የሚያጋጥምዎ አደጋዎችን መገምገም
Last Reviewed: January 10, 2019
ጠቅላላ ውሂብዎን ሁልጊዜ ከሁሉም ሰው ለመጠበቅ መሞከር እጅግ አድካሚ እና የማይቻል ነው፡፡ ነገር ግን መፍራት የለብዎትም! ደኅንነት በጥንቃቄ በሚነደፍ ዕድቅ የሚመራ እና ለእርሶ ትክክለኛ የሆነውን እየተጠቀሙ የሚያዳብሩት ሂደት ነው፡፡ ደኅንነት ማለት እንዳንድ መሳሪያዎች መጠቀም ወይም ሶፍትዌር ማውረድ ማለት አይደለም፡፡ እርስዎ በተለየ የተጋረጠብዎን የደኅንነት ስጋት ከመረዳት እና እነዚህን ስጋቶች እንዴት መመከት እንደሚቻል ከማወቅ የሚጀምር ነው፡፡.
በኮምፒተር ደኅንነት ስጋት የሚባለው ውሂብዎን ከጥቃት ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት የማሳነስ አቅም ያለው ክስተት ነው፡፡ ምን መከላከል እንደሚፈልጉ እና ከማን መከላከል እንደሚፈልጉ በመለየት ያጋጠመዎትን ስጋት መጋፈጥ ይችላሉ፡፡ ይህ ሂደት “የስጋት ሞዴል ” ይባላል፡፡
ይህ መመሪያ የስጋት ሞዴልዎን እንዴት መቅረጽ እንዳለብዎ ወይም የዲጂታል መረጃዎችዎ የሚያጋጥማቸውን አደጋ እንዴት መገምገም እንደሚችሉ እና የትኞቹ መፍትሔዎች ለእርስዎ የተሻለ እንደሆኑ ያስተምራል፡፡
የስጋት ሞዴል እንዴት ያለ ነገር ነው? ቤትዎ እና ንብረትዎን እንዳይዘረፉ ይፈልጋሉ እንበል፡፡ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቀዎች ይጠይቃሉ፡
በቤቴ ውስጥ ያለ ጥበቃ የሚያስፈልገው ነገር ምንድን ነው?
- የንብረትዎ ዝርዝር ጌጣጌጦች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ የባንክ ሰነዶች፣ የመጓጓዣ ሰነዶች ወይም ፎቶግራፎችን ሊጨምሩ ይቻላሉ፡፡
ከማን ነው ራሴን መከላከል የምፈልገው?
- የባለጋራዎችዎ ዝርዝር፡- ዘራፊዎችን፣ ደባልዎችዎን ወይም እንግዳዎችን ሊጨምር ይቻላል፡፡
መከላከል ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
- ጎረቤቶቼ ከዚህ በፊት ተዘርፈው ያውቃሉ? ደባሎቼ ወይም እንግዶቼ ምን ያህል ታማኝ ናቸው? ባለጋራዎቼ እኔን ማጥቃት የሚያስችል ምን አቅም አላቸው? ግምት ውስጥ የማስገባቸው አደጋዎች ምንድን ናቸው?
ይሄንን መከላከል ባልችል ሊደርስብኝ የሚችለው አደጋ መጠኑ ምን ያህል ነው?
- በቤቴ ያለ ልተካዉ የማልችለው ነገር ምን ምንድን ነው? እነዚህን ነገሮች መተካት የሚያስችል ገንዘብ እና ጊዜ አለኝ? የገባኹት የመድኅን ዋስትና ከቤቴ የተዘረፉ ንብረቶችን ይጨምራል?
ሊደርስብኝ ከሚችል አደጋ ራሴን ለመከላከል ምን ያህል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ?
- ለአደጋ የተጋለጡ ሰነዶችን ማሰቀመጫ የሚሆን ካዝና ለመግዛት ፍቃደኛ ነኝ? እጅግ አስተማማኝ ቁልፎችን የመግዛት አቅም አለኝ? በአቅራቢያዬ የሚገኝ ባንክ የደኅንነት ሳጥን ተከራይቼ ውድ ንብረቶቼን ለማስቀመጥ ጊዜ አለኝ?
እነዚህን ጥያቄዎች ለራስዎ ካቀረቡ በኋላ ማድረግ የሚችሉትን ነገር ለመገምገም ዝግጁ ነዎት፡፡ ንብረትዎችዎ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ሆነው ነገር ግን የመዘረፍ እድላቸው ዝቅተኛ ከሆነ ካዝና በመግዛት ብዙ ገንዘብ ማውጣት አይኖርብዎት ይሆናል፡፡ ነገር ግን አደጋው ከፍተኛ ከሆነ ገበያ ላይ የሚገኝ ምርጥ ካዝና መግዛት ይኖርብዎታልም፤ ደኅንነት ስርዓት ለመጨመርን ማሰብ ይኖርብዎታል፡፡
የደኅንነት ስጋት ሞዴል መገንባት የሚያጋጥምዎን የተለየ አደጋ ፣ ንብረትዎችዎን፣ ባለጋራዎችዎን፣ የባላጋራዎችዎን አቅም እና የተጋረጠብዎ አደጋ የመፈጸም ዕድል ምን ያህል እንደሆነ እንዲገነዘቡ ይረዳዎታል፡፡
የስጋት ሞዴል ምንድን ነው? ከየትስ ነው የሚጀምረው? anchor link
የስጋት ሞዴል ዋጋ በሚሰጧቸው ነገሮች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ነገሮች እንዲለዩ እና ከማን መጠበቅ እንደሚገባዎ እንዲያውቁ ይረዳዎታል፡፡ የስጋት ሞዴልዎን ሲቀርጹ ለእነዚህ አምስት ጥያቄዎች መልስ ያዘጋጁ:
- ምንድን ነው መከላከል የምፈልገው?
- ራሴን መከላከል የምፈልገው ከማን ነው?
- ይሄንን መከላከል ባልችል ሊደርስብኝ የሚችለው አደጋ መጠኑ ምን ያህል ነው?
- ራሴን መከላከል ምን ያህል ነው የሚያስፈልገኝ?
- ሊደርስብኝ ከሚችል አደጋ ራሴን ለመከላከል ምን ያህል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ?
እያንዳንዱን ጥያቄ በዝርዝር እንመልከት፡፡
ምንድን ነው መከላከል የምፈልገው? anchor link
ንብረት ዋጋ የሚሰጡት እና እንዳይጠፋብዎ የሚጠብቁት ነገር ነው፡፡ ስለ ዲጂታል ደህንነት በምንነጋገርበት ወቅት እሴት ወይም ንብረት የምንለው ነገር መረጃን እንደኾነ መታወቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ የኢሜል አድራሻዎ፣ የወዳጆችዎ ዝርዝር፣ የፈጣን መልዕክት ልውውጥዎ፣ ቦታዎች እና የተለያዩ ሰነድዎችዎ በሙሉ ንብረትዎችዎ ናቸው። በተጨማሪም ኮምፒውተርዎ፣ ስልክዎ እና የመሳሰሉትም ንብረትዎችዎ ናቸው።
የንብረትዎን ዝርዝር፣ ውሂብዎ የት እንደተቀመጠ፣ እነማን መጠቀም እንደሚችሉ እና ሌሎች እንዳይጠቀሙት የሚከለክላቸው ምን እንደኾነ ይጻፉ።.
ራሴን መከላከል የምፈልገው ከማን ነው? anchor link
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ማን እርስዎን አና መረጃዎችዎን ዒላማ ውስጥ ማስገባት ይፈልጋል የሚለውን ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ግለሰብ ወይም ሌላ አካል ንብረቶችዎ ላይ ስጋት የሚጥል ሁሉ “ባለጋራዎ” ነው፡፡ አለቃዎ፣ የቀድሞ ባልደረባዎ፣ የቢዝነስ ተፎካካሪዎ፣ የሀገርዎ መንግስት ወይም በህዝባዊ ትይይዝት ላይ ያለ የመረጃ ጠላፊ አቅም ያላቸው የባለጋራዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
የእርስዎን ውሂብ ወይም የግንኙነት መረጃዎን ማግኘት የሚፈልግ ማን ሊኾን እንደሚችል ጥርጣሬ ውስጥ በማስገባት የባለጋራዎችዎን ዝርዝር ያውጡ። እነርሱም ግለሰቦች፣ የመንግስት አካላት ወይም ተቋማት ሊኾኑ ይችላሉ፡፡
የስጋት ሞዴልዎን ካዘጋጁ በኋላ እንደባለጋራዎችዎ ማንነት፣ በተወሰኑ ሁኔታዎች ውስጥ ይህንን ዝርዝር ማስወገድ ይኖርብዎ ይሆናል፡፡
ይሄንን መከላከል ባልችል ሊደርስብኝ የሚችለው አደጋ መጠኑ ምን ያህል ነው? anchor link
ባለጋራዎ በመረጃዎ ላይ ጉዳት ወይም አደጋ ሊያደርስ የሚችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ ግንኙነትዎ በኔትወርክ በሚተላለፍበት ወቅት ባለጋራዎ የግንኙነትዎን ይዘት ሊያዳምጥ ወይም ሊያነብ፤ ወይም የግል ውሂብዎን ሊሰረዝ ወይም ሊያበላሽ ይችላል።
ባለጋራዎች የሚያደርሱት ጥቃት የተለያየ እንደኾነ ሁሉ ጥቃት ለመሰንዘር የሚነሱበት አላማም እንዲሁ የተለያየ ነው። ለምሳሌ ፖሊስ ወይም የተለያዩ የሕግ አስፈጻሚ አካላት የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያሳይ ቪዲዮ ቢኖርዎት መንግስት የዚህን ቪዲዮ ስርጭት ለመቀነስ በማሰብ ቪዲዮውን ለማጥፋት ወይም ተደራሽነቱን ለመቀነስ ሊሞክር ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካዊ ባላንጣዎችዎ እንዲህ ዓይነቱን ድብቅ መረጃ ያለ እርስዎ ዕውቀት በእጃቸው ማስገባት እና ማተም ይፈልጉ ይሆናል።
የስጋት ሞዴል ባለጋራዎ ከንብረትዎ በአንዱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቢሳካለት የሚያስከትለውን ጉዳት መጠን በመረዳት ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ ይህን ለማድረግ የባለጋራዎን አቀም ከግምት ውሰጥ ማስገባት ይገባል፡፡ ለምሳሌ የስልክ አገልግሎት አቅራቢ በስልክዎ የሚያደርጉትን ግንኙነት በሙሉ ማግኘት ስለሚችል የራስዎን መረጃ በመጠቀም ሊጎዳዎት ይችላል። ክፍት የኾኑ የዋይፋይ ኔትወርኮችን በሚጠቀሙበት ወቅት መረጃ ጠላፊዎች ያልተመሰጠሩ ግንኙነትዎትን ሊያገኙ ይችላሉ። መንግስታት ደግሞ የበለጠ አቅም ይኖራቸዋል፡፡
በመኾኑም ባለጋራዎ በግል ውሂብዎ ማድረግ የሚፈልገው ምን ሊኾን እንደሚችል ይዘርዝሩ።
መከላከል ምን ያህል አስፈላጊ ነው? anchor link
አደጋ የሚባለው የደኅንነት ስጋት የተወሰነ ንብረትዎን የምር መጠቃት አዝማሚያ ነው፡፡ ይህም ከአቅም ጋር ጎን ለጎን አብሮ የሚሄድ ነው። ምንም እንኳን የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢ የእርስዎን ውሂብ ሙሉ በሙሉ የማግኘት አቅም ቢኖረውም የእርስዎን መልካም ስም ለማጉደፍ ኾን ብለው የግል ውሂብዎን በአደባባይ ላይ የመለጠፍ አዝማሚያው አናሳ ነው።
በስጋት እና በአደጋው የመከሰት አዝማሚያ መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ጠቃሚ ነው። ስጋት ሊከሰት የሚችለው ጉዳት ሲኾን አደጋው የመከሰቱ አዝማሚያ ወይም ሪስክ የሚባለው ደግሞ ይህ ስጋት ሊከሰት የሚችልበት አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል ነው። ለምሳሌ የህንጻ መደርመስ ስጋት ቢኖር ይህ ስጋት ግን ለስምጥ ሸለቆ ቅርብ በሆኑ ከተሞች ሊከሰት የሚችልበት አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል በርቀት ከሚገኙት በጣም ከፍ ያለ ነው።
አደጋው የመከሰቱ አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል ትንተናን ማካሄድ ግለሰባዊ እና በግለሰቡ አመለካከት የተቃኘ ሂደት ነው። ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ስጋትን የሚያይበት እና ቅድሚያ የሚሰጥበት መንገድ ተመሳሳይ አይደለም። በርካታ ሰዎች የተወሰኑ ስጋቶች የመከሰት አዝማሚያቸው ምንም ይሁን ምን ለመጋፈጥ ፈቃደኛ አይደሉም። ምክንያቱም የስጋቱ መኖር ብቻ ከሚያስፈልጋቸው ዋጋ ጋር ሲወዳደር ሚዛን አይደፋም ብለው ስለሚያምኑ ነው። በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ ግለሰቦች አደጋው የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ቢኾንም እንኳን ስጋቱን እንደ ችግር አያዩትም።
በከፍተኛ ትኩረት ሊመለከቷቸው የሚገቡ ስጋቶችዎን በዝርዝር ይጻፉ፤ እንደገናም የመከሰት ዕድላቸው አናሳ የሆኑ ወይም ጉዳት የለሽ በመሆናቸው (ወይም ለመከላከል አዳጋች የሆኑትን) የሚያስጨንቅዎን ያስፍሩ፡፡
ሊደርስብኝ ከሚችል አደጋ ራሴን ለመከላከል ምን ያህል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ? anchor link
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የጉዳት አዝማሚያ ትንታኔ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች አይኖሩትም ወይም ስጋቶችን በተመሳሳይ መንገድ አይመለከትም፡፡
ለምሳሌ በብሔራዊ ደኅነነት ጉዳይ ውስጥ የሚገኝ ደንበኛውን የሚወክል የህግ አማካሪ/ጠበቃ ከአንድ ለልጅዋ አስቂኝ የድመት ቪዲዮዎችን ከምትልክ እናት በበለጠ የተመሰጠሩ ኢሜሎችን ለመጠቀም እና ግንኙነቶቹን ለመጠበቅ ብዙ ርቀት ይጓዛል፡፡
ልዩ ስጋቶችዎ የሚያደርሱብዎን ጉዳት ለመቀነስ ያልዎትን አማራጮች በሙሉ ይዘርዝሩ፤ የገንዘብ እጥረት፣ የቴክኒክ ጉድለት ወይም ማኀበራዊ እንቅፋት ካለብዎም ያስፍሯቸው፡፡
ስጋት ሞዴል እንደ የዘወትር ተግባር anchor link
የስጋት ሞዴልዎ እርስዎ ያሉበት ሁኔታ ሲቀየር አብሮ እንደሚቀየር በአእምሮዎ ይመዝግቡ፡፡ በዚህ ምክንያት በየጊዜው የስጋት ሞዴልን መገምገም ጥሩ ልምድ ነው፡፡
በራስዎ ልዩ ሆኔታ ላይ የተመሰረተ የራስዎን የስጋት ሞዴል ይፍጠሩ፡፡ለወደፊት በቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ፡፡ ይህም የስጋት ሞዴልዎን እንዲከልሱ እና አሁን ለሚገኙበት ሁኔታ ተገቢ መሆኑን እንዲፈትሹ ይረዳዎታል፡፡