የውሂብ ደኅንነት ጥበቃ
Last Reviewed: November 02, 2018
ስማርት ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ታብሌት ካልዎት ሁልጊዜም የሚንቀሳቀሱት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሂብ ተሸክመው ነው፡፡ የእርስዎ ማኀበራዊ ዕውቂያዎች፣ ግላዊ ግኝኙነቶች፣ የግል ሰነዶች፣ፎቶግራፎች(ምንም አልባትም ደርዘን እና በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ምስጢራዊ መረጃዎች) የመሳሰሉት በዲጂታል መሣሪያዎ ከሚያስቀምጧቸው ነገሮች ውስጥ የተወሰኑ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በጣም ብዙ ውሂብ ስለምንይዝ እና ስለምናስቀምጥ ደኅንነቱን መጠበቅ ከባድ ነው፡፡ በቀላሉ ሊወሰድ የሚችል መሆኑ ደግሞ የበለጠ ከባድ ያደርገዋል፡፡
ውሂብዎ ድንበር ላይ ሊያዝ፣ መንገድ ላይ ሊሰረቅ ወይም ከቤትዎ ሊዘረፍ እና በጥቂት ሰከንዶች ኮፒ ሊደረግ ይችላል፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ በይለፍ ቃል፣ በግላዊ መለያ ቁጥር ወይም በፊት ገጽ ቢቆለፍም እንኳን መሣሪያው ከተያዘ ውሂቡን መጠበቅ አይቻልም፡፡ በአንጻራዊንት እነዚህን ቁልፎች በቀላሉ በማለፍ ወሂብ በቀላሉ በሚነበብ መልኩ ከውስጥ ይገኛል፡፡ ባለጋራ ያለ የይለፍ ቃል የእርስዎን ውሂብ ለመቅዳት ወይም ለማጥናት የሚጠበቅበት ወደ መሣሪያው መግባት ብቻ ነው፡፡
ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት መሣሪያዎን በግዘፍ(ከነ ነፍሱ) የሚሰርቁ ሰዎች በቀላሉ እንዳያገኙት ማድረግ ይችላሉ፡፡የውሂብዎን ደኅንነት መጠበቅ የሚያችልዎት የተወሰኑ መንገዶችን እዚህ ያገኛሉ፡፡
ውሂብዎን ያመስጥሩ anchor link
ምስጠራ ከተጠቀሙ የእርስዎን የተመሰጠረ ውሂብ ለመፍታት ባለጋራዎ የሚያስፈልገው መሣሪያዎ እና የይለፍ ቃልዎን ነው፡፡ ስለዚህ የተሰወኑ ሰነዶችን ማቀፊያዎችን ሳይሆን ውሂብዎን በሙሉ ማመስጠር እጅግ የበለጠ ደኅንነት ይሰጣል፡፡ አብዛኛዎቹ ስማርት ስልኮች እና ኮምፒውተሮች ሙሉ ዲስክ ምስጠራ አማራጭ ይሰጣሉ፡፡
ለስማርት ስልኮች እና ታብሌቶች፡-
- አንድሮይድ መጀመሪያ አዲስ ስልክ ሲያደራጁ ወይም ወደፊት በፈለጉበት ጊዜ ሙሉ ዲስክ ምስጠራ በሁሉም መሣሪያዎች ያቀርባል፤ ቅንብር ውስጥ “Security” ጋር ያገኙታል፡፡
- እንደ አይፎን እና አይፓድ ያሉ የአፕል መሣሪያዎች “Data Protection” ብለው ይገልጹታል፡፡ ያብሩትና የይለፍ ኮድ ያስገቡ፡፡
ለኮምፒውተር፡-
- አፕል በማክኦኤስ ፋይልቫልት የሚባል አብሮ የተሰራ ሙሉ ዲስክ ምስጠራ ያቀርባል፡-
- ሊኒክስ ዲስትሪቡሽን አብዛኛውን ጊዜ ስርዓተ ክውናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲዳራጁ ሙሉ ዲስክ ምስጠራን ያቀርባል፡፡
- ዊንዶውስ በኋላ ደግሞ ቪሲታ ቢትሎከር የሙሉ ዲስክ ምስጠራ አካተዋል፡፡
የቢትሎከር ኮድ የተዘጋ እና በባለቤትነት የተያዘ ነው፡፡ ይህም ማለት ምን ያህል አስተማማኝ እንደሆነ ለማወቅ ለውጭ ገምጋሚዎች ከባድ ነው፡፡ ቢትሎከርን ለመጠቀም ማይክሮሶፍት ያለ ምንም የተሸሸገ ተጋላጭነት ደኅንነቱ የተጠበቀ የማከማቻ ስርዓት ያቀርባል ብለው ማመን ይኖርብዎታል፡፡ በሌላ በኩል አስቀድመው ዊንዶውስ እየተጠቀሙ ከሆነ በተመሳሳይ ደረጃ ማይክሮሶፍትን ይተማመኑበታል ማለት ነው፡፡ በዊንዶውስ ወይም በቢትሎከር ውስጥ ባለ የጀርባ የመረጃ መረብ ስለላ ጥቅሙን ሊያውቁ ወይም ሊጠቀሙባቸው ከሚችሉ ባለጋራዎች ስጋት ካለብዎት እንደ ጂኤንዩ/ሊኒክስ ወይም ቢኤስዲ የመሳሰሉ አማራጭ ክፍት ምንጭ ስርዓቶችን ለመጠቀም ግንዛቤ ውሰዱ፤ በተለይ የደኅንነት ጥቃቶች ለመቋቋም ተብለው የጠነከሩ እንደቴይልስ ወይም ኩብዝ ኦኤስ ያሉትን ይጠቀሙ፡፡ እንደ አማራጭም የሃርድ ድራይቭን ለማመስጠር ቬራክሪፕትየዲስክ ምስጠራ ሶፍትዌርን ለመጫን ያስቡ፡፡
ያስታውሱ፡- መሣሪያዎ ምስጠራውን በፈለገው ስም ይጥራው ጥሩ የሚሆነው እንደ የይለፍ ቃልዎ ጥሩነት ነው፡፡ አንድ ባለጋራ መሳሪያዎን በእጁ ካስገባ የይለፍ ቃልዎን ለማወቅ ረጅም ጊዜ አለው፡፡ ጠንካራና የማይረሳ የይለፍ ቃል ለመፍጠር ዳይስ እና የቃላት ዝርዝር መጠቀም ውጤታማ መንገድ ነው፡፡ እነዚህ ቃላት አንድ ላይ በመሆን "የይለፍ ሐረግ" ይባላሉ፡፡ "የይለፍ ሐረግ" ለተጨማሪ ደኅንነት ሲባል የረዘመ የይለፍ ቃል አይነት ነው፡፡ ለዲስክ ምስጠራ ቢያንስ ስድስት ቃላትን መምረጥ እንመክራለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ጠንካራ የይለፍ ቃል መፍጠር የሚለውን መመሪያችንን ይመልከቱ፡፡
ምንአልባት ለመልመድ እና በስማርት ስልክዎ ወይም ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ላይ ረጅም የይለፍ ሐረግን ለመተየብ አስቸጋሪ ሊሆንብዎ ይችላል፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ምስጠራ በአዘቦት መግባትን ለመከልከል ጠቃሚ ቢሆንም እርስዎ መጠቀም ያለብዎት የምር ምስጢራዊ መረጃዎችን ባለጋራ እንዳይደርስበት ለመደበቅ ነው፤ አሊያ የበለጠ ደኅንነቱ ወደ በተጠበቀ መሣሪያ ይገልብጡት፡፡
ደኅንነቱ የተጠበቀ መሣሪያ ይፍጠሩ anchor link
ደኅንነቱ የተጠበቀ ከባቢን ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ በጣም ሲጎብዙ የይለፍ ቃሎችን፣ ልማዶችን እና ምናልባትም በዋናው ኮምፒተርዎ ወይም መሣሪያዎ ላይ የሚጠቀሙት ሶፍትዌሮች ሊለውጡ ይችላሉ፡፡ በጣም በሚሰንፉ ጊዜ ደግሞ ምስጢራዊ መረጃን እየረሱ እንደሆነ ወይም አደገኛ ልምዶችን እየተጠቀሙ ስለመሆኑ ዘወትር ቢያሰላስሉም ችግሮችን ሲያውቁ መፍትሄዎችን ላይተገብሩ ይችላሉ ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ ለመነጋገር የሚፈልጉት ሰዎች ደኀንነቱ ያልተጠበቀ የዲጂታል ልምዶችን አሏቸው፡፡ ለምሳሌ፣ የስራ ባልደረባዎች ከእነርሱ የኢሜይል የሚመጡ አባሪዎችን እንዲከፍቱላቸው ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳን ባለጋራዎ የስራ ባልደረቦችዎ በመምሰል ሸርዌር ሊልክዎ ቢችልም፡፡
ታዲያ መፍትሔው ምንድን ነው? በጣም ጠቃሚ እና ዋጋ ያላቸው ውሂቦች እና ግንኙነቶችን የበለጠ ደኅንነቱ በተጠበቀ መሣሪያ ለማስቀመጥ ያስቡ፡፡ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሣሪያዎን የሚስጥራዊ ውሂብዎን ዋና ኮፒ ማስቀመጫ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ይህንን መሣሪያ አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ይጠቀሙበት፡፡ ሲጠቀሙም ከሌላው ጊዜ የተለየ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ የተላኩ አባሪዎችዎን መክፈት ወይም ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ሶፍትዌር መጠቀም ሲፈልጉ በሌላ መሣሪያ ይጠቀሙ፡፡
ተጨማሪ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ ኮምፒውተር እርስዎ እንደሚያስቡት በጣም ውድ አማራጭ አይደለም፡፡ በአብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል እና ጥቂት ፕሮግራሞችን ብቻ የሚያስተዳድረው ኮምፒውተር በጣም ፈጣን ወይም አዲስ መሆን አያስፈልገውም፡፡ ለአንዳንድ ዘመናዊ ላፕቶፕ ወይም ስልክ በሚገዙበት ገንዘብ ሽራፊ ኔትቡክ(ትንሽ ላፕቶፐ) መግዛት ይችላሉ፡፡ አሮጌ ስልኮችም እንደ ቴይልስ ያሉ ሶፍትዌሮችን ከአዳዲስ ሞዴሎች ጋር አብሮ ከሚሰሩት የበለጠ የመስራት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ አንዳንድ አጠቃላይ ምክሮች በአብዛኛው ጊዜ እውነት ናቸው፡፡ መሣሪያ ወይም ስርዓተ ክወና ሲገዙ የሶፍትዌር ዝማኔዎችን የመጨረሻው ያድርጉ፡፡ ዝማኔዎች ብዙውን ጊዜ ጥቃት በሚያስከትሉ የቆዩ ኮዶች ላይ ያሉ የደኅንነት ችግሮችን ሊጠግኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ የቆዩ ስርዓተ ክወናዎች ከአሁን በኋላ ሊሰሩ አይችሉም፤ ለደህንነት ማዘመኛዎችም ጭምር፡፡
ደኅንነቱ የተጠበቀ ኮምፒውተር ስናደራጅ ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ምን እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን? anchor link
- መሣሪያዎ በደንብ የተደበቀ፣ ቢነካካ ሊያውቁት በሚችልበት ቦታ የተቆለፈ የቁም ሳጥን መሳቢያ ውስጥ ያስቀመጡት፤ ለማንም ያስቀሙበትን ስፍራ አይንገሩ፡፡
- የኮምፒውተርዎ ሐርድ ድራይቭን በጠንካራ የይለፍ ሐረግ ይመስጥሩት፤ ቢሰረቅ እንኳን ያለ የይለፍ ሐረግ ሳይነበብ፣ ሊነበብ የማይችል እንደሆነ ይቆያል፡፡
- እንደ ቴይል ያሉ የግላዊነት እና የደኅንነት-ተኮር ስርዓተ ክወና ይጫኑ፡፡ በዕለት ተዕለት ስራዎ ውስጥ ነጻ-ምንጭ ስርዓተ ክወና የመጠቀም (ወይም የመፈለግ) ምርጫ ላይኖርዎት ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በዚህ ደኀንነቱ የተጠበቀ ኢሜይሎች ወይም ፈጣን መልዕክቶች ብቻ ማከማቸት፣ ማረም እና መፃፍ የሚፈልጉ ከሆነ, ቴይል ጥሩ ውጤት ይኖረዋል፤ ከፍተኛ የደኅንነት ቅንብሮችንም በነባሪነት ይዟል፡፡
- መሣሪያዎን ከኢንተርኔት ጋር አያገናኙ፡፡ ራስዎን ከመስመር ላይ ጥቃት እና ስለላ ለመከላከል እጅግ የተሻለው መንገድ ከኢንተርኔት ጋር አለመገናኘት መሆኑ አያስገርምም፡፡ መሣሪያዎ ከየትኛውም አውታረመረብ ወይም ዋይፋይ ጋር አለመገናኘቱን እርግጠኛ ይሁኑ፤ ሰነዶችን እንደ ዲቪዲ ወይም ዩኤስቢ ድራይቭ ባሉ ግዘፍ ያላቸው ማስተላለፊያ መንገዱች ተጠቅመው ይጫኑ፡፡ በአውታረመረብ ደኅንነት በኮምፒውተርዎ እና በቀረው መሀል ያለ “የአየር ክፍተት ” የሚባል ነገር አለ፡፡ ይህንን አማራጭ የሚጠቀሙት ብዙ ጊዜ የማይጠቀሙበት ነገር ግን መቼም ሊያጡት የማይፈልጉትን(እንደ የምስጠራ ቁልፍ ፣ የይለፍ ቃላት ዝርዝር ወይም የሆነ የሚያምኖት ሰው በአደራ እርስዎ ጋር ያስቀመጠው የግል መረጃ) ውሂብ ለማስቀመጥ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከሙሉ ኮምፒውተር ይልቅ ሽሽግ የማስቀመጫ መሣሪያ ለመጠቀም ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ የተመሰጠረ የዩኤስቢ ቁልፍ ልክ ከኢንተርኔት ጋር እንዳልተገናኘ ሙሉ ኮምፒውተር በቀላሉ መሸሸግ የሚችል ጠቃሚ(ወይም ጥቅም አልባ) ሊሆን ይችላል፡፡
- ወደ ተለመዱ መለያዎችዎ አይግቡ፡፡ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሣሪያዎን ከኢንተርኔት ጋር ለመገናኘት የሚጠቀሙ ከሆነ ከዚህ መሣሪያ ሆነው ግንኙነት የሚደርጉበት የተለየ የኢሜል መለያ ወይም ድር ይፍጠሩ፡፡ እናም ከእነዚህ አገልግሎቶች የአይፒ አድራሻዎን ለመከለል ቶር (ለሊኒክስ፣ ለማክኦኤስ እና ዊንዶውስ መመሪያዎችን ይመልከቱ፡፡) ይጠቀሙ፡፡ የሆነ አካል የእርስዎን ማንነት በሸርዌር ለማጥቃት ወይም ግንኑነትዎን ሰብሮ ለማግባት ከመረጠ ቶር በእርስዎ ማንነት እና በዚህ መሣሪያ መሀል በመግባት በመነጠል መርዳት ይችላል፡፡
አንድ ደኀንነቱ የተጠበቀ አንድ መሣሪያ ጠቃሚ እና ምስጢራዊ መረጃዎች ከባለጋራ ለመጠበቅ ቢረዳም አንድ የታወቀ የጥቃት ዒላማንም ይፈጥራል፡፡ መሣሪያው ከተበላሸ በአንድ ቅጂ ብቻ ያልዎትን ውሂብ የማጣትም አደጋ አለ፡፡ እርስዎ ውሂብዎን በሙሉ ማጣትዎ ባለጋራዎን የሚጠቅም ከሆነ ምንም እንኳን ደኀንነቱ የተጠበቀ ቢሆንም አንድ ቦታ ብቻ አያስቀምጡ፡፡ ቅጂውን አመስጥረው ሌላ ቦታ ያስቀምጡ፡፡
ስለ ደኀንነቱ የተጠበቀ መሣሪያ የሀሳብ መለያየት ደኅንነቱ ያልተጠበቀ መሣሪያ እንዲኖር ያደርጋል፤ ይህ መሣሪያ ወደ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ወይም አደጋ ያለው ሥራ ሲከውኑ የሚጠቀሙት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል በርካታ ጋዜጠኞች እና ተሟጋቾች ሲጓዙ አንድ መሰረታዊ ኔትቡክ ይይዛሉ፡፡ ይህ ኮምፒዩተር ምንም አይነት ሰነዶች ወይም የተለመደው ዕውቂያ ወይም የኢሜይል መረጃ የለውም ስለዚህ ቢቀማ ወይም ቢቃኝ የሚደርሰው ኪሳራ ትንሽ ነው፡፡ ለሞባይል ስልኮች ተመሳሳይ ስልት ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ስማርትፎን የሚጠቀሙ ከሆነ ለተወሰኑ ጉዳዮች ሲጓዙ ርካሽ ተንቀሳቃሽ ስልክ መግዛትን ግምት ውስጥ ያስገቡ፡፡