Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ጥንድ ቁልፍ

የአደባባይ ቁልፍ ስነመሰውርን በመጠቀም የተመሰጠሩ መልዕክቶችን ለመቀበል (እና በአስተማማኝ ኹኔታ መልዕክቱ ከእርስዎ እንደመጣ ለሌሎች ለማሳወቅ) ሁለት ቁልፎችን መፍጠር ይጠበቅብዎታል። አንደኛው በምስጢር የሚጠብቁት የግል ቁልፍ ነው። ሌላኛው ደግሞ ሌሎች እንዲያዩት የሚፈቅዱት የአደባባይ ቁልፍ ነው። እነዚህ ሁለት ቁልፎች ቀመራዊ በኾነ መንገድ የተያያዙ ሲኾኑ በብዛት በጋራ ስማቸው "ጥንድ ቁልፍ" ይባላሉ።