ቀዳሚ የበይነ መረብ ደህንነት ጥራዝ
ቀላል ቅደም ተከተሎችን በመምረጥ ይጀምሩ።
በየትኛውም ሥፍራ ብንኖርም ኾነ የትኛውንም ዓይነት ሥራ ብንሠራ ከመስመር ላይ ስለላ ተጽዕኖ አናመልጥም። አንዳንዶች በቀጥታ ተጽዕኖ ውስጥ ሲወድቁ ሌሎች ደግሞ ቀላል እርምጃዎችን በመውሰድ የመስመር ላይ ግንኙነታቸውን እና መረጃዎቻቸውን ከስለላ እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ማወቅ ይፈልጋሉ። ይህ መግቢያ የዲጂታል ዝርዝር የአደጋ ተጋላጭነትዎን እንዴት እንደሚገመግሙ፣ የመስመር ላይ ግንኙነትዎን እና መረጃዎን ምስጢራዊነት እንዴት እንደሚጠብቁ እንዲሁም ግላዊነትን/ብሕትውነት (ፕራይቬሲ) የሚጨምሩ አጋዥ መሳሪያዎችን በዕለት ተዕለት ሕይወትዎ እንዴት ማካተት እንደሚችሉ ለማሰላሰል በሩን ይከፍትልዎታል።