Surveillance
Self-Defense

አይፎንዎን ማመስጠር

አይፎን 3GS ወይም ከዛ በላይ፣ አይፓድ ተች 3rd ሊኒክስ ion ወይም ከዛ በላይ፣ ወይም ማንኛውም አይፓድ ካለዎት ምስጠራን በመጠቀም የመሣሪያዎትን ይዘት ከአደጋ መከላከል ይችላሉ። ይህም ማለት አንድ ሰው የመሣሪያዎትን ቁሳዊ ይዞታ ማግኘት ቢችል እንኳ በውስጡ የተጠራቀመውን ውሂብ ማለትም ዕውቂያዎችዎን፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክትዎትን ወይም ጽሐፍዎችዎን፣ የስልክ ጥሪ ምዝገባዎችዎን እና ኢሜልዎችዎን ለመፍታት የማለፊያ ኮዶ ያስፈልገዋል ማለት ነው።

በእውነቱ ከኾነ አብዛኛዎቹ ዘመናዊ የአፕል መሣሪያዎች በተለያየ የደህንነት ደረጃ በነባሪው ይዘታቸው መመስጠር ይችላሉ። ነገር ግን አንድ ሰው መሣሪያዎትን በመስረቅ ከሚያደርገው የውሂብ ስርቆት ራስዎን ለመከላከል ይህን ምስጠራ እርስዎ ብቻ በሚያውቁት የማለፊያ ሐረግ ወይም ኮድ መዝጋት ያስፈልግዎታል።

ከiOS 4 እስከ iOS 7 በተጫነባቸው መሳሪያዎች አጠቃላይ መዋቅር ውስጥ በመሄድ እና ፓስኮድ (ወይም አይተች &አምፕ እና ፓስኮድ) የሚለውን በመምረጥ ይህንን ማድረግ ይችላሉ። ለiOS 8 ደግሞ በሴቲንግ መተግበሪያ ውስጥ ፓስኮድ የራሱ የኾነ ክፍል አለው። የማለፊያ ኮዱን ለመፍጠር የሚያመጣልዎትን ይከተሉ። መሣሪያውን በማይጠቀሙበት ወቅት ሳይዘጋ እንዳይቀር “ሪኳየር ፓስኮድ” የሚለውን ምርጫ “ኢሚዲየትሊ” በሚለው መዋቅር መቀየር አለብዎት። ከ4 አሃዞች በላይ የኾነ ኮድ መጠቀም እንዲችሉ “ሲምፒል ፓስኮድ” የሚለውን አማራጭ ማቦዘን አለብዎት።

ሁሉም ቁጥር የኾነ የማለፊያ ኮድ ከመረጡ ስልክዎን መክፈት በሚፈልጉበት ወቅት ቁጥራዊ ቁልፈ ሰሌዳን ያገኛሉ። ይህም በትንሽ ምናባዊ የቁልፍ ሰሌዳ ላይ የሆሄያት እና የምልክቶች ስብስብን ከመተየብ ቀላል መንገድ ሊኾን ይችላል። የአፕል እቃዎች የማለፊቃል መስበሪያ መሣሪያዎችን ፍጥነት እንዲቀንሱ ተደርገው የተሰሩ ቢኾንም የማለፊያ ኮድዎትን ረዘም ለማድረግ መሞከር አለብዎት። ከ6 አሃዞች በላይ የያዘ የማለፊያ ኮድ ለመፍጠር ይሞክሩ።

አንዴ የማለፊያ ኮዱን ከወሰኑ በኋላ ወደታችኛው የፓስኮድ ማዋቀሪያ ገጽ ያሸብልሉት። እዚህ ጋር ሲደርሱ “ዳታ ፕሮቴክሽን ኢኔብልድ” የሚል መልዕክት ሊያዩ ይገባል። ይህ ማለት የመሣሪያው ማመስጠሪያ ከማለፊያ ኮድዎት ጋር ተጣምዷል በመኾኑም በስልክዎት ላይ የሚገኙ አብዛኞቹን ውሂቦች ለመክፈት ኮዱ ያስፈልጋል ማለት ነው።

How to Encrypt Your iPhone 1

 

የግል ውሂብን በጥቅም ላይ ለማዋል ሊያስቧቸው የሚገቡ ሌሎች የiOS ገጽታዎች እዚህ ቀርበዋል፦ Anchor link

  • አይቲዩን የመሳሪያዎን ይዘት በኮምፒውተርዎ ላይ መጠባበቂያ ማስቀመጥ የሚያስችል ምርጫ አለው። በመሳሪያዎ በአይትዩን “ሰመሪ” ትር ላይ “ኢንክሪፕት ባክአፕ” የሚለውን ከመረጡ አይትዩን በጣም ሚስጥራዊ የኾኑ መረጃዎችን (ልክ እንደ የWifi የማለፊያ ቃል እና ኢሜል የማለፊያ ቃል) መጠባበቂያ ያስቀምጣል። በኮምፒውተርዎት ላይ ከማስቀመጡ በፊት ግን ያመሰጥረዋል። እዚህ ጋር የተጠቀሙትን የማለፊያ ቃል በደንብ ማስቀመጥዎን ያረጋግጡ። ውሂብዎን ከመጠባበቂያ መልስዎ ማግኘት አብዛኛውን ጊዜ የማይከሰት ኹኔታ ቢኾንም በድንገተኛ ጊዜ መጠባበቂያውን የሚከፍትልዎት የማለፊያ ቃልን ማስታወስ ካልቻሉ በጣም አድካሚ ነው።

  • በአፕል አይክላውድ ላይ መጠባበቂያን ካስቀመጡ ውሂቡን ከአደጋ ለመጠበቅ ረዥም የማለፊያ ሃረግ መጠቀም እና የማለፊያ ሃረጉን በሚያስተማምን ቦታ ማስቀመጥ አለብዎት። አፕል ብዙውን ውሂብ በመጠባበቂያዎቹ ላይ ቢያመሰጥርም ኩባንያው ውሂብዎትን ለሕግ አስፈጻሚ አካላት አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል (በተለይም በሚጻፉበት ወቅት ሳይመሰጠሩ የተጠራቀሙ ኢሜል እና ማስታወሻዎች)።

  • ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የውሂብ ጥበቃን ካስቻሉ በመሳሪያዎ ላይ ያለ ውሂብን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እና በፍጥነት መሰረዝ ይችላሉ። በፓስኮድ ማዋቀሪያ ውስጥ ከአስር የተሳሳተ የማለፊያ ሃረጎዎት ሙከራ በኋላ በመሳሪያዎ ላይ የሚገኘውን ውሂብ ሙሉ በሙሉ እንዲያጠፋ አድርገው ማዋቀር ይችላሉ።

  • በአፕል ቆየት ያለ የሕግ ማስፈጸም መመሪያ መሠረት “አፕል በማለፊያ ኮድ ከተቆለፉ ስልኮች በተወሰነ ክፍል (ካታጎሪ) ውስጥ የሚገኙ ውሂቦችን ማውጣት ይችላል። በተለይም በiOS መሣሪያ ላይ በተጠቃሚው የተመረቱ በአፕል መተግበሪያዎች ውስጥ ያሉ ንቁ ፋይሎች እናም ውሂቦች (“በተጠቃሚው የተመረቱ ንቁ ፋይሎች”) የማለፊያ ኮድን በመጠቀም የተመሰጠሩ ስላልኾነ ከስልኩ ላይ ማውጣት እና በውጭ ማህደረ መረጃ ለሕግ አስፈጻሚ አካላት ሊሰጥ ይችላል። iOS 4 ወይም ከዚያ ቅርብ በሆኑ የiOS ስሪቶች ላይ አፕል ይህንን የውሂብ ማውጣት ሂደትን ማከናወን ይችላል። እባክዎትን፣ ለሕግ አስፈጻሚ አካላት ሊሰጡ የሚችሉት በተወሰነ ክፍል ውስጥ ያሉ በተጠቃሚው የተመረቱ እንደ አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ እውቂያዎች፣ የድምጽ ቅጂዎች፣ እና የጥሪ ታሪክ ያሉ ንቁ ፋይሎች ብቻ መኾናቸውን ይገንዘቡ። አፕል እንደ ኢሜል፣ የቀን መቁጠሪያ ምዝገባዎች፣ ወይም የሦስተኛ አካል መተግበሪያ ውሂብን መስጠት አይችልም።”

ከላይ የተጠቀሰው መረጃ የሚሰራው ከiOS 8.0 በፊት ያሉ ስሪቶችን በሚጠቀሙ የiOS መሣሪዎች ብቻ ላይ ነው።

  • “አሁን iOS 8 በተጫነባቸው መሣሪያዎች ላይ ፎቶዎች፣ መልዕክቶች (አባሪዎችን ጨምሮ)፣ ኢሜል፣ ዕውቂያዎች፣ የጥሪ ታሪክ፣ የአይቲዩን ይዘት፣ ማስታወሻዎች፣ እና ማሳሰቢያዎች የመሳሰሉትን ግላዊ ውሂቦች በማለፊያ ኮድ ጥበቃ ውስጥ እንደሚቀመጡ” አፕል ይገልጻል። “… አፕል የማለፊያ ኮዶዎትን ማለፍ ስለማይችል ይህን ውሂብ ማግኘት አይችልም። ስለዚህ iOS 8ትን ከሚጠቀሙ መሣሪያዎች ላይ ይህንን ውሂብ አውጡልን ለሚል የመንግስት ትዕዛዝ በቴክኒክ ምክኒያት የተነሳ መመለስ አይችልም።”

ያስታውሱ፦ አፕል ከስልክዎት በቀጥታ ውሂብ ማውጣት የማይችል ቢኾንም መሳሪያው ከአይክላውድ ጋር በጥምረት እንዲሰራ ተደርጎ ከተዋቀረ፣ ወይም በኮምፒውተርዎት ላይ በተጠባባቂነት የተቀመጠ ከኾነ አብዛኛው ተመሳሳይ ውሂብ ለሕግ አስከባሪ አካላት በእርግጥ ሊገኝ ይችል ይኾናል። ብዙውን ጊዜ የiOS ምስጠራ ውጤታማ የሚኾነው መሣሪያው ሙሉውን ከጠፋ (ወይም ክፍቱን ሳይተው እንደ አዲስ ዳግም ከተነሳ) ብቻ ነው። አንዳንድ አጥቂዎች መሳሪያዎን ክፍት ኾኖ ሳለ ጠቃሚ ውሂብን ከማህደረ ትውስታ ውስጥ ሊውሰዱ ይችላሉ። (መሣሪያው ጠፍቶ እያለ እንኳን ውሂብን ሊውስዱ ይችላሉ)። ይህንን አውቀው ከተቻለ መሣሪያዎ በሌሎች ሰዎች ሊያዝብዎት ወይም ሊሰረቅ እንደሚችል በሚያስቡበት ወቅት መሣሪያዎት መጥፋቱን (ወይም ዳግም የተነሳ እና ክፍት እንዳልኾነ) ለማረገገጥ ይሞክሩ።

  • መሣሪያዎ እንዳይጠፋ ወይም እንዳይሰረቅ የሚሰጉ ከኾነ “ፋይንድ ማይ አይፎን” የሚባለውን ገጽታ በመጠቀም ከሩቅ ሥፍራ ኾነው ማጥፋት እንዲችሉ አድርገው የአፕል መሣሪያዎን ማዋቀር ይችላሉ። ይህ አፕል ከሩቅ ኾኖ በማንኛውም ሰዓት መሣሪያዎት ያለበት ሥፍራ የት እንደኾነ መጠየቅን እንደሚፈቅዱለት ይገንዘቡ። መሳሪያዎት ከቁጥጥርዎት ውጪ ቢኾን ውሂብን መሰረዝ ያለው ጥቅምን እና ያሉበትን ቦታ በመግለጽ የሚከተለውን ተጋላጭነት ማወዳደር አለብዎት። (የተንቀሳቃሽ ስልኮች ይህንን መረጃ ለአገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች ሲያስተላልፋ እንደ አይፓድ እና አይፖድ ተች ያሉ የWiFi መሳሪያዎች ግን አያስተላልፉም።)

Last reviewed: 
2015-05-29
ይህ ገጽ ከእንግሊዘኛው ቅጂ የተተረጎመ ነው፡፡ የእንግሊዘኛው ቅጂ ምን አልባት የበለጠ የዘመነ ይሆናል፡፡
JavaScript license information