Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ዲበ ውሂብ ለምን አስፈላጊ ሆነ

Last Reviewed: March 12, 2019

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

ዲበ ውሂብ አብዛኛውን ጊዜ ከንግግርዎ/ወይይትዎ ይዘት ውጭ ያለውን ሁሉንም ነገር ይገልጻል፡፡ ዲበ ውሂብ ከአንድ የፖስታ ወረቀት ጋር እኩል ሊሆን ይችላል፡፡ ልክ እንደ አንድ ፖስታ ወረቀት እንደ መልእክት ላኪ፣ ተቀባይ እና የመልዕክቱ መድረሻ መረጃ የያዘ ሲሆን ዲበ ውሂብም እንዲሁ ያደርጋል፡፡ ዲበ ውሂብ ሲልኩ እና ስለቀበሉ የሚፈጥሩት የዲጂታል ግንኙነቶች መረጃ ነው፡፡ የተወሰኑ የዲበ ውሂብ ምሳሌዎች እነዚህን ያካትታሉ:-

  • የኢሜይል መልዕክትዎ ርዕስ
  • ንግግርዎ የፈጀው ጊዜ
  • ንግግሩ የተከናወነበት የጊዜ መዋቅር
  • መልዕክቱን ሲለዋወጡ የነበሩበት ስፍራ(ከእርስዎ ጋር የሚነጋገረውን ሰው ጨምሮ)

ታሪክ እንደሚያስረዳን አሜሪካንን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገሮች ዲበ ውሂብ፣ ከግንኙነት ይዘት ይልቅ አነስ ያለ የግለኝነት ጥበቃ ይደረግለታል። ለምሳሌ በበርካታ ሀገሮች ፖሊስ ስልክዎን በመጥለፍ የሚያወሩትን ከመስማት ይልቅ ባለፈው ወር ለማን ስልክ እንደደወሉ የሚያሳይ መረጃ በቀላሉ ማግኘት ይችላል።

ዲበ ውሂብን የሚሰበስቡ ወይም የሚጠይቁ መንግስታት ወይም የቴሌኮሚኒኬሽን ኩባንያዎች የሚከራከሩት ዲበ ውሂብን መግለጥ (እና መሰብሰብ) ምንም ጉዳት አያስከትልም በማለት ነው። እንዳለመታደል ሆኖ እነዚህ የመከራከሪያ ነጥቦች ትክክል አይደሉም፡፡ በጣም ትንሿ የዲበ ውሂብ ናሙና እንኳን የአንድን ግለሰብ ህይወት እንደሌንስ አጉልቶ የሚሳይ መረጃ ሊሰጥ ይችላል።  ለመንግስታት እና ኩባንያዎች ዲበ ውሂብን መሰብሰብ ምን ያህል በጣም ወሳኝ የሆነ እንመልከት፦

  • ከምሽቱ 2:24 ላይ የስልክ ላይ የወሲብ አገልግሎት ወደሚሰጥበት በመደወል ለ18 ደቂቃዎች እንዳወሩ ያውቃሉ። ስለምን እንዳወሩ ግን አያውቁም።
  • ከጎልደን ጌት ድልድይ ላይ ሆነው እራስን ማጥፋት የመከላከል አገልግሎት ወደሚሰጠጥበት መደወልዎን ያውቃሉ ነገር ግን የደወሉበት የመነጋገሪያ ርእስ ሚስጥር እንደሆነ ይቆያል።
  • ከኤችአይቪ ምርመራ አገልግሎት የኢሜል መልእክት እንደደረስዎ፣ በመቀጠል ዶክተርዎ ጋር እንደደወሉ እና በተመሳሳይ ሰዓት የኤችአይቪ የምክር አገልግሎት ቡድንን መካነ ድር እንደጎበኙ ያውቃሉ። ነገር ግን የተላከልዎት ኢሜል ይዘት ምን እንደሆነ ወይም በስልክ ስለ ምን እንዳወሩ አያውቁም።
  • “ለምክር ቤቱ SESTA/FOSTA የተባሉትን አዋጆች እንዲያስቆም እንንገረው” የሚል ርዕስ ኢሜይል ከዲጂታል መብት አራማጆች ቡድን እንደደረስዎ እና በመቀጠል ወዲያውኑ ለህዝብ ተወካይ የምክር ቤት አባል እንደደወሉ ያውቃሉ። ነገር ግን የግንኙነትዎ ይዘት ከመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደተጠበቀ ይቆያል።
  • የማህጸን ስፔሻሊስት ጋር እንደደውሉና ለግማሽ ሰአት እንዳወሩ እና በመቀጠልም በአካባቢዎ የሚገኝ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ጋር እንደደወሉ ያውቃሉ። ነገር ግን ምን እንዳወሩ ማንም አያውቅም።

ሦስተኛ አካላት ስኬታማ በሆነ መንገድ ግንኙነቱን እንዲፈጽሙ ለማድረግ ዲበ ውሂብን ማግኘት ስለሚያስፈልጋቸው ዲበ ውሂብን ውጫዊ በሆነ አካል እንዳይሰበሰብ ለማድረግ ከቴክኒክ አንጻር አዳጋችነት አለው። የፖስታው የውጭ ክፍል በፖስታ ሠራተኛው መነበብ እንዳለበት ሁሉ የዲጂታል ግንኙነቶችም አብዛኛውን ጊዜ መነሻቸው እና መድረሻቸው መመልከት አለበት። የተንቀሳቃሽ ስልክ ኩባንያዎች የሚደረግልዎትን የስልክ ጥሪዎችን ለማስተላለፍ በደምሳሳው ያሉበትን ስፍራ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።

እንደ ቶር ያሉ አገልግሎቶች የተለመዱ የመስመር ላይ ግንኙነቶች የተነሳ የሚፈጠሩ የዲበ ውሂብዎችን መጠን ለመቀነስ ተስፋ በማድረግ ይሰራሉ። ከዲበ ውሂብ ጋር የተያያዙ ህግጋት እስኪሻሻሉ ድረስ እና ዲበ ውሂብን የሚቀንሱ መሳሪያዎች እስካልተስፋፉ ድረስ አንድ ግለሰብ ማድረግ የሚችለው በግንኙነት ወቅት ምን አይነት ዲበ ውሂብ እንደሚያስተላልፍ፣ ያንን መረጃ ማን እንደሚያገኘው እና እንዴት በጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በደንብ ማወቅ ነው።