የተቃውሞ ሰልፎች ላይ መሳተፍ (በአሜሪካ)
Last Reviewed: January 09, 2015
የግል የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች እየተስፋፉ በመምጣታቸው ምክንያት የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሚሳተፉ የሁሉም ዓይነት የፓለቲካ መስመር አቀንቃኞች የተቃውሞ ሰልፎችን እየቀረጹ ማስቀረት ከጀመሩ ሰንብተዋል። የተቃውሞ ሰልፍ ተሳታፊዎች የዲጅታል ካሜራ እና የተንቀሳቃሽ ስልኮችን በመጠቀም ከፓሊስ ጋር ያላቸውን ገጠመኞች ይቀርጻሉ። በተለይም በኾነ አጋጣሚ አድማ በታኝ ፖሊስ ወደ እርስዎ ሲመጣ የሚያሳይ አንድ ፎቶ ግራፍ ወይም ቪዲዮ ቀርጸው ቢያስቀሩ እርስዎ አምነውበት በአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ የወጡበት ጉዳይ የሌሎች ሰዎችን ትኩረት በቀላሉ እንዲያገኝ ሰበብ እንዲሁም እጅግ ኃያል ምልክት ሊኾን ይችላል።
እራስዎን በተቃውሞ ሰልፎች ላይ ኾነው ቢያገኙት እና በአጋጣሚ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ቢውሉ ወይም በፖሊስ ቢጠየቁ እና የኤልክትሮኒክ ማሳሪያዎችዎን መከላከል ቢያስስፈልግዎት የሚከተሉትን ምክሮች ማስታውስ ጠቃሚ ነው። እነዚህ ምክሮች እንደ አጠቃላይ መመሪያ የሚያገለግሉ መኾናቸውን ማስታውሱ ተገቢ ነው። ነገር ግን እርስዎን በተለየ የሚያሳስብዎት ነገር ካለ እባክዎትን ጠበቃዎትን ያነጋግሩ።
ከዩናይትድ ስቴት ውጪ ነው የሚኖሩት? ተቃውሞ ለሚታደሙ ያዘናጀነውን መመሪያ ይመልከቱ (አለም ዓቀፍ)፡፡
የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከመሳተፍዎት በፊት የተንቀሳቃሽ ስልክዎትን ደህንነት ያረጋግጡ anchor link
የተቀንሳቃሽ ስልክዎትን ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ስፍራ ይዘው ከመምጣትዎ በፊት በጥንቃቄ ያስቡበት።
የተንቀሳቃሽ ስልክዎት በርካታ የግል ውሂቦችን ይይዛል። ይህም የእውቂያ ዝርዝሮችን፣ የቅርብ ጊዜ የስልክ ጥሪ ስም ዝርዝርን፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን፣ የኢሜል ልውውጦችን፣ ፎቶግራፎች እና ቪዲዮዎችን፣ የGPS የሥፍራ ውሂብን፣ የድረ መረብ እሰሳ ታሪኮችን እና የማለፊያ ቃሎችን ወይም ንቁ መግቢያዎችን፣ ኢሜል እና የማህበራዊ ሚዲያ መለያ ይዘቶችን ይጨምራል። ሌሎች ሰዎች በተንቀሳቃሽ ስልክዎት ላይ ያስቀመጡትን የማለፊያ ቃላትን ተጠቅመው ራቅ ካለ ሥፍራ ካለ አገልጋይ ኮምፒውተር ወደ ማኅበራዊ ድረ ገጽ መለያዎ ሊገቡ ይችላሉ።
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቅርቡ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ሰዎች መረጃ ለማግኘት የፍርድ ቤት ማዘዣ ማግኘት እንዳለበት ወስኗል። ነገር ግን የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ውስንነቶች ገና በደንብ እየተመረመሩ ነው። በተጨማሪም የሕግ አስፈጻሚ አካላት የተንቀሳቃሽ ስልኮችን የወንጀል ማስረጃ ይገኝባቸዋል (ለምሳሌ በተቃውሞ ሰልፍ ላይ ያነሱዋቸው ፎቶዎች) ወይም ለሌላ ምርመራ እንደመነሻነት ያገለግላሉ ብለው ስለሚያምኑ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው ይፈልጋሉ። በቁጥጥር ስር የዋሉትን ስልኮች ለመመርመር የፍርድ ማዘዣ ቆየት ብለው ሊያገኙ ይችላሉ።
መብትዎን ለማስጠበቅ በእጅዎ ላይ ያለውን ስልክ ጠበቅ አድርገው በመያዝ ከፍለጋ መከላከል ይችላሉ። በተጨማሪም ወደ ተቃውሞ ሰልፍ በሚወጡበት ወቅት አማራጭ ስልክ ይዘው ለመውጣት ማሰብ ይኖርብዎታል። ይህ አማራጭ ስልክ እጅግ አንገብጋቢ የኾኑ ውሂቦችን ያልያዘ እና የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎን በፍጹም ያልተጠቀሙ እና ቢጠፋ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ከእርስዎ ቢርቅ ምንም ጉዳት የማያደርስ መኾኑን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። በርካታ ወይም አንገብጋቢ የኾነ መረጃን የያዘ ስልክ ይዞ ከመውጣት ይልቅ ሌላ አማራጭ ስልክ ይዞ መውጣት የተሻለ ነው።
የማለፊያ ቃል መከላከያ እና ማመስጠሪያ አማራጮች፦ ሁልጊዜም ስልክዎትን በማለፊያ ቃል ይዝጉት። ስልክዎትን በማለፊያ ቃል መዝጋት ወይም መቆለፍ ከአባዲና ሞያዊ ትንተና ሊከላከል እንደማይችል ማወቅ ያስፈልግል። ምንም እንኳ ደህንነቱ የተረጋገጠው አማራጭ ስልክዎን ሌላ ቦታ መተው ቢኾንም አንድሮይድ እና አይፎን ሁለቱም በስረዓተ ክወናቸው ሙሉ በሙሉ የዲስክ ማመስጠር አገልግሎትን ስለሚሰጡ መጠቀም ይኖርብዎታል።
በአንድሮይድ ላይ የተንቀሳቃሽ ስልክን ማመስጠር ዋንኛ ችግር ዲስኩን ለማመስጠር እና ስክሪኑን ዘግቶ ለመክፈት የሚጠቀሙት ተመሳሳይ የማለፊያ ቃል መኾኑ ነው። ይህ የዲዛይን ችግር ነው ምክኒያቱም ተጠቃሚዎች ለማመስጠር እጅግ ደካማ የኾነ የማለፊያ ቃል ወይም ለስክሪናቸው እጅግ የረዘመ እና አመቺ ያልኾነ የማለፊያ ቃል እንዲመርጡ ስለሚያስገድድ ነው። የተሻለው አማራጭ የሚኾነው በመሣሪያዎት ላይ በቀላሉ ለማስገባት አመቺ የኾኑ ከ8-12 ርዝመት ያለው የዘልማድ ምልክቶችን የያዘ የማለፊያ ቃል መጠቀም ነው። ወይም የአንድሮይድ ስልክዎ የስር ግንኙነት ካለዎት እና ሼልን መጠቀም የሚያውቁ ከኾነ ይህንን ያንብቡ። (በተጨማሪም የጹሑፍ መልዕክቶችን እና የድምጽ ጥሪዎችን እንዴት ማመስጠር እንደሚችሉ ጥልቀት ላለው መረጃ "ከሌሎች ጋር ስለሚደረግ ግንኙነት” የሚለውን ሞጁል ይመልከቱ።)
የውሂብዎትን መጠባበቂያ ማስቀመጥ፦ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ምናልባት ሊውል ስለሚችል በስልክዎ ላይ ያለን ውሂብ መጠባበቂያ ማስቀመጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። የዚህም ጥቅም የተንቀሳቃሽ ስልክዎትን ለተወሰነ ጊዜ ላያገኙት ስለሚችሉ እና አውቀውም ኾነ ሳያውቁ በተንቀሻቃሽ ስልክዎት ውስጥ ያሉ ይዘቶች ሊሰረዙ ወይም ሊጠፉ ስለሚችሉ ነው። ምንም እንኳን ፖሊስ በስልክዎት ውስጥ ያሉ ይዘቶችን ማጥፋቱ ትክክለኛ እንዳልኾነ ብናምንም ውሂብዎ የመጥፋት አጋጣሚ ሊኖረው ይችላል።
በተመሳሳይ ምክንያት ስልክዎ ሊጠፋብዎት ስለሚችል እና ስልክ መደወል ሊፈጉ ስለሚችሉ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ግን የማያስወነጅል የስልክ ቁጥርን በማይጠፋ ማርከር ገላዎት ላይ መጻፍን ከግምት ውስጥ ያስገቡ።
የስልክ የሥፍራ መረጃ፦ የተንቀሳቃሽ ስልክዎትን የተቃውሞ ሰልፍ በሚካሄድበት ስፍራ ይዘው ቢሄዱ መንግስት የት ሥፍራ እንዳሉ ለማወቅ ከአገልግሎት ሰጪው መረጃ በመጠየቅ ሊደርስበት ይችላል። (የሥፍራ መረጃን ለመውሰድ መንግስትን የፍርድ ቤት ማዘዣ እንዲያገኝ ሕጉ የሚያስገድድ እንደኾነ እኛ ብናምንም ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ መንግሥት በዚህ አይስማማም)። በተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንደተሳተፉ መንግስት እንዲያውቅብዎት ካልፈለጉ ስልክዎትን የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ይዘው መሄድ የለብዎትም። የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ መገኘት ግድ የሚኾን ከኾነ በስምዎ ያልተመዘገበ የተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ይገኙ።
ከተያዙ ወይም ከታሰሩ የሥራ ባልደረባዎን ለማግኘት ይቸገሩ ይኾናል። ከሰላማዊ ሰልፍ በኋላ ቀድመው ያቀዱትን የስልክ ጥሪ ለጓደኛዎ ማድረግ ይፈልጉ ይኾናል። ይህንን ሳያደርጉ ሲቀሩ የሥራ ባልደረባዎት እና ጓደኞችዎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሊገምቱ ይችላሉ።
አሁን በተቃውሞ ሰልፍ ቦታ ላይ ነዎት ምን ማድረግ ይኖርብዎታል? anchor link
የተቀሳቃሽ ስልክዎን በጥብቅ ቁጥጥር ውስጥ ማኖር፦ ጥብቅ ቁጥጥር ማለት በማንኛውም ሰዓት ስልክዎ ከእጆ እንዳይወጣ መጠንቀቅ ወይም እርስዎን በሕግ ቁጥጥር ስር ሊያውል በሚችል ጉዳይ የሚጠመዱ ከኾነ ለልብ ጓደኛዎ መስጠት ማለት ነው።
ፎቶዎችን ማንሳት እና ቪዲዮዎችን መቅረጽ ማሰብ፦ ካሜራዎች በተቃውሞ ሰልፍ ላይ መኖራቸው ብቻ ፖሊሶችን አላስፈላጊ ከኾነ ባህሪ እንዲቆጠቡ ያደርጋቸዋል። EFF እርስዎ የአደባባይ ተቃውሞ ሰልፎችን የፖሊስ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ የመቅረጽ የፈርስት አሜንድመት መብት እንዳለዎት ያምናል። ነገር ግን ፖሊስ የተለያዩ የስቴት እና የአካባቢ ሕጎችን በመጥቀስ ከእኛ አቋም ጋር ላይስማማ እንደሚችል ይገንዘቡ። የድምጽ ቀረጻ ለማካሄድ የሚያስቡ ከኾነ ረፖርተርስ ኮሚቲ ፎር ፍሪደም ኦፍ ዘ ፕረስ ካን ዊ ቴፕ የሚለውን? ጠቃሚ መመሪያ ይከልሱ።
ማንነትዎን እና የሥፍራ አድራሻዎን መደበቅ የሚፈልጉ ከኾነ ፎቶዎችን ከመለጠፍዎ በፊት ሜታ ዳታውን ከፎቶዎቹ ላይ ሙሉ በሙሉ መሰረዝዎትን ያረጋግጡ።
በሌላ ኹኔታዎች ውስጥ ደግሞ ሜታ ዳታዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ስለመሳተፍዎ እውነተኛነት ለማረገጋጥ እንደ ማስረጃ ሊጠቅሙ ይችላሉ። የዘ ጋርዲያን ፕሮጀክት ኢንፎርማካም የተሰኘ ሜታ ዳታዎችን ከተጠቃሚዎች መረጃ ማለትም የGPS ኮርድኔትን፣ ከፍታን፣ የኮምፓስ አቅጣጫን፣ የብርሃን መጠን ንባብን፣ በአካባቢው የነበሩ ሌሎች መሳሪያዎች ምልክትን፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ ምሶሶዎችን፣ እና የWiFi መረቦችን መመዝገብ የሚችል መሳሪያ ሰርቷል። ይህም የዲጂታል ፎቶው የተቀረጸበትን ኹኔታ እና አውድ በገሀድ ያሳያል።
ፎቶ ወይም ቪዲዮ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ቀርጸው ካስቀሩ ፖሊስ እንደ መረጃ ሊጠቀመው ስለሚፈልግ ስልክዎን በቁጥጥር ስር ሊያውለው ይፈልግ ይኾናል። በጋዜጠኝነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ከኾነ የጋዜጠኝነት መብትዎን በመጠቀም ያልታተመ ስራዎትን መከላከል ይችላሉ። RCFP በተለያዩ ስቴቶች የጋዜጠኞችን መብት የሚገልጽ መመሪያ አለው።
ማንነትዎ እንዳይታወቅ የሚፈልጉ ከኾነ በፎቶ አማካኝነት እንዳይታወቁ ፊትዎትን ይሸፍኑ። ጭምብል ማጥለቅ በአንዳንድ አካባቢዎች በሕግ የሚያስጠይቅ ስለኾነ ችግር ውስጥ ሊጥልዎት ይችላል።
እየታሰርኩ ነው እርዱኝ! እርዱኝ! anchor link
Remember that you have a right to remain silent—about your phone and anything else.
ያስታውሱ ስለ ስልክዎም ኾነ ስለ ማንኛውም ነገር ምንም ያለማለት መብት አለዎት። .
ፖሊስ ቢጠይቅዎት በትህትና ነገር ግን ጠበቅ አድርገው ጠበቃዎትን ማናገር እንዳለብዎት እንዲሁም ከዚህ በኋላ ጠበቃዎ እስኪገኝ ምንም አይነት ጥያቄ እንደማያስተናግዱ ይናገሩ። እጅግ የተሻለው መፍትሄ ጠበቃዎን የማናገር እድል እስኪያገኙ ድረስ ምንም አለመናገር ነው። ነገር ግን ጥያቄዎችን ለመመለስ ከወሰኑ እውነቱን ይናገሩ። ለፖሊስ መዋሸት እንደ ወንጀል የመቆጠር እድሉ ከበድ ያለ ሲኾን በኮምፒውተርዎ ውስጥ ከሚፈልጉት ነገር ይልቅ ለሕግ አስፈጻሚ አካል በመዋሸትዎ እራስዎን የከፋ ችግር ውስጥ ሊከቱ ይችላሉ።
ፖሊስ ስልክዎን ለማየት ቢፈልግ ስልክዎትን እንዲበረብር ፈቃደኛ እንዳልኾኑ ይናገሩ። እንዲህም ኾኖ ከታሰሩ በኋላ ስልክዎትን በማዘዣ አማካኝነት ሊበረብሩ ይችላሉ። ነገር ግን እርስዎ በትንሹም ቢኾን ይህንን እንዲያደርጉ ፈቃደኛ እንዳልኾኑ ግልጽ አድርገዋል።
ፖሊስ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችዎን የማለፊያ ቃላት ቢጠይቅዎ (ወይም እንዲከፍቱት ቢጠይቅዎ) ለመስጠት ፍቃደኛ እንዳልኾኑ በትህትና ይግለጹ እና ከጠበቃዎ ጋር ለመነጋገር ፈቃድ ይጠይቁ። ፖሊስ ስልኩ የእርስዎ እንደኾነ ቢጠይቅዎ ባለቤትነትዎን ወይም በስልኩ ላይ ያለዎትን ቁጥጥር ባለማመን ወይም ባለመክዳት በሕጋዊ መንገድ በእጅዎ ላይ የሚገኝ እንደኾነ መናገር ይችላሉ። ሁሉም የእስር ኹኔታ ይለያያል በመኾኑም የእርስዎን ዓይነተኛ የእስር ኹኔታ ለመፍታት ከጠበቃዎ ጋር መነጋገር ይኖርብዎታል።
ራስዎን በወንጀለኝነት የማያስጠይቅ ምስክርነትን ስለሚከላከልልዎት ስለ ፊፍዝ አሜንድመንት መብትዎ ጠበቃዎን ይጠይቁ። የማመስጠሪያ ቁልፍዎን ወይም የማለፊያ ቃልዎን አሳልፎ መስጠት ይህን መብት የሚነካ ከኾነ ፍርድ ቤት እንኳን ይህንን መረጃ እንዲሰጡ ማስገደድ አይችልም። የማመስጠሪያ ቁልፍዎን ወይም የማለፊያ ቃልዎን ለመንግስት በመስጠትዎ ምክንያት መንግስት የሌለውን መረጃ (በኮምፒውተርዎ ውስጥ ያሉ ሰነዶችን አጋልጦ የሚሰጥ ከኾነ) ፊፍዝ አሜንድመት ይህን ሊከላከልልዎት እንደሚችል ጠንካራ የመከራከሪያ ነጥብ አለ። ነገር ግን የማመስጠሪያ ቁልፍዎን ወይም የማለፊያ ቃልዎን መስጠት እራስዎ ላይ እንደመመስከር የማይቆጠር ከኾነ ለምሳሌ በውሂቦ ላይ የራስዎ ቁጥጥር እንዳለ ማሳየት ከተቻለ ፊፍዝ አሜንድመት ጥበቃ ላያደርግልዎት ይችላል። በዚህ ጉዳይ ላይ የእርስዎን ኹኔታ በተመለከተ ጠበቃዎ ሊረዳዎት ይችላል።
ፖሊስ የማለፊያ ቃልዎን እንዲሰጡ ሊያስገድዶት አይችልም ማለት የማለፊያ ቃልዎን ለማግኘት ጫና አያደርስቦትም ማለት አይደለም። ፖሊስ ከእነርሱ ጋር እንደማይተባበሩ ካሰቡ ወዲያውኑ በነጻ ከማሰናበት ይልቅ በእስር ሊያቆይዎት ይችላሉ። በእንደዚህ ዓይነት ጊዜ ለፖሊስ ለመታዘዝ ወይም ላለመታዘዝ መወሰን ይኖርብዎታል።
ፖሊስ የተንቀሳቃሽ ስልኬን ይዞታል እንዴት ማግኘት እችላለሁ? anchor link
በሕገ ወጥ መንገድ ስልክዎ ወይም የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎ ከተያዘ እና በሚለቀቁበት ወቅት ወዲያውኑ ካለተመለሰልዎት ጠበቃዎ ንብረትዎን እንዲመለስልዎት በፍርድ ቤት ሊጠይቅልዎት ይችላል። ፖሊስ በኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎ ውስጥ የወንጀል ማስረጃ ፎቶዎች ወይም ቪዲዮዎች ጨምሮ እንደተገኘ ካመነ መሳሪዎን እንደ ማስረጃ ሊይዘው ይችላል። የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎን ሙሉ በሙሉ እንዲተውላቸው ይሞክሩ ይኾናል ነገር ግን ይህንን በፍርድ ቤት መከራከሩ ተመራጭ ይኾናል።
የተንቀሳቃሽ ስልክዎ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የተቃውሞ ሰልፎች ዋንኛ መገለጫዎች ናቸው። በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ዜጎችም ኾኑ ዜጎች ያልሆኑ ነዋሪዎች የአሜሪካን የመጀመሪያ ማሻሻያ ሕግ (ፈርስት አሜንድመንት) የመናገር እና የመሰብሰብ ነጻነታቸውን መጠቀም ይችላሉ፤ አለባቸውም። ከላይ የተጠቀሱት ምክሮች ለእርስዎ በብልሃት ንብረትዎን እና ግላዊነትዎን ለማስተዳደር ይጠቀሙበታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።