Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የመስመር ላይ ሳንሱርን እንዴት ማለፍ እንደሚቻል

Last Reviewed: August 09, 2017

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

ይህ አጠር ያለ የመስመር ላይ ሳንሱር እንዴት እንደሚታለፍ የሚያሳይ መመሪያ ነው። ይሁንና መመሪያው ምሉዕ የሚባል አይደለም።

መንግስታት፣ ኩባንያዎች፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሰጪዎች ተጠቃሚዎች የተለያዩ ድረ ገጾችን እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን መጠቀም እንዳይችሉ ለማድረግ ሶፍትዌር ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ኢንተርኔትን ማገድ ማድረግ ወይም ማጥለል ተብሎ የሚጠራ አንዱ የሳንሱር ዓይነት ነው። ኢንተርኔን ማጥለል በተለያየ መንገድ ይደረጋል። አንዳንድ ጊዜ ድረ ገጹ ሙሉ በሙሉ ሲታገድ፣ ሌላ ጊዜ የድረ ገጹ የተወሰነ ገጽታዎች ወይም ይዘቶች ብቻ ይታገዳሉ። አልፎ አልፎ ደግሞ የተወሰኑ ቃላትን የያዙ ድረ ገጾች ብቻ ተመርጠው ሊታገዱ ይችላሉ።

የኢንተርኔት እገዳን ማለፍ የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ከስለላ ይጠብቅዎታል ነገር ግን ብዙዎቹ ያን አያደርጉም፡፡ የሆነ አካል የኢንተርኔት ግንኙነትዎን ሲቆጣጠር ወይም ድረ ገጽ ሲያግድ የሚፈልጉትን መረጃ ለማግኘት የቆረጣ መሣሪያዎችን መጠቀም እንደሚችሉ የታወቀ ነው፡፡ ማስታወሻ፣ ግለኝነትን ወይም ደኅንነት ለመጠበቅ ቃል የሚገቡ የቆረጣ መሣሪያዎች ሁሉም ግላዊ እና ደኀንነታቸው የተጠበቀ ነው ማለት ይከብዳል፡፡ “anonymizer” የመሳሰሉ ስሞች የያዙ መሣሪያዎች ሁልጊዜም ማንነትዎን ሙሉ በሙሉ ምስጢራዊ አድርገው ይይዛሉ ለማለት አይቻልም፡፡

ለእርስዎ ተገቢ የኾነው የቆረጣ መሣሪያ ደኀንነት በስጋትዎ ሞዴል ላይ የተመሠረተ ነው። የስጋት ሞዴልዎ ምን እንደኾነ እርግጠኛ ካልኾኑ ከዚህ መጀመር ይችላሉ።

በዚህ ጽሑፍ ሳንሱርን ቆርጠው ማለት ስለሚያስችሉ አራት መንገዶች እንነጋገራለን

  • የታገደ ድረ ገጽን ለማየት ተኪ ድረ ገጽ መጎብኘት
  • የታገደ ድረ ገጽን ለማየት የተመሰጠረ ተኪ ድረ ገጽን መጎብኘት
  • የታገደ ድረ ገጽን ለማየት ምናባዊ የግል ትይይዝት(ቪፒኤን) መጠቀም
  • የታገደ ድረ ገጽን ለማየት ወይም ማንነትን ለመደበቅ ቶር ብሮወዘርን መጠቀም

መሠረታዊ ስልቶች anchor link

የቆረጣ መሣሪያዎች በአብዛኛው የሚሠሩት ድርዎ የሚጠቀምበትን መስመር በመቀየር ሳንሱር የሚያደርገውን መኪና እገዳ ወይም ማጥለልን በማለፍ ነው፡፡ የኢንተርኔት ግንኑነትዎን እነዚህን እገዳዎች እንዲያልፍ የሚያደርገው አገልግሎት ተኪ ወይም በእንግሊዘኛው ፕሮክሲ ይባላል።

HTTPS የHTTP ለሚባለው የድረ ገጽ መዳሰሻ ስነስርዓት ደህንነቱ የተረጋገጠው ስሪት ነው። ይህም የተለያዩ ድረ ገጾችን ለመጎብኘት ያስችላል። አንዳንድ ጊዜ ሳንሱር የሚያከናውነው አካል ደህንነቱ ያልተረጋገጠን ወይም HTTP የኾነን ድረ ገጽ ብቻ ሊዘጉ ይችላሉ። ይህ በሚኾንበት ወቅት የድረ ገጹን አድራሻ በHTTPS እንዲጀምር አድርጎ በመቀየር በቀላሉ ድረ ገጹን መጎብኘት ይችላሉ።

ይህ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሚኾነው ያጋጠምዎት እቀባ አንዳንድ ቃላትን መሠረት በማድረግ ወይም የተወሰነ የድረ ገጽ ገጽታዎች ላይ የተደረገ እንደኾነ ብቻ ነው። HTTPS የሚባለው ስነስርዓት እቀባውን የሚጥለው አካል የድር ትራፊክዎን መከታተል እንዳይችሉ ሲያደርግ የትኞቹን ቃላትን እንደተጠቀሙ ወይም የትኛውን ነፍስ ወከፍ ድረ ገጽ እንደጎበኙ ማወቅ እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል፡፡

አሁንም ሳንሱር አድራጊዎች የጎብኛቸውን ድረ ገጽች የጋራ ስሞች በሙሉ ማየት ይችላሉ፡፡ እንደ ምሳሌ eff.org/https-everywhere” የሚለውን ከጎበኙ ሳንሱር አድራጊዎች “eff.org” ገጽን እንደጎበኙ ማየት ሲችሉ ነገር ግን “https-everywhere” የሚለውን ገጽ ማየትዎን መመልከት አይችሉም፡፡

ይህን ዓይነት ቀላል ክልከላ እንደተደረገ ከጠረጠሩ በድረ ገጹ ስም በፊት ያለውን http:// የሚለውን https:// ብለው በመተካት ይሞክሩ።

በEFF የተዘጋጀውን HTTPS በሁሉም ቦታ የሚለውን ተሰኪ በመጠቀም አገልግሎቱ በሚደግፉ ድረ ገጾች ላይ HTTPSን በቀጥታ ማስቻል ይቻላል።

ሌላው የተለያዩ መሠረታዊ እቀባዎችን ወይም የመስመር ላይ ሳንሱርዎችን ማለፍ የሚያስችልዎ መንገድ ሌሎች አማራጭ የጎራ ስምን ወይም URLን በመቀያየር መጠቀም ነው። ለምሳሌ ቲዊተር የተሰኘወን ድረ ገጽ ለመጎብኘት http://twitter.com በመጠቀም ፈንታ ለተንቀሳቃሽ ስልክ የተዘጋጀውንhttp://m.twitter.com የሚለውን ይጠቀሙ። የመስመር ላይ እቀባ አድራጊዎች እገዳውን የሚያከናውኑት እቀባ የጣሉባቸውን ድረ ገጾች ወይም ገጾችን ዝርዝር በጥቁር መዝገብ በመመዝገብ ሲኾን በጥቁር መዝገቡ ውስጥ የሌሉ ማናቸውንም ገጾች ማግኘት ይችላሉ። የአንዳንድ ድረ ገጾች ወይም ጦማሮች በተለይም ገጻቸው እንዳይነበብ ከዚህ በፊት የታገደባቸው እገዳውን ለመከላከል ሌላ አማራጭ የዶሜዬን ስም ያስመዘግባሉ። ስለዚህ ድረ ገጽ ዝርዝር ውስጥ የሌሉ የአማራጭ የዶሜዬን ስሞችን በመጠቀም እገዳውን ማለፍ ይቻላል።

በድር ላይ የተመሰረቱ የውከላ ዘዴዎች anchor link

ይህ በእንግሊዝኛው ዌብ ቤዝድ ፕሮክሲ በመባል ይታወቃል (ለምሳሌ http://proxy.org/)። ይህም ቀላል ኢንተርኔት ላይ የሚደረጉ እገዳዎችን ማለፍ የሚያስችል ድር ላይ የተመሠረተ የውከላ ስነስርዓት ነው። በድር ላይ የተመሠረተ ውከላን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚጠበቅብዎ የታገደውን ድረ ገጽ አድራሻ በድር ላይ በተመሠረተ የውከላ ስነስርዓት ላይ ማስገባት ሲኾን ወካዩ የታገደውን ይዘት ያሳይዎታል።

በድር ላይ የተመሠረተ ውከላ እጅግ በጣም ፈጣን እና ቀላል የኾነ የታገዱ ድረ ገጾችን የመጠቀሚያ ዘዴ ሲኾን ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ማንኛውንም ዓይነት ደህንነት የማይሰጥ እና የስጋት ሞዴልዎ የእርስዎ የኢንተርኔት ግንኙነት የሚከታተል አካል እንዳለ የሚጨምር ከኾነ ደካማ ምርጫ ነው። በተጨማሪም ሌሎች የታገዱ እና በድር ላይ ያልተመሠረቱ እንደ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ያሉትን ስርዓቶችን መጠቀም አያስችልም። በመጨረሻም የስጋት ሞዴልዎን መሠረት በማድረግ ወካዩ እርስዎ መስመር ላይ የሚያደርጉት ሙሉ መረጃ ቅጂ ስለሚኖረው ግላዊነትዎ ላይ የተጋረጠ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

የተመሰጠረ ውከላ anchor link

በርካታ የውከላ መሣሪያዎች ማጥለልን አልፎ ለመግባት ከማስቻላቸው በተጨማሪ የደኅንነት ገበር ለመፍጠር ምስጠራን ይጠቀማሉ፡፡ ግንኙነቱ ስለተመሰጠረ ሌሎች ምን እንደጎበኙ ማየት አይችሉም፡፡ የተመሰጠተሩ የውከላ ገጾች ካልተመሰጠሩ አገልግሎቶች ደኅንታቸው የተጠበቀ ቢሆንም መሣሪያውን ያቀረበው ስለእርስዎ መረጃ ሊኖረው ይችላል፡፡ ለምሳሌ ስምዎ እና የኢሜይል አድራሻዎ በመዝገባቸው ሊኖር ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት እነዚህ መሣሪያዎች ሙሉ ስምየለሽነትን አይሰጡም፡፡

ቀላሉ ዓይነት ሚስጥራዊ ድር ላይ የተመሰረተ ውከላ “https” በሚል የሚጀምር ሲኾን ይህም አብዛኛው ጊዜ ደህንነታቸው በተጠበቀ ድረ ገጾች የሚሰጥ ሚስጥራዊነትን የሚጠቀም ነው። ይኹንና የዚህ ውከላ መሣሪያ ባለቤቶች የሚልኩትን እና ከሌሎች ደኅንነታቸው ከተረጋገጠ ድረ ገጾች የሚቀበሉትን ውሂብ ማየት ስለሚችሉ ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልግዎታል። አልትራሰርፍ እና ሳይፈን የእነዚህ መሣሪያዎች ምሳሌ ናቸው።

ምናባዊ የግል ኔትዎርክ ወይም VPN anchor link

ምናባዊ የግል ኔትዎርክ ወይም VPN በኮምፒውተርዎ እና በሌላ ኮምፒውተር የሚደረገውን የበይነ መረብ የውሂብ ልውውጥ አመስጥሮ የሚልክ ነው። ይህ VPN የንግድ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ ሃሳባዊ የግል ኔትዎርክ አገልግሎት፣ የኩባንያዎ ወይም የታማኝ ወዳጆ ሊኾን ይችላል። የVPN አገልግሎት አንዴ በትክክለኛ መንገድ ኮምፒውተርዎ ላይ ከተዋቀረ የተለያዩ ድረ ገጾችን ለመጎብኘት፣ ለኢሜል፣ ለፈጣን የመልዕክት አገልግሎት፣ IPን ተጠቅሞ ለሚደረግ የድምጽ ግንኙነት አገልግሎት (VoIP) እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት ሊጠቀሙበት ይችላሉ። የግል ሚስጥራዊ ኔትዎርክ ወይም VPN ትራፊክዎ በሌላ በሦስተኛ ወገን እንዳይሰለል ቢከላከልም፤ የVPN አገልግሎት ሰጪው የትራፊክዎ መረጃ (የጎበኛቸውን የድረ ገጾች እና መቼ እንደጎበኛቸው የሚያሳይ) ማስቀመጥ ወይም የሚያደርጉትን የድር ዳሰሳ ሶስተኛ አካል በቀጥታ መሰለል እንዲችል ሊያደርጉ ግን ይችላሉ። የስጋት ሞዴልዎን መሠረት በማድረግ የተለያዩ የመንግስት አካላት በVPN የሚያደርጉትን ግንኙነቶች መስማታቸው ወይም የግንኙነትዎን ዝርዝር ማግኘታቸው ከባድ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ሲኾን ለአንዳንድ የVPN ተጠቃሚዎች ግን ከሚያስከትለው ጉዳት ይልቅ VPNን ለጥቂት ጊዜ በመጠቀማቸው የሚያገኙት ጥቅም በልጦ ሊገኝ ይችላል።

ምናባዊ የግል ኔትዎርክን ወይም የVPN አገልግሎትን በተመለከተ ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ጠቅ ያድርጉ።

እኛ በኢኤፍኤፍ ያለን ሰዎች ስለቪፒኤኖች ደረጃ ማረጋገጫ መስጠት አንችልም፡፡ አንዳንድ እንደ አርአያ ሊጠቀስ የሚችል የግላዊነት ፖሊሲ ያላቸው የVPN አገልግሎቶች በአታላዮች የሚመሩ ሊኾኑ ይችላሉ። የማያምኑትን የVPN አገልግሎት አይጠቀሙ።

ቶር anchor link

ቶር በድር ላይ ማንነትዎ እንዳይታወቅ እንዲያደርግ ታስቦ የተሠራ ክፍት ምንጭ ሶፍትዌር ነው፡፡ ቶር ማሰሻ በቶር አኖኒሚቲ ኔትዎርክ የበላይነት የተሰራ የድር ማሰሻ ነው፡፡ ቶር ድር አሰሳዎን ሰብሮ ስለሚገባ ሳንሱርን ማለፍ ያስችሎታል፡፡ (ለሊነክስማክ ኦኤስ እና ዊንዶውስ ያዘጋጀናቸውን የቶር አጠቃቀም መመሪያዎችቻንን  ይመልከቱ)፡፡

ቶር ማሰሻን ሲከፍቱ ሳንሱር በሚደረግ ትይይዝት ላይ እንዳሉ ለይተው አማራጩን መምረጥ ይችላሉ:

ቶር ማንኛውም ዓይነት ብሔራዊ የመንግሥት እቀባን ማለፍ ብቻ አይደለም በስርዓት ከተሰናዳ ማንነትዎን በሀገርዎ ትይይዝት ከሚመጣ አደገኛ ስላላ ይጠብቅሎታል፡፡ነገር ግን እጅግ በጣም ዘገምተኛ እና ለአጠቃቀም ከባድ ሊኾን ይችላል። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ እጅግ ቀርፋፋ የኔትወርክ አገልግሎት ባላቸው አገራት ቶርን መጠቀም በጣም ከባድ ነው።

በዴስክቶፕ የቶርን አጠቃቀም ለማወቅ ለሊነክስ እዚህ ይጫኑ፣ ለማክ ኦኤስ እዚህ ይጫኑ፣ ለዊንዶወስ እዚህ ይጫኑ፤  ነገር ግን ከላይ በታየው ሰሌዳ ላይ በ“Connect” ፈንታ “Configure” የሚለውን መንካትዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡