Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የዋትስአፕ አጠቃቀም በአይኦኤስ

Last Reviewed: May 09, 2018

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

የዋትስአፕ ግንኙትዎን ደኅንነት የበለጠ እንዲጠበቅ  ከዚህ በታች እንደተገለጸው ቅንብሮችዎን እንዲቀይሩ(እንዲሁም እውቂያዎችዎ ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ እንዲጠይቁ!) አጥብቀን እናበረታታለን፡፡

በተለይ በነሐሴ 2008 ዓ.ም. ይፋ የተደረገው ለእናት ድርጅቱ ፌስቡክ መረጃ ማጋራትን የሚፈቅደው አዲሱ የግለኝነት ፖሊሲው ያሳስበናል፡፡ ይህ ፌስቡክን በርካታ የተጠቃሚዎችን መረጃ የዋትስአፕ ስልክ ቁጥር እና ዋትስአፕ በመጠቀም ሂደት ያከማቸውን መረጃ ጨምሮ እንዲያገኝ ይፈቅዳል፡፡
 
ቀድመው ዋትስአፕን መጠቀም ለጀመሩ ተጠቃሚዎች የግለኝነት ፖሊሲው ፌስቡክ ከዋትስአፕ ባገኘው መረጃ መሠረት ጓደኛ እንዳይጠቁም ወይም የማስታወቂያ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚከልክል ቅንብር የሚያደራጁበት ጊዜ ይሰጣል፡፡ አዲስ ተጠቃሚዎች ግን እንዲዚህ አይነቱን የተለጠጠ የራሳቸውመረጃ ካለፈቃዳቸው መጠቀምን አንፈልግም የሚሉበት ዕድል የላቸውም፡፡ ለአዲስ ተጠቃሚ ያለው ብቸኛ አማራጭ የመረጃ ማጋራትን በሚፈቅደው አዲሱ የግለኝነት ፖሊስ ስር ዋትስአፕን መቀላቀል ነው፡፡ ምንም እንኳን ኩባንያው መረጃውን በቀጥታ ለማስታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንደማያጋራ ቢገልጽም ይህ ሂደት ግን በግልጽ አስጊ ነው፡፡ ስጋት ለተጠቃሚዎች የዋትስአፕ መረጃቸው እንዴት እንደሚጋራ እና ጥቅም ላይ እንደሚውል፡፡
 
በተጨማሪ የሚያሳስበን የዋትስአፕ ድር መተግበሪያ ነው፡፡ ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች መልዕክቶች መላክ እና መቀበል የሚስችል HTTPS ደኅንነቱ የተጠበቀ የድር በይነገጽ አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ነገር ግን በሁሉም ድረገጾች እንደተለመደው መተግበሪያውን ለመጫን የሚያስፈልጉ ነገሮች ገጹን በጎበኙ ቁጥር ይወርዳሉ፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ድረገጹ የምስጠራ ድጋፍ ቢኖረውም በማንኛውም የገጽ ጭነት የመካነ ድሩ መተግበሪያ በቀላሉ ወደ ጎጂነት ያለው የመተግበሪያ አይነት ይቀየራል፤ ይህም ሁሉንም መልዕክቶች ወደ ሦስተኛ አካል ለማቅረብ ያስችለዋል፡፡
 
ዋትስአፕ በመጀመሪያ ላኪው መልዕክቱን ወደሚስጥራዊ መልዕክት የሚቀየርበት፣ በመጨረሻ በተቀባዩ ብቻ የሚፈታ፣ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አገልግሎት እስካሁን ይሰጣል፡፡ ይህ ምስጠራ በሚካሄድበት መንገድ ላይ ምንም የምንለው የለንም፡፡ የሚጠቀመው የምስጠራ ፕሮቶኮል፣ ሲግናል ፕሮቶኮል ወደፊት የበለጠ ይስፋፋል ብንል ተስፋ እናደርጋለን፡፡.ነገር ግን የሲግናል ፕሮቶኮል ምርጥ ጥረት እንዳለ ሆኖ የዋትስአፕ ደኅንነት ግን ያሳስበናል፡፡

ካሁን በኋላም ዋትስአፕን መጠቀም ከወደዱ ከዚህ በታች ያለውን የአጠቃቀም መመሪያ ይመልከቱ፡፡ ስለዚህም ምትክ ፋይል ማስቀመጫን ያጥፉ፤ ጣት አሻራ ለውጥ ማሳወቂያዎችም እንዲደርስዎት ያድርጉ(ተጨማሪ የደኅንነት ጥንቃቄዎች ቅንበር ክፍልን ይመልከቱ)፡፡

የማውረጃ ስፍራ: ከመተግበሪያ ግምጃ መተግበሪያውን ማውረድ ይቻላል

አስፈላጊ ቅድመ ኹኔታዎች: አይኦኤስ 6 ወይም ከዚያ በላይ፣ በዚህ ጊዜ አይፖድ እና አይፓድ መገልገያዎች አገልግሎት አይሰጡም፡፡

በዚህ መርጃ ጽሑፍ የተጠቀምነው ዝርያ: 2.16.2

ፈቃድ: ንብረትነቱ

ተጨማሪ ንባብ:

ደረጃ: ጀማሪ-መካከለኛ

የሚወስደው ጊዜ: ከ15-20 ደቂቃ

ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ ግንኙነት እንዲያደርጉ የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡ ተጠቃሚዎች ይህንን ተጠቅመው ደህንነታቸው ተጠብቆ መደዋወል እና መጻጻፍ እንዲችሉ፣ ሰነድ እንዲላላኩ እና በቡድን ውይይት እንዲሳተፉ ያስችላል፡፡ ምንም እንኳን ዋትስአፕ የስልክ ቁጥሮችን እንደ እውቂያዎች ቢጠቀምም ስልኮች የሚደወሉት እና መልዕክቶች የሚላኩት የውሂብ ግንኙነት በመጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም በንግግሩ የሚሳተፉ አካላት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡በዚህ ምክንያት የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ለዚህ አይነት ንግግሮች፣ የአጭር የጽሑፍ መልዕክቶች እና የህብር ሚዲያ መልዕክቶች ክፍያዎች አይጠየቁም፡፡

ዋትስአፕ ንብረትነቱ የፌስቡክ ነው፡፡ መተግበሪያው ራሱ ምንጨ-ዝግ ሶፍትዌር ነው፡፡ ያ ማለት ውጭ ለሚገኝ ባለሙያ ኩባንያው ምስጠራውን ደኅንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማድረጉን ማረጋገጥ እጅግ አስቸጋሪ ነው ማለት ነው፡፡ ይሁንና ዋትስአፕ የተመሰጠሩ መልዕክቶችን ለመላክ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ለህዝብ ግልጽ የሆነ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

በአይፎን ስልክዎ ዋትስአፕ መጫን anchor link

ቅደም ተከተል 1: ዋትስአፕን በማውረድ ስልክዎ ላይ መጫን anchor link

በአይ ኦ ኤስ መገልገያዎ ወደ አፕ ስቶር በመግባት “ዋትስአፕ”ን ይፈልጉ፡፡ ዋትስአፕ ሜሰንጀር በዋትስአፕ አይኤንሲ መተግበሪያ ቀጥሎ ያለውን "GET" የሚለውን ከዚያም "INSTALL."ን ይንኩ፡፡
ዋትስአፕ ወርዶ ከጨረሰ በኋላ መተግበሪያውን ለማሰጀመር “OPEN” የሚለውን ይጫኑ፡፡

ቅደም ተከተል 2: ስልክ ቁጥርዎን ያስመዝግቡ እና ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ anchor link

ዋትስአፕ በእርስዎ ስልክ የተመዘገቡ ወዳጆችዎን መረጃ ለማግኘት ይጠይቃል፡፡ እርስዎ ይህንን ከፈቀዱ ዋትስአፕ የእውቂያዎችዎን ዝርዝር በሙሉ ይወስዳል፡፡ ካልፈቀዱ ደግሞ ወዳጅዎችዎን አንድ ባንድ በማስገባት በጽሑፍ መወያየት ይችላሉ ነገር ግን ዋትስአፕ የወዳጆችዎን ዝርዘር እንዲያገኝ ሳይፈቅዱ አዲስ ጥሪ ማድረግ አይችሉም፡፡ ፎቶዎችን፣ የሚዲያ ውጤቶችን ወይም ሰነዶችንም መላክ ከፈለጉ ዋትስአፕ እነዚህን ፋይሎች ለማግኘት ፍቃድ ይጠይቃል፡፡

ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው መፍቀድ ከፈለጉ "Continue,"ከዚያም "Allow" የሚለውን ይንኩ

በመቀጠል ዋትስአፕ ማሳወቂያዎችን ለመላክ ፍቃድ ይጠይቃል፡፡ አዲስ መልዕክት ሲመጣ ማሰወቂያ እንዲደርስዎ ከፈለጉ "OK" የሚለውን ይንኩ፡፡

በመጀመሪያ የዋትስአፕን የአገልግሎት ውል እና የግለኝነት ፖሊሲ መቀበል ይኖርብዎታል፡፡

"Agree & Continue." የሚለውን ይጫኑ፡፡ ይህንን የሚመስል ሠሌዳ ያገኛሉ:

የተንቀሳቃሽ ስልክዎን ቁጥር ያስገቡና "Done." የሚለውን ይንኩ፡፡ ቀጥለው የማረጋገጫ መልዕክት ይመለከታሉ:

የስልክ ቁጥርዎን ለማረጋገጥ "Yes." የሚለውን ይንኩ፤ ስድስት አሃዝ ያለው ኮድ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ይቀበላሉ፡፡ ይህንን በሚመስለው ሠሌዳ ላይ ያስገቡት:

የዋትስአፕ አጠቃቀም anchor link

ዋትስአፕን ለመጠቀም መልዕክት የሚልኩለት ወይም የሚደውሉለት ሰው ዋትስአፕ መተግበሪያን እንደእርስዎ በስልኩ ላይ መጫን አለበት፡፡
 
አዲስ የተመሰጠረ ንግግር ሲጀመር የሚከተለውን ማሳወቂያ ይመለከታሉ: "Messages you send to this chat and calls are now secured with end-to-end encryption. Tap for more info." በዚህ ጊዜ መተግበሪያው ሲወርድ ( ቁልፍ ማረጋገጫ የተባለ ሂደት) እንዳልተቀየጠ ወይም ከሌላ ሰው ቁልፍ ጋር እንዳልተቀያየረ በመረዳት እየተነጋገሩት ያለው ሰው በትክክል ራሱ መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ማረጋገጫው እየተነጋገሩ ያለው ሰው በአካል ሲኖር የሚደረግ የማረጋገጥ ሂደት ነው፡፡ ለማረጋገጥ፣ ከላይ የሚገኘውን የወዳጅዎን ስም[1] መጫን በመቀጠል ተከትሎ በሚመጣው ሠሌዳ ላይ የሚገኘውን ሰማያዊ ቁልፍ ምልክት [2] መጫን:

ወዳጅዎም በስልካቸው በተመሳሳይ ተመሳሳይ ሂደት ሲከተሉ የሚከተለውን ሠሌዳ ይመለከታሉ "Verify security code"፡፡
የስልሳ አሃዞች ቅጥልጥል ይመለከታሉ፡፡ እነዚህን ቁጥሮች አንድ በአንድ በመናበብ እና ከወዳጅዎ ቁጥሮች ጋር በተጓዳኝ በማስተያየት ወይም በዚህ ሠሌዳ ላይ ያለውን ኪው አር ኮድ በመቅረጽ ማረጋገጥ ይችላሉ ፡፡

ለሌላኛው ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ማረጋገጫ መንገድ ቁጥሮቹን ፎቶ በመንሳት በሌላ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደ ባለ መንገድ ማጋራት ነው፡፡

አንዴ እንደዚህ ካደረጉ በኋላ ከዚህ ወዳጅዎ ጋር የሚያርጉት የተመሰጠረ ግንኙነት የሚታየው በእርስዎ እና በወዳጅዎ ብቻ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡ ይህ ለዋትስአፕ የጽሑፍ መልዕክቶች እና ለዋትስአፕ የድምጽ ደውሎች ለሁለቱም ይሰራል፡፡

ተጨማሪ የደኅንነት ቅንብሮች anchor link

የደኅንነት ማሳወቂያዎችን አሳይ anchor link

ከላይ እንደተገለጸው በማንኛውም ምክንያት የወዳጅዎችዎ የምስጠራ ቁልፍ ሲለወጥ ስለዚህ ለውጥ ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል፡፡

በመደበኛነት የቁልፍ መለዋወጥ እንደችግር የሚታይ አይደለም፤ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተው መተግበሪያው እንደገና ሲጫን ወይም የስልኮች መቀያየር ሲኖር ነው፡፡ ነው፡፡ ነገር ግን በመሃከል ያለ ሦስተኛ ሰው በተንኮል ቁልፍ ሊቀይር የሚችልበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ በዚህ ምክንያት የወዳጅዎችዎ ቁልፍ ሲቀየር እንደገና ማረጋገጥ (ከላይ እንደተገለጸው) ጥሩ ልምድ ነው፡፡ በዋናነት ዋትስአፕ የዕውቂያዎች ቁልፍ ለውጥ ሲኖር አያሳይም፡፡ ይህንን ለማስጀመር ወደ ቀንብር ይግቡና ይህንን ሂደት ይከተሉ Settings → Account → Security እና 'Show security notifications' የሚለውን ወደቀኝ ያንሸራትቱ:

አይክላውድ ምትክ ሰነድ anchor link

በተጨማሪም ከላይ እንደተገለጸው ምናልባትም ያልተመሰጠሩ ምትክ ሰነዶች ወደ አፕል አለመላካቸውን እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ፡፡

ክላውድ ምትክ ሰነድ አለማስቀመጡን እርግጠኛ ለመሆን ቅንበር ወስጥ Settings → Chats → Chat Backup ብለው ይፈልጉ፡፡ "Auto Backup" በሚለው ስር "Off"ን ይምረጡ: