የዋትስአፕ አጠቃቀም በአይኦኤስ
Last Reviewed: May 09, 2018
የዋትስአፕ ግንኙትዎን ደኅንነት የበለጠ እንዲጠበቅ ከዚህ በታች እንደተገለጸው ቅንብሮችዎን እንዲቀይሩ(እንዲሁም እውቂያዎችዎ ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ እንዲጠይቁ!) አጥብቀን እናበረታታለን፡፡
ካሁን በኋላም ዋትስአፕን መጠቀም ከወደዱ ከዚህ በታች ያለውን የአጠቃቀም መመሪያ ይመልከቱ፡፡ ስለዚህም ምትክ ፋይል ማስቀመጫን ያጥፉ፤ ጣት አሻራ ለውጥ ማሳወቂያዎችም እንዲደርስዎት ያድርጉ(ተጨማሪ የደኅንነት ጥንቃቄዎች ቅንበር ክፍልን ይመልከቱ)፡፡
የማውረጃ ስፍራ: ከመተግበሪያ ግምጃ መተግበሪያውን ማውረድ ይቻላል
አስፈላጊ ቅድመ ኹኔታዎች: አይኦኤስ 6 ወይም ከዚያ በላይ፣ በዚህ ጊዜ አይፖድ እና አይፓድ መገልገያዎች አገልግሎት አይሰጡም፡፡
በዚህ መርጃ ጽሑፍ የተጠቀምነው ዝርያ: 2.16.2
ፈቃድ: ንብረትነቱ
ተጨማሪ ንባብ:
-
https://www.whatsapp.com/security/WhatsApp-Security-Whitepaper.pdf
-
https://medium.com/@thegrugq/operational-whatsapp-on-ios-ce9a4231a034/
ደረጃ: ጀማሪ-መካከለኛ
የሚወስደው ጊዜ: ከ15-20 ደቂቃ
ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ ግንኙነት እንዲያደርጉ የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡ ተጠቃሚዎች ይህንን ተጠቅመው ደህንነታቸው ተጠብቆ መደዋወል እና መጻጻፍ እንዲችሉ፣ ሰነድ እንዲላላኩ እና በቡድን ውይይት እንዲሳተፉ ያስችላል፡፡ ምንም እንኳን ዋትስአፕ የስልክ ቁጥሮችን እንደ እውቂያዎች ቢጠቀምም ስልኮች የሚደወሉት እና መልዕክቶች የሚላኩት የውሂብ ግንኙነት በመጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም በንግግሩ የሚሳተፉ አካላት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡በዚህ ምክንያት የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ለዚህ አይነት ንግግሮች፣ የአጭር የጽሑፍ መልዕክቶች እና የህብር ሚዲያ መልዕክቶች ክፍያዎች አይጠየቁም፡፡
ዋትስአፕ ንብረትነቱ የፌስቡክ ነው፡፡ መተግበሪያው ራሱ ምንጨ-ዝግ ሶፍትዌር ነው፡፡ ያ ማለት ውጭ ለሚገኝ ባለሙያ ኩባንያው ምስጠራውን ደኅንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማድረጉን ማረጋገጥ እጅግ አስቸጋሪ ነው ማለት ነው፡፡ ይሁንና ዋትስአፕ የተመሰጠሩ መልዕክቶችን ለመላክ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ለህዝብ ግልጽ የሆነ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
በአይፎን ስልክዎ ዋትስአፕ መጫን anchor link
ቅደም ተከተል 1: ዋትስአፕን በማውረድ ስልክዎ ላይ መጫን anchor link
ቅደም ተከተል 2: ስልክ ቁጥርዎን ያስመዝግቡ እና ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ anchor link
ዋትስአፕ በእርስዎ ስልክ የተመዘገቡ ወዳጆችዎን መረጃ ለማግኘት ይጠይቃል፡፡ እርስዎ ይህንን ከፈቀዱ ዋትስአፕ የእውቂያዎችዎን ዝርዝር በሙሉ ይወስዳል፡፡ ካልፈቀዱ ደግሞ ወዳጅዎችዎን አንድ ባንድ በማስገባት በጽሑፍ መወያየት ይችላሉ ነገር ግን ዋትስአፕ የወዳጆችዎን ዝርዘር እንዲያገኝ ሳይፈቅዱ አዲስ ጥሪ ማድረግ አይችሉም፡፡ ፎቶዎችን፣ የሚዲያ ውጤቶችን ወይም ሰነዶችንም መላክ ከፈለጉ ዋትስአፕ እነዚህን ፋይሎች ለማግኘት ፍቃድ ይጠይቃል፡፡
የዋትስአፕ አጠቃቀም anchor link
ለሌላኛው ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ማረጋገጫ መንገድ ቁጥሮቹን ፎቶ በመንሳት በሌላ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደ ባለ መንገድ ማጋራት ነው፡፡
ተጨማሪ የደኅንነት ቅንብሮች anchor link
የደኅንነት ማሳወቂያዎችን አሳይ anchor link
ከላይ እንደተገለጸው በማንኛውም ምክንያት የወዳጅዎችዎ የምስጠራ ቁልፍ ሲለወጥ ስለዚህ ለውጥ ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል፡፡
አይክላውድ ምትክ ሰነድ anchor link
በተጨማሪም ከላይ እንደተገለጸው ምናልባትም ያልተመሰጠሩ ምትክ ሰነዶች ወደ አፕል አለመላካቸውን እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ፡፡
ክላውድ ምትክ ሰነድ አለማስቀመጡን እርግጠኛ ለመሆን ቅንበር ወስጥ Settings → Chats → Chat Backup ብለው ይፈልጉ፡፡ "Auto Backup" በሚለው ስር "Off"ን ይምረጡ: