ለማክ OS X የቶር አጠቃቀም

ይህ መመሪያ በOS X ላይ ቶር ብራውዘር በንድልን እንዴት እንደሚጠቀሙ ይዘረዝራል።

ቶር ምንድን ነው? Anchor link

ቶር መስመር ላይ ማን እንደኾኑ እና የት ኾነው ግንኙነት እንደሚያደርጉ ከለላ በመስጠት ድብቅነትን እና ግላዊነትን የሚሰጥ በበጎ ፈቃደኞች የሚሰጥ አገልግሎት ነው። ይህ አገልግሎት ከራሱ ከቶር ጭምር ይከላከላል።

አንዳንድ ድረ ገጾችን በሚዳስሱበት ወቅት አልፎ አልፎ ድብቅነትን እና ግለኝነትን መጠበቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የቶር ብራውዘር ፈጣን እና ቀላል የቶር አውታረ መረብን መጠቀሚያ ዘዴ ነው።

የቶር ብራውዘር በንድል የቶር አውታረ መረብን መጠቀሚያ ቀላሉ መንገድ ሲኾን ይህም የድር ማሰሻን፣ ቶር ሶፍትዌርን እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ድርን ለማሰስ የሚረዱ ሌሎች ጠቃሚ ሶፍትዌሮችን በአንድነት የያዘ ነው።

የቶር ብራውዘር ግንኙነትዎን በቶር ኔትወርክ አማካኝነት ከማድረጉ በስተቀር የሚሰራው ከሌሎች የድር ማሰሻዎች ጋር በተመሳሳይ መልኩ ነው። ይህም እርስዎን የሚቆጣጠሩ ሰዎች መስመር ላይ ምን እየሰሩ እንደሆነ ማወቅን እና እየተጠቀሙት ያለውን ድረ ገጽ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ከየት ሆነው ድረ ገጹን እየተጠቀሙ እንዳለ ማወቅን ከባድ ያደርግባቸዋል። በቶር ብራውዘር ውስጥ ገብተው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብቻ ድብቅ እንደሚሆን ይወቁ። የቶር ብራውዘር በኮምፒውተርዎ ላይ ተጫነ ማለት በተመሳሳይ ኮምፒውተር ሌላ ሶፍትዌሮችን (ለምሳሌ መደበኛ የድር መዳሰሻዎን) በመጠቀም የሚሠሯቸውን ሥራዎች ድብቅ አያደርግም።

የቶር ብራውዘር በንድልን ማግኘት Anchor link

እንደ ሞዚላ ፋየርፎክስ ወይም ሳፋሪ ያሉ የድር ማሰሻን ይክፈቱ እና በURL አሞሌው ላይ https://www.torproject.org/download/download-easy.html.en ይህንን ይጻፉ። የቶር ብራውዘር በንድልን ለመፈለግ የፍለጋ ፕሮግራሙን የሚጠቀሙ ከኾነ የጻፉት URL ትክክል መኾኑን ያረጋግጡ።

የቶር ብራውዘር በንድል የመጫኛ ፕሮግራሙን ለማግኘት ዳውንሎድ የሚለውን ትልቅ ሃምራዊው አዝራርን ጠቅ ያድርጉ።

ድረ ገጹ በኮምፒውተርዎ ላይ የተጫነውን ስርዓተ ክወና ያጣራ እና ለOS X ትክክለኛ የኾነውን ፋይል ያወርድልዎታል። ይህን ማድረግ ካልቻለ ትክክለኛውን ስሪት ለማውረድ ከሐምራዊው አዝራር ጎን ያለውን አገናኝ ጠቅ ማድረግ ይችላሉ።

ሳፋሪን የሚጠቀሙ ከኾነ የቶር ብራውዘር በንድል መውረድ ይጀምራል። በፋየርፎክስ ደግሞ ሰነዱን መክፈት ወይም ማስቀመጥ እንደሚፈልጉ ይጠየቃሉ። ሁልጊዜ ሰነዱን ማስቀመጥ ጥሩ አማራጭ ነው ስለዚህ “ሴቭ” የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህ ምሳሌ ይህን መመሪያ በጻፍንበት ወቅት የመጨረሻ ስሪት የነበረውን ቶር ብራውዘር በንድል 4.0.8 በመጠቀም የተዘጋጀ ነው። ይህን በሚያነቡበት ወቅት ከዚህ የቀረበ አዲስ ብጅት ለማውረድ ተዘጋጅቶ ሊያገኙ ይችላሉ።

ቶር ብራውዘር በንድልን መጫን Anchor link

ቶርን አውርዶ ከጨረሰ በኋላ ፋይሉ የወረደበትን ማህደር መክፈት የሚያስችል ምርጫ ሊያገኙ ይችላሉ። በነባሪ የሚወርድብት ሥፍራ የማውረጃ ማኅደሩ ነው። Torbrowser-4.0.8-osx32_en-US.dmg የሚለው ፋይል ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ።

የቶር ብራውዘር በንድልን ጎትተው አፕሊኬሽን አቃፊ ውስጥ በማስገበት እንዲጭኑት የሚጠይቅ መስኮት ይከፈታል። ይህንንም አሁን ያድርጉ።

           

የቶር ብራውዘር በአፕሊኬሽን አቃፊዎ ውስጥ አሁን ተጭኗል።

ቶር ብራውዘር በንድልን መጠቀም Anchor link

የቶር ብራውዘርን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመክፈት በመፈለጊያው ወይም በአዲሱ የOS X ብጅት በላውንችፓድ ላይ ፈልገው ያግኙት።

በቶር ብራውዘር አዶው ላይ ጠቅ ካደረጉ በኋላ ስለ ሶፍትዌሩ ስረ ነገር የሚያስጠነቅቅ መልዕክት የያዘ መስኮት ይከፈታል። ሁልጊዜም እንዲህ ዓይነቱን ማስጠንቀቂያ የምር መውሰድ እና መጫን የፈለጉትን ሶፍትዌር እንደሚያምኑት እና እውነተኛ ቅጂውን ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነትን በመጠቀም ከኦፊሴላዊ ድረ ገጹ ላይ እንዳገኙት ማረጋገጥ ይገባዎታል። የሚፈልጉት ምን እንደኾነ፣ ሶፍትዌሩን የት እንደሚያገኝ ስለሚያውቁ እና ዳውንሎድ ያደረጉት ደህንነቱ ከተጠበቀ የቶር ፕሮጀክትስ HTTPS ድረገጽ ላይ እስከኾነ ድረስ ኦፕን የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

የቶር ብራውዘርን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያስጀምሩት አስፈላጊ ከኾነ አንዳንድ መዋቅሮችን መቀየር የሚያስችልዎ መስኮት ይመጣልዎታል። አንዳንድ መዋቅሮችን መልሰው መቀየር ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለአሁን ግን ይቀጥሉ እና ኮኔክት የሚለውን አዝራር ጠቅ በማድረግ ከቶር አውታረ መረብ ጋር ይገናኙ።

ኮኔክት የሚለውን አዝራር ጠቅ ካደረጉ በኋላ እንደ ቶር ሶፍትዌር የአጀማመር ሂደት መጠን አብሮ እያደገ የሚሄድ አራንጓዴ አሞሌ ያለው አዲስ መስኮት ይከፈታል።

የቶር ብራውዘር ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ ሲውል ከተለመደው ትንሽ ሊዘገይ ይችላል። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ቶር ብራውዘር መክፈቱን ይጨርስ እና እንኳን ደስ አለዎት የሚል የቶር ድር መዳሰሻ ይከፈትልዎታል።

ከቶር አውታረ መረብ ጋር መገናኘትዎን check.torproject.org የሚለውን ድረ ገጽ በመጎብኘት ማረጋገጥ ይችላሉ። በትክክል የተገናኙ ከኾነ ድረ ገጹ “ኮንግራጁሌሽን ዚስ ብራውዘር ኢዝ ኮንፊገርድ ቱ ዩዝ ቶር” ይላል።

ቶርን ተጠቅሞ መዳሰስ ከመደበኛው የዳሰሳ ልምድ በአንዳንድ መንገዶች የተለየ ነው። በቶር ትክክለኛ ዳሰሳን እንዲያደርጉ እና ድብቅነትዎን ጠብቀው እንዲቆዩ እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች እንዲያነቡ  እናሳስባለን።

አሁን በይነ መረብን በቶር ተደብቀው ለመዳሰስ ዝግጁ ኖዎት።

 

Last reviewed: 
2017-09-05
This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.
JavaScript license information