖርት: 993
 • ሪኳየርስ SSL፦ የስ

አውትጎይንግ ሜል (SMTP) ሰርቨር - ሪኳየርስ TLS

 • smtp.ጂሜል.ኮም
 • ፖርት፦ 465 ወይም 587
 • ሪኳየርስ TLS፦ የስ
 • ሪኳየርስ አውተንቲኬሽን ፦ የስ
 • ዩዝ ሴም ሴቲንግ አስ ኢንካሚንግ ሜል ሰርቨር

ሙሉ ስም ወይም የፊት ስም፦ [የግል ስሞ ወይም የሀሰት ስም]

የመለያ ስም ወይም የተጠቃሚ ስም፦ የእርስዎ ሙሉ የጂሜል አድራሻ (የተጠቃሚ ስም@ጂሜል.ኮም)። የጎግል መተግበሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ እባክዎ የተጠቃሚ ስም@ዩር_ዶሜን.ኮም ያስገቡ

የኢሜል አድራሻ፦ የእርስዎ ሙሉ የጂሜል አድራሻ (የተጠቃሚ ስም@ጂሜል.ኮም)። የጎግል መተግበሪያ ተጠቃሚ ከኾኑ እባክዎ የተጠቃሚ ስም@ዩር_ዶሜን.ኮም ያስገቡ

የማለፊያ ቃል፦ የእርስዎ የጂሜል ማለፊያ ቃል

ባለ ሁለት ማትሪያ ማመሳከሪያን ከጎግል (የስጋት ሞዴልዎን መሠረት አድርገው ሊጠቀሙ ይገባል) ጋር የሚጠቀሙ ከኾነ መደበኛ የጂሜል ማለፊያ ቃልዎን ከተንደርበርድ ጋር መጠቀም አይችሉም። ይልቁንም የጂሜል አድራሻዎን በተንደርበርድ ለመጠቀም ለመተግበሪያው የተወሰነ አዲስ የማለፊያ ቃል መፍጠር ያስፈልግዎታል። ይህን ለማድረግ የራሱ የጎግል መመሪያን ይመልከቱ። 

ሁሉንም መረጃ በትክክል ካስገቡ በኋላ “ደን” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ሞዚላ ተንደርበርድ የኢሜልዎን ቅጂዎች በኮምፒውተርዎ ላይ ማውረድ ይጀምራል። የሙከራ ኢሜል ለጓደኞችዎ ለመላክ ይሞክሩ።

 

ኤኒግሜልን መጫን Anchor link

ኤኒግሜል የሚጫነው ከሞዚላ ተንደርበርድ እና GPG4Win በተለየ መንገድ ነው። ቅድም እንደተጠቀሰው ኤኒግሜል የሞዚላ ተንደርበርድ ቅጥያ ነው። “ሜኑ በተን” ወይም ሃምበርገር በተን የሚባለው ላይ ጠቅ ያድርጉ እና “አድ-ኦንስ” የሚለውን ይምረጡ።

ይህም ወደ አድ-ኦንስ ማናጀር ትር ይወስድዎታል።

ትንሽ ምናሌን ለማምጣት የማሽን ምልክቱ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና “ኢንስቶል አድ-ኦንስ ፍሮም ፋይል” የሚለውን ይምረጡ። ይህም የፋይል መምረጫ መስኮትን ያመጣልዎታል።

የፋይል መምረጫ መስኮቱ የማውረጃ ማህደሩን የመክፈት ዕድሉ ከፍ ያለ ነው። ካልከፈተ ግን ወደ ማውረጃ ማህደሩ (ኤኒግሜል የተቀመጠው እዚህ ነው) ይሂዱ እና enigmail-1.7-tb+sm.xpi የሚለው ፋይል ላይ ጠቅ ካደረጉ በኋላ “ኦፕን” የሚለውን አዝራር ይጫኑ።

ኤኒግሚልን መጫን እንደሚፈልጉ ወይም እንደማይፈልጉ ማረጋገጫ የሚጠይቅ ትንሽ መስኮት ያያሉ። “ኢንስቶል ናው” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የኤኒግሜል ቅጥያ ከተጫነ በኋላ ሞዚላ ተንደርበርድ ኤኒግሜልን ለማግበር የድር ማሰሻውን እንደገና እንዲያስጀምሩ ይጠይቅዎታል። “ሪስታርት ናው” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ እና ሞዚላ ተንደርበርን እንደገና ያስጀምሩ።

ሞዚላ ተንደርበርድ እንደገና ሲጀምር የኤኒግሜል ቅጥያን የማዋቀር ሂደት የሚያስጀምር ተጨማሪ መስኮት ይከፈታል። “የስ, አይ ውድ ላይክ ዘ ዊዛርድ ቱ ጌት ሚ ስታርትድ” የሚለውን አዝራር እንደተመረጠ ያቆዩት እና “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉት።

ኤኒግሜል ኢሜልዎን መቼ ማመስጠር እንደሚፈልጉ ሦስት አማራጮችን ይሰጥዎታል። የነባሪ ምርጫው ኢሜሉን የሚልኩለት ሰው “የአደባባይ ቁልፍ” በእጅዎ ኖሮ የሚልኳቸውን ኢሜሎች እንዲያመሰጥር ከኾነ ኤኒግሜል ያመሰጥራል። ነገር ግን የተቀባዩ የአደባባይ ቁልፍ ከሌለዎት ኢሜሉን ሳያመሰጥር እንዳለ ይተወዋል። በተጨማሪም ሁልጊዜ ለሁሉም ሰው የሚልኩትን ኢሜል በPGP ቁልፍ ማመስጠር የሚያስችል ምርጫ አለዎት። ይህም ማለት ቀደም ብሎ የአደባባይ ቁልፋቸው የሌለዎትን ሰዎች ቁልፍ ማግኘት አለብዎት ማለት ነው። ወይም በአጠቃላይ የራስሰር አመስጣሪውን በአጠቃላይ አጥፍተው PGP ሲያስፈልግዎ ብቻ መጠቀም ይችላሉ።

ለእርስዎ ተገቢው ምርጫ ምን እንደኾነ አናውቅም። ይሁንና “ኮንቪኒያንት አውቶ ኢንክሪፕሽን” የሚለው ምርጫ የተሻለ አማራጭ እንደኾነ እናምናለን። በጥርጣሬ ውስጥ ከኾኑ “ዶንት ኢንክሪፕትማይ ሜሴጅ ባይ ዲፎልት” የሚለውን ይምረጡ። ከዛም “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አሁን በሚልኳቸው ሁሉም ኢሜሎች ላይ የዲጂታል ፊርማ ማኖር ይችላሉ። ኢሜልዎን በPGP መፈረም የኢሜሉ ተቀባይ እርሶ መልዕክት እንደላኩለት ማጣራት እና የመልዕክቱ ይዘት በሦስተኛ ወገን ያልተነካካ መኾኑን ማረጋገጥ ይችላል። ይህንን ገጽታ ለማስጀመር “ሳይን ማይ ሜሴጅስ ባይ ዲፎልት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። ነገር ግን ይህን የማድረግ የጎንዮሽ ጉዳቱ PGPን እንደሚጠቀሙ ኢሜል ለሚልኩለት ማንኛውም ሰው ማሳየቱ ነው። በአንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች (ቻይና፣ ኢራን፣ ቤላሩስ፣ እና አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ መንግስታትን ጨምሮ) ለግል ጥቅም እንኳን ፈቃድ የሌለዎትን ማመስጠሪያ መጠቀም ወንጀል ነው። ስለዚህ PGPን እንደሚጠቀሙ ለሌሎች ላለማሳወቅ በቂ ምክንያት አለዎት።

“ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አሁን ኤኒግሜል በሞዚላ ተንደርበርድ መዋቅር ላይ አንዳንድ ለውጦችን እንዲያደርግ የሚጠይቅ ምርጫ ያያሉ።

ዲቴልስ የሚለውን አዝራር ጠቅ ካደረጉ እነዚህ ለውጦች ምን እንደኾኑ ማየት ይችላሉ።

በነባሪነት PGP/MIME የሚጠቀሙ ከኾነ (እሱን በኋላ እናዋቅረዋለን) እንከን አልባ ሽግግር ለማድረግ የሚከተሉትን ምርጫዎች አለመምረጥ (መልሶ ማስቻል) ይችላሉ፦

 • ዲስኤብል ፍሎውድ ቴክስት
 • ቪው ሜሴጅ ቦዲ አስ ፕሌን ቴክስት
 • ዱ ኖት ኮምፖዝ HTML ሜሴጅስ

የመጨረሻው አማራጭ ኢሜልዎን በሚያመስጥሩበት እና በሚፈቱበት ወቅት ከሚያጋጥም ያልታሰበ ችግር ይከላከላል። ይጠንቀቁ! ይህንን ሳጥን ማመልከት የደመቀ፣ የተሰመረበት እና የቀለመ ጽሑፍ የመላክ አቅሞትን ይገፋል። ለውጡን ካዩ በኋላ “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ትንሹ መስኮት ይዘጋል። “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አሁን የግል እና ይፋዊ ቁልፎች መፍጠር ይጀምራሉ፡፡ የአደባባይ ቁልፎች ስነ መሰውር እና PGP መግቢያ የተሰኘው መመሪያችን ላይ ስለቁልፎች ምንነት ለመረዳት የተጻፈውን ያንብቡ፡፡

 

የአደባባይ ቁልፍ እና የግል ቁልፍ መፍጠር Anchor link

የኢንግሜል ቅጥያን መጫን እና ማዋቀር ተጠናቋል። አሁን የግል እና የአደባባይ ጥንድ ቁልፍዎን የመፍጠር አማራጭ አለዎት። ይህ መመሪያ ከዚህ በፊት የግል ቁልፍ ፈጥረው እንደማያውቁ ግምት ውስጥ በማስገባት የተዘጋጀ ነው።.

“ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ከአንድ በላይ የኢሜል አድራሻ ካላዋቀሩ በስተቀር ኤኒግሜል ቀድመው ያዋቀሩትን የኢሜል አድራሻዎን ይመርጣል። በመጀመሪያ ሊያደርጉት የሚገባው ነገር ለግል ቁልፍዎ ጠንካራ የኾነ የማለፊያ ሐረግ ማግኘት ነው።

ይህንን የማለፊያ ሀረግ በቃልዎ እስኪያስታውሱት ድረስ በወረቀት ላይ መጻፍዎን ያረጋግጡ። ወረቀቱንም መወሰዱን ወይም በሌላ ሰው መታየቱን በሚያውቁበት ስፍራ (ለምሳሌ የኪስ ቦርሳዎ) ያስቀምጡት። ይህንን ወረቀት በየቦታው ማዝረክረክ የለብዎትም።

“ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ኤኒግሜል ስለ ግል ቁልፍዎ እና እንዲሁም ስለ ቅንብር አወቃቀሩ አንዳንድ መረጃን ያሳያል። 4096 ቢት ርዝመት ያለው ቁልፍ እንዲፈጥሩ እናሳስባለን። “ኔክስት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ከኾነ ጊዜ በኋላ የቁልፍዎ የአገልግሎት ዘመን ያበቃል። ይህ በሚኾንበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ለእርሶ በሚልኳቸው አዳዲስ ኢሜሎች ላይ ቁልፉን መጠቀም ያቆማሉ። ይህም ለምን እንደኾነ ማስጠንቀቂያ ወይም ማብራሪያ ላያገኙ ይችላሉ። ስለዚህ በቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ማድረግ እና የአገልግሎት ዘመኑ ከሚያበቃበት ከወር ወይም ቀደም ብሎ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት ይጠበቅብዎታል።

አሁን ያለውን ቁልፍ አዲስ የወደፊት የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ በመስጠት የእድሜ ዘመኑን ማራዘም ወይም ከመጀመሪያ ጀምሮ አዲስ ቁልፍ በመፍጠር አሮጌውን ቁልፍ መቀየር ይቻላል። በሁለቱም ሂደቶች PGPን ተጠቅመው ኢሜል የሚልኩልዎትን ሰዎች ማግኘት እና የዘመነውን ቁልፍ እጃቸው ማስገባታቸውን ማረጋገጥ ሊያስፈልግዎ ይችላል። የአሁን ሶፍትዌሮች በራስ ሰርነት እምብዛም አይደሉም። ስለዚህ ለራስዎ ‘አስተዋሽ’ ያኑሩ፤ ይህን መተግበር የሚችሉ ካልመሰለዎት ደግሞ የቁልፉ የአገልግሎት ዘመን እንዳያበቃ አድርገው ማቀናበርን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ሲኾን ለወደፊቱ የግል ቁልፍዎ ከጠፋብዎት ወይም PGPን መጠቀም ካቆሙ ከብዙ ጊዜ በኋላ ሌሎች ሰዎች ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት ሊገለገሉበት ይችላሉ።

የተንደርበርድ ቁልፍዎ አገልግሎት የሚያበቃበትን ቀን ለማጣራት ኢንግሜይልን በመጫን “key management” የሚለውን ይምረጡ፡፡ ቁልፍዎን ከኢንግሜይል ቁልፍ አስተዳደር መስኮት ይፈልጉና ድርብ ጠቅ ያድርጉ፡፡ አዲስ መስኮት ይመስኮት ይከፈትና “Expiry” በሚለው ቦታ የአሁን ቁልፍዎ የአገልግሎት ጊዜ የሚያልቅበት ቀን ይታያል፡፡ አዲስ የአገልግሎት ማብቂያ ቀን ማስቀመጥ ከፈለጉ ከአሁን ቁልፍዎ የአገልግሎት ማብቂያ ቀን ጎን  “Change” የሚለውን ይጫኑ፡፡ የአገልግሎት መብቂያ ቀኑን ሲቀይሩ የተቀየረውን የአደባባይ ቁልፍ ለሚገናኙት ሰው መላክዎን ወይም በቁልፍ ማስቀመጫ ሰርቨር ላይ ማተምዎን አይርሱ፡፡

ኢንግሜይል ቁልፎችን አመንጭቶ ሲጨርስ ትንሽ መስኮት ይከፈትና አገልግሎቱን የመሻሪያ የምስክር ወርቀት አንዲፈጥሩ ይጠይቀዎታል፡፡ ይህ የመሻሪያ የምስክር ወረቀት መያዝ የሚጠቅመው የግል ቁልፍዎ በጠፋ ወይም በተሰረቀ ጊዜ የግል እና ይፋዊ ቁልፎችዎ እንዳይሰሩ ማድረግ በማስቻሉ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ይህንን የመሻሪያ የምስክር ወረቀት ከአደባባይ ቁልፍዎ በተለየ ቦታ በሲዲ በመቅዳት ወይም በፍላሸ ዲሰክ በማድረግ ደኅንነቱ የተጠበቀ ቦታ ያስቀምጡት፡፡ ይህንን የምስክር ወረቀት በቁልፍ ማሰቀመጫ ሰርቨር ላይ ማተም ሌሎች የPGP ተጠቃሚዎች የአደባባይ ቁልፎች እንዳይጠቀሙ ወይም እንዳያምኑ ያደርጋቸዋል፡፡  ይፋዊ ቁልፎቹን ማጥፋት የግል ቁልፎችን ከአገልግሎት ውጪ አያደርጋቸውም ምናልባት ሌሎች እርስዎ መፍታት የማይችላቸው የተመሰጠሩ መልዕክቶች ሊልኩ ይቻላሉ፡፡ “Generate Certificate” የሚለውን ይንኩ፡፡

የመሻሪያ የምስክር ወረቀትዎን የሚያስቀምጡበት ቦታ የሚያስመርጥዎ መስኮት ይከፈታል። ፋይሉን ኮምፒውተርዎ ላይ ማስቀመጥ ቢችሉም ለሌላ ጉዳይ የማይጠቀሙት እና ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ የሚያስቀምጡት ፍላሽ ድራይቭ ላይ ፋይሉን እንዲያስቀምጡ እናሳስባለን። በተጨማሪም ያልታሰበ የቁልፍ መሻርን ለመከላከል የመሻሪያ ምስክር ወረቀቱን ከቁልፉ ጋር ከኮምፒውተርዎ ላይ እንዲያጠፉት እናሳስባለን።

ፋይሉን በተለየ ሚስጥራዊ ዲስክ ላይ ማስቀመጥ ደግሞ ከሁሉም የተሻለ ነው። ይህን ፋይል የሚያስቀምጡበትን ቦታ ይምረጡ እና “ሴቭ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አሁን ኤኒግሜል የመሻሪያ ምስክር ወረቀቱን እንዲያስቀምጡ በድጋሚ ተጨማሪ መረጃን ይሰጥዎታል። “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

በመጨረሻ የግል ቁልፍ እና የአደባባይ ቁልፍ ማመንጨትን ጨርሰዋል። “ፊኒሽ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

 

በምርጫ የሚደረጉ የመዋቅር ሂደቶች Anchor link

ረጅም IDዎችን ማሳየት

የሚከተሉት ደረጃዎች ሙሉ በሙሉ በምርጫ የሚደረጉ ቢሆኑም OpenPGPን እና ኤኒግሜልን ለመጠቀም አስፈላጊ ሊኾኑ ይችላሉ። በአጭሩ ኪይ ID የሚባለው የጣት አሻራ ትንሹ ክፍል ነው። የአንድ ግለሰብን የአደባባይ ቁልፍ ወደማረጋገጡ ሲመጣ የጣት አሻራ የተሻለ መንገድ ነው። የነባሪውን ማሳያ መቀየር የሚያውቁትን የምስክር ወረቀት የጣት አሻራን ለማንበብ ቀላል ያደርገዋል። በመጀመሪያ ኮንፊገሬሽን የሚለውን አዝራር ቀጥሎም ኤኒግሜል ኦፕሽን በመጨረሻም ኪይ ማኔጅመንት የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ስም እና ኪይ IDን የሚያሳይ ሁለት ረድፍ ያለው መስኮት ይከፈታል።

በቀኝ በኩል ጥጉ ላይ ትንሽ አዝራር አለ። ረድፉን ለማዋቀር ይህንን አዝራር ጠቅ ያድርጉት። ኪይ ID ኦፕሽን በሚለው ፋንታ ፊንገርፕሪንት ኦፕሽን የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

አሁን ረድፉ ይህን ይመስላል፦

አሁን መደበኛ እና ሚስጥራዊ ኢሜልን ለመላክም ኾነ ለመቀበል የሚያስችል ስርዓት አዋቅረዋል። ከዚህ ቀትሎ ምስጢራዊ ኢሜል የሚለዋወጧቸው ሰዎችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ቅደም ተከተሉን በዝርዝር እናያለን።

 

PGP/MIME መጠቀም Anchor link

PGP/MIMEን ማስቻል የመጨረሻው በምርጫ የሚደረግ መዋቅር ሲኾን ይህም የተመሰጠረ እና የተፈረመ አባሪን መላክ ቀላል የሚያደርግ ነው።

ይህን ለመዋቀር የሜኑ በተንን ጠቅ በማድረግ በኦፕሽንስ ላይ ያንዣብቡ። በመቀጠልም አካውንት ሴቲንግስ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። ከዚያም የአካውንት ሴቲንግስ መስኮት ይከፈታል።

የአካውንት ሴቲንግስ መስኮት ሲከፈት OpenPGP ሴኪዩሪቲ የሚለውን ትር ጠቅ ያድርጉ። ከዛም ዩዝ PGP/MIME ባይ ዲፎልት ከሚለው ቀጥሎ ያለውን የማመልከቻ ሳጥን ያመልክቱ። ቀጥሎም ኦኬ የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። አሁን ኤኒግሜል PGP/MIMEን በነባሪነት ይጠቀማል።

PGPን መጠቀም የላኪውን እና የተቀባዩን መረጃ ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ኢሜልዎን አያመስጥርም። አሁን ባለው የኢሜል ስርዓት የላኪን እና የተቀባይ መረጃን ማመስጠር አይቻልም። ተንደርበርድን ከኤኒግሜል ቅጥያ ጋር መጠቀም የኢሜልዎን ይዘት ማመስጠር እና መፍታት የሚያስችል ቀላል መንገድን ይሰጥዎታል።

 

PGP እንደሚጠቀሙ ለሌሎች ማሳወቅ Anchor link

አሁን በኮምፒውተርዎ ላይ PGP አለዎት። በመኾኑም ሌሎች ሰዎች PGPን በመጠቀም የተመሰጠሩ መልዕክቶችን እንዲልኩልዎት PGPን እንደሚጠቀሙ መንገር ይጠበቅብዎታል።

PGPን እንደሚጠቀሙ ለሰዎች የሚያሳውቁበት ሦስት የተለያዩ መንገዶችን እንመልከት።

1. PGPን እንደሚጠቀሙ በኢሜል ማሳወቅ

የአደባባይ ቁልፍዎን ቅጂ በኢሜል አባሪ አድርገው በመላክ ለሌላ ሰው በቀላሉ ማሳወቅ ይችላሉ።

በሞዚላ ተንደርበርድ ውስጥ “ራይት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አድራሻ እና ርዕሰ ጉዳዩን ያስገቡ። ርዕሰ ጉዳዩ “የአደባባይ ቁልፍ” ሊኾን ይችላል። የኤኒግሜል ምናሌውን ጠቅ ያድርጉ እና “አታች ማይ ፐብሊክ ኪይ” የሚለውን ምርጫ ይምረጡ።

አሁን ኢሜሉን መላክ ይችላሉ። ተቀባዩም የላኩለትን የአደባባይ ቁልፍ ማውረድ እና መጠቀም ይችላል።

ይህንን ዘዴ ከተጠቀሙ ምናልት ኢሜሉ አስቀድሞ የተጠለፈ እና የተነካካ እንዳይሆን ተቀባዩ የአደባባይ ቁልፍ አሻራዎን በሌላ የመገናኛ መንገድ እንዲያረጋግጥልዎ ማድረግ መልካም ሃሳብ ነው።

2. በድረ ገጽዎ PGPን እንደሚጠቀሙ ለሰዎች ማሳወቅ

ኢሜል በመላክ ከማሳወቅ በተጨማሪ የአደባባይ ቁልፍዎን በድረ ገጽዎ ላይ በመለጠፍ ለሰዎች ማሳወቅ ይችላሉ። ቀላሉ መንገድ ፋይሉን ጭነው አገናኝ ያድርጉለት። ይህ መመሪያ እነዚህን ነገሮች እንዴት እንደሚተገብሩ አያሳይም ነገር ግን ወደፊት ጥቅም ላይ ለማዋል የምስክር ወረቀቱን በፋይል መልክ እንዴት እንደሚልኩ ማወቅ አለብዎት።

ኮንፊገሬሽን የሚለውን አዝራር ከዛም ኤኒግሜል ኦፕሽን በመቀጠልም ኪይ ማኔጅመንትን የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

የምስክር ወረቀቱን በደማቁ ከመረጡ በኋላ ምናሌውን ለማምጣት "ቀኝ ጠቅ" ያድርጉ እና "ኤክስፖርት ኪይስ ቱ ፋይል" የሚለውን ይምረጡ።

ሶስት አዝራሮች ያሉት ትንሽ መስኮት ብቅ ይላል። “ኤክስፖርት ፐብሊክ ኪይስ ኦንሊ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

“ኤክስፖርት ሴክሬት ኬይስ” የሚለውን አዝራር ጠቅ አለማድረግዎን ያረጋግጡ። ምክንያቱም የሚስጥር ቁልፍን ኤክስፖርት ማድረግ ሌሎች ሰዎች የማለፊያ ቃልዎን መገመት ከቻሉ እርስዎን መስለው ሊታዩ ስለሚችሉ ነው።

አሁን ፋይሉን ማስቀመጥ የሚያስችልዎ መስኮት ይከፈታል። ወደፊት በቀላሉ ፈልገው እንዲያገኙት፤ እባክዎን ፋይሉን በዶክመንት ማህደር ውስጥ ያስቀምጡት።

አሁን ይህን ፋይል እንደፈለጉ መጠቀም ይችላሉ።

3. የቁልፍ አግልጋይ ላይ መጫን

የቁልፍ አገልጋይ የአደባባይ ቁልፍን የመፈለግ እና የማውረድ ተግባርን ቀላል ያደርገዋል። አብዛኞቹ ዘመናዊ የቁልፍ አገልጋዮች ስምሙ ናቸው። ይህም ማለት በአንዱ አገልጋይ ላይ የተሰቀለ የአደባባይ ቁልፍ በመጨረሻ ለሁሉም አገልጋዮች ይደርሳቸዋል።

የአደባባይ ቁልፍዎን የቁልፍ አገልጋይ ላይ መስቀል የአደባባይ PGP ምስክር ወረቀት እንዳለዎት ለሰዎች ማሳወቂያ አመቺው መንገድ ነው። ይሁንና በቁልፍ አገልጋዮች የአሰራር ተፈጥሮ ምክንያት አንዴ የተሰቀለን የአደባባይ ቁልፍ መሰረዝ የሚያስችል መንገድ እንደሌለ እና መሻራቸውን ብቻ ማመልከት እንደሚችሉ ማወቅ አለብዎት።

የቁልፍ አገልጋይ ላይ የአደባባይ ቁልፍዎን ከመጫንዎ በፊት, የአደባባይ ቁልፍ እንዳለዎት መላው ዓለም እንዲያውቅ እንደሚፈልጉ እና እንደማይፈልጉ ጥቂት ጊዜ ወስደው ማሰብ ተገቢ ነው።

የቁልፍ አገልጋይ ላይ የአደባባይ ቁልፍዎን መጫንን ከመረጡ ወደ ኤኒግሜል ኪይ ማኔጅመንት መስኮት ይመለሱ።

ኪይሰርቨር ሜኑ አይተም የሚለውን ጠቅ ያድርጉ እና "አፕሎድ ፐብሊክ ኪይስ" የሚለውን ምርጫ ይምረጡ።

 

PGPን የሚጠቀሙ ሌሎች ሰዎችን መፈለግ Anchor link

1. በኢሜል የአደባባይ ቁልፍ ማግኘት

የአደባባይ ቁልፍን በኢሜል አባሪ ተደርጎ ተልኮልዎት ሊያገኙ ይችላሉ።

በአዲሱ መልዕክት ላይ ሁለቴ ጠቅ ሲያደርጉ አዲስ ትር ይከፈታል። በመስኮቱ የታችኛው ክፍል ላይ ያለውን አባሪ ያስተውሉ። በአባሪው ላይ ቀኝ ጠቅ ያድርጉ እና “ኢንፖርት OpenPGP ኪይ” የሚለውን ይክፈቱ። ትንሽ መስኮት ተከፍቶ የኢንፖርቱን ውጤት ይሰጥዎታል። "ኦኬ" የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የኤኒግሜል ማኔጅመንት መስኮትን እንደገና ከከፈቱ ውጤቱን ማጣራት ይችላሉ። ሁለቱም የግል ቁልፍ እና አደባባይ ቁልፍ ስላለዎት የእርስዎ የPGP ቁልፍ ደማቅ ነው። አሁን ኢንፖርት ያደረጉት የአደባባይ ቁልፍ ግን ደማቅ አይደለም። ምክኒያቱም ደግሞ የግል ቁልፍ አለመያዙ ነው።

2. የአደባባይ ቁልፍን በፋይል መልክ ማግኘት

የአደባባይ ቁልፍን ከድረ ገጽ በማውረድ ወይም አንድ ሰው በመስመር ላይ ግንኙነት ሶፍትዌር አማካኝነት ልኮልዎት ሊያገኙ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ፋይሉን በማውረጃ ማህደር ውስጥ እንዳወረዱት ያስቡ።

የኤኒግሜል ኪይ ማናጀርን ይክፈቱ እና “ፋይል” የሚለው ምናሌ ላይ ጠቅ ያድርጉ። “ኢንፖርት ኪይስ ፍሮም ፋይል” የሚለውን ይምረጡ።

የአደባባዩ ቁልፉ እንደ .asc፣ .pgp፣ ወይም .gpg ያሉ የተለያየ የፋይል ስም መጨረሻ ሊኖረው ይችላል። ፋይሉን ይምረጡ እና “ኦፕን” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የኢንፖርቱን ውጤት የሚያሳይ ትንሽ መስኮት ይከፈታል። “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

3. የአደባባይ ቁልፍን ከቁልፍ አገልጋይ ማገኘት

የቁልፍ አገልጋይ የአደባባይ ቁልፎችን ለማግኘት በጣም ጠቃሚ መንገድ ነው። የአደባባይ ቁልፍን ለማግኘት ይሞክሩ። የኪይ ማናጀሩን ይክፈቱ ከዛም “ኪይሰርቨር” ምናሌን ጠቅ ያድርጉ እና “ሰርች ፎር ኪይስ” የሚለውን ይምረጡ።

የመፈለጊያ መስክ ያለው ትንሽ መስኮት ብቅ ይላል። በሙሉ የኢሜል አድራሻ፣ በከፊል የኢሜል አድራሻ፣ ወይም በስም መፈለግ ይችላሉ። በዚህ መመሪያ የሚፈልጉት “eff.org” የሚል የያያዘ የምስክር ወረቀትን ነው።

በርካታ አማራጮች ያሉት ትልቅ መስኮት ብቅ ይላል። ቁልቁል ከሸበለሉት ሰያፍ እና አመድማ የኾኑ ጥቂት የምስክር ወረቀቶችን ይመለከታሉ። አነዚህም የተሻሩ ወይም በራሳቸው ሰዓት የአገልግሎት ጊዜያቸው የተጠናቀቀ የምስክር ወረቀቶች ናቸው።

ለምሳሌ የዳንኤልን የአደባባይ ቁልፍ እንውሰድ። እርሱም አንድ የአገልግሎት ጊዜው ያለቀ ወይም የተሻረ የምስክር ወረቀት እና አንድ የሚሠራ የምስክር ወረቀት አለው። በግራ በኩል ያለውን ሳጥን ጠቅ በማድረግ የሚታወጀውን የምስክር ወረቀት ይምረጡ ከዛም ኦኬ የሚለውን አዝራር ይጫኑ።

በአንዳንድ አጋጣሚዎች አንድ ሰው ከአንድ በላይ የሚሰሩ የምስክር ወረቀቶች ሊኖሩት ይችላል። ያስተውሉ ማንኛውም ግለሰብ ለሌላ ሰው የአደባባይ ምስክር ወረቀትን መጫን እንደሚችል እና ከሁለቱ ቁልፎች አንዱ ተጓዳኝ የኢሜል አድራሻው ባለቤት ላይኾን እንደሚችል ይወቁ። በዚህ ጊዜ የጣት አሻራን ማረጋገጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

ከተሳካልዎ ይህን የሚያውጅ ትንሽ የማሳወቂያ መስኮት ብቅ ይላል፦

የኤኒግሜል ኪይ ማናጀር የተጨመሩትን የምስክር ወረቀቶች ያሳይዎታል፦

 

በPGP የተመሰጠረ ኢሜልን መላክ Anchor link

አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰጠረ ኢሜል ለተቀባይ ይልካሉ። በሞዚላ ተንደርበርድ ዋናው መስኮት ላይ “ራይት” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። አዲስ መስኮት ይከፈታል።

መልዕክትዎን ይጻፉ እና የተቀባዩን አድራሻ ያስገቡ። ለዚህ ሙከራ ቀድመው የሚያውቁት የአደባባይ ቁልፍ ያኖሩለትን ተቀባይ ይምረጡ። ኤኒግሜል ይህንን ያገኝ እና ኢሜሉን ወዲያውኑ ያመሰጥረዋል።

ያስተውሉ ርዕሰ ጉዳዩ አይመሰጥርም። ስለዚህ ልክ እንደ “ሄሎ” ያሉ ጉዳት የለሽ መልዕቶችን መርጠው ይጠቀሙ።

“ሴንድ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ሲያደርጉ የPGP ቁልፍዎን የማለፊያ ቃል የሚያስገቡበት መስኮት ይመጣልዎታል።ያስታውሱ ይህ ከኢሜልዎ የማለፊያ ቃል የተለየ ነው!

የማለፊያ ቃልዎን ካስገቡ በኋላ “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። ኢሜሉ ምስጢራዊ ይኾን እና ይላካል።

.

የኢሜሉ ዋና መልዕክት ምስጢራዊ ይኾን እና ይቀየራል። ለምሳሌ ይህ ጽሑፍ፦

ወደዚህ ይቀየራል፦

 

በPGP የተመሰጠረ ኢሜልን መቀበል Anchor link

የተመሰጠረ ኢሜልን በሚቀበሉበት ወቅት ምን እንደሚኾን በቅደም ተከተል እንመልከት። ሞዚላ ተንደርበርድ አዲስ ኢሜል እንዳለዎት ያሳውቅዎታል። በመልዕክቱ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

የPGP ቁልፍዎን የማለፊያ ቃል የሚጠይቅ ትንሽ መስኮት ይከፈታል። ያስታውሱ የኢሜልዎን የማለፊያ ቃል እንዳያስገቡ። “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አሁን መልዕክቱ ተፈትቶ ይታያል።

 

የPGP ቁልፍን መሻር Anchor link

የPGP ቁልፍዎን በኤኒግሜል በይነ-ገጽ አማካኝነት መሻር

በኤኒግሜል የመነጨው የPGP ቁልፍ ከአምስት ዓመት በኋላ ወዲያውኑ የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃል። ስለዚህ የቁልፍዎ የአገልግሎት ዘመን ካበቃ እና ፋይልዎ ሙሉ በሙሉ ከጠፋብዎት በኋላ ሰዎች ሌላ ቁልፍ መጠየቅ እንዳለባቸው እንደሚያውቁ ተስፋ ያድርጉ።

የPGP ቁልፉ የአገልግሎት ዘመኑ ከማብቃቱ በፊት ለማቦዘን በቂ ምክንያት ሊኖርዎት ይችላል። ምናልባት አዲስ እና ጠንካራ የPGP ቁልፍ ማመንጨት ይፈልጉ ይኾናል። በኤኒግሜል የPGP ቁልፍዎን ለመሻር ቀላሉ መንገድ የኤኒግሜል ኪይ ማናጀርን መጠቀም ነው።

በእርስዎ የPGP ቁልፍ (ደማቅ ነው) ላይ ቀኝ ጠቅ ያድርጉ እና “ሪቮክ ኪይ” የሚለውን ምርጫ ይምረጡ።

ምን እንደሚከሰት የሚያሳውቅዎ እና የእርስዎን ማረጋገጫ የሚጠይቅ መስኮት ብቅ ይላል። “ሪቮክ ኪይ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የማለፊያ ቃል መስኮት ይከፈታል። የPGP ቁልፍ የማለፊያ ቃልዎን ያስገቡ እና “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አሁን እንደተሳካልዎት የሚያሳውቅ አዲስ መስኮት ይከፈታል። “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ወደ ኤኒግሜል ኪይ ማናጀር መስኮት ሲሄዱ በPGP ቁልፍዎ ላይ ለውጥን ይመለከታሉ። አሁን የPGP ቁልፍዎ ሰያፍ እና አመድማ ይሆናል።

 

የPGP ቁልፍን በመሻሪያ ምስክር ወረቀት መሻር Anchor link

ቀደም ሲል እንደተገለጸው በኤኒግሜል የመነጨው የPGP ቁልፍ ከአምስት ዓመት በኋላ ወዲያውኑ የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃል። ስለዚህ የቁልፍዎ የአገልግሎት ዘመን ካበቃ እና ፋይልዎ ሙሉ በሙሉ ከጠፋብዎት በኋላ ሰዎች ሌላ ቁልፍ መጠየቅ እንዳለባቸው እንደሚያውቁ እርግጠኛ ይሁኑ።

ቅድም እንደገለጽነው የPGP ቁልፍን የአገልግሎት ዘመኑ ከማብቃቱ በፊት ለማቦዘን በቂ ምክኒያት ሊኖርዎ ይችላል።

በተመሳሳይ ኹኔታ ሌሎች ሰዎችም በመስራት ላይ ያለን ቁልፍ ለመሻር በቂ ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል።

ቁልፋቸውን መሻር እንደሚፈልጉ የሚያሳውቅ የመሻሪያ ምስክር ወረቀቶች ከጓደኞችዎ ተልኮ ሊያገኙ ይችላሉ።

በቀደመው ክፍል በኤኒግሜል ኪይ ማናጀር አማካኝነት ቁልፍን በሚሽሩበት ወቅት ኤኒግሜል በውስጥ የመሻሪያ ሰርተፍኬት እንደሚያመነጭ እና ኢንፖርት እንደሚያደርግ ተመልክተው ይኾናል። ነገር ግን በእዚህኛው የመሻሪያ መንገድ ቀደም ሲል ያመነጩት የመሻሪያ የምስክር ወረቀት ስላለዎት ቁልፍዎን ለመሻር እርሱን ይጠቀማሉ።

ከኤኒግሜል ኪይ ማናጀር ይጀምሩ እና “ፋይል” የሚለውን ምናሌ ጠቅ ያድርጉ። በመቀጠልም “ኢንፖርት ኪይስ ፍሮም ፋይል” የሚለውን ይምረጡ።

የመሻሪያ ምስክር ወረቀቱን መምረጥ የሚያስችልዎ መስኮት ይከፈታል። ፋይሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና “ኦፕን” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

የምስክር ወረቀቱ በተሳካ ኹኔታ ኢንፖርት እንደተደረገ እና ቁልፉ እንደተሻረ ማረጋገጫ ያገኛሉ። “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

አንዴ “ኦኬ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ካደረጉ በኋላ ወደ ኤኒግሜል ኪይ ማናጀር ይመልስዎት እና የሻሩት የምስክር ወረቀት አመድማ እና ሰያፍ ኾኖ ያዩታል።

የሻሩት ቁልፍ የራስዎ ከኾነ እና የአደባባይ ቁልፍዎን ከዚህ በፊት በቁልፍ አገልጋዩ ላይ የጫኑ ከኾነ ሌሎች ሰዎች አይተው ከዚህ በኋላ እንዳይጠቀሙት ለማድረግ አሁን የሻሩትን ቁልፍ በቁልፍ አገልጋዩ ላይ ደግመው መጫን ይጠበቅብዎታል።

አሁን ሁሉም ተገቢ መሳሪያዎች ስላለዎት በPGP የተመሰጠረ ኢሜል መላክን ይሞክሩ።

JavaScript license information