Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የተቃውሞ ሰልፎች ላይ መሳተፍ (ዓለም አቀፍ)

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

የግል የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች እየተስፋፉ በመምጣታቸው ምክንያት የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሚሳተፉ የሁሉም ዓይነት የፓለቲካ መስመር አቀንቃኞች የተቃውሞ ሰልፎችን እየቀረጹ ማስቀረት ከጀመሩ ሰንብተዋል። የተቃውሞ ሰልፍ ተሳታፊዎች የዲጅታል ካሜራ እና የተንቀሳቃሽ ስልኮችን በመጠቀም ከፓሊስ ጋር ያላቸውን ገጠመኞች ይቀርጻሉ። በተለይም በኾነ አጋጣሚ አድማ በታኝ ፖሊስ ወደ እርስዎ ሲመጣ የሚያሳይ አንድ ፎቶ ግራፍ ወይም ቪዲዮ ቀርጸው ቢያስቀሩ እርስዎ አምነውበት በአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ የወጡበት ጉዳይ የሌሎች ሰዎችን ትኩረት በቀላሉ እንዲያገኝ ሰበብ እንዲሁም እጅግ ኃያል ምልክት ሊኾን ይችላል። በተቃውሞ ሰልፎች ላይ ራስዎን ቢያገኙት እና በአጋጣሚ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ቢውሉ ወይም በፖሊስ ቢጠየቁ እና የኤልክትሮኒክ ማሳሪያዎቾን መከላከል ቢያስስፈልግዎት የሚከተሉትን ምክሮች ማስታውስ ጠቃሚ ነው። እነዚህ ምክሮች እንደ አጠቃላይ መመሪያ የሚያገለግሉ መኾናቸውን ማስታውሱ ተገቢ ነው። ነገር ግን እርስዎን በተለየ የሚያሳስብዎት ነገር ካለ እባክዎትን ጠበቃዎትን ያነጋግሩ።

በዩናይትድ ስቴት ውስጥ የሚደረግ ተቃውሞን ለሚታደሙ ያዘጋጀነውን መመሪያ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎን ለተቃውሞ ሰልፍ ማዘጋጀት anchor link

የተንቀሳቃሽ ስልክዎትን ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ይዘው ከመሄድዎ በፊት በስልክዎ ላይ ምን ምን እንዳለ በጥንቃቄ ይመርምሩ። የተንቀሳቃሽ ስልክዎ በርካታ የግል ውሂቦችን ይይዛል። ይህም የእውቂያ ዝርዝሮችን፣ የቅርብ ጊዜ የስልክ ጥሪ ስም ዝርዝርን፣ አጭር የጽሁፍ መልዕክቶችን እና የኢሜል መልዕክት ልውውጦችን፣ ፎቶግራፎች እና ቪዲዮዎችን፣ የGPS የሥፍራ ውሂብን፣ የድረ መረብ አሰሳ ታሪኮችን እና የማለፊያ ቃሎችን እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያ መለያ ይዘቶችን ሊጨምር ይችላል። በተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ የተቀመጡ የማለፊያ ቃሎችን ወይም ንቁ መግቢያዎችን በመጠቀም የኾነ ሰው ራቅ ካለ ሥፍራ ከጠቀመጠ አገልጋይ ኮምፒውተር ወደ ማህባራዊ ድረ ገጽ መለያው መግባት እና ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላል:: (ከእነዚህ አገልግሎቶች ዘግተው መውጣት ይችላሉ)።

በብዙ አገራት ዜጎች የተንቀሳቃሽ ስልክ በሚገዙበት ወቅት የሲም ካርዳችውን የማስመዝገብ ግዴታ አለባችው። ይህም የተቃውሞ ሰልፍ ወደሚደረግበት ሥፍራ ስልክዎን ከወሰዱ የመንግስት አካላት እርስዎ በዛ ስፍራ መኖርዎን ለማወቅ በቀላሉ ይረዳችዋል። በተቃውሞ ሰልፎች ላይ መገኝትዎን ምስጢር ማድረግ እና የመንግሥት ወይም የሕግ አስፈጻሚ አካላት እንዳያውቁ የሚፈልጉ ከኾነ በፎቶዎች ላይ ማንነትዎ እንዳይታወቅ ለማድረግ ፊትዎን ይሸፍኑ። ነገር ግን በአንዳንድ አካባቢዎች ባለው የጸረ ጭምብል ሕግ መሠረት ጭምብል ማጥለቅ ሌላ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ይገንዘቡ። በተጨማሪም የተንቀሳቃሽ ስልክዎን ይዘው አይሂዱ። የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ መገኘት ግድ ከኾነብዎ በስምዎ ያልተመዘገበ የተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ለመሄድ ይሞክሩ።

መብትዎን ለማስጠበቅ በእጅዎ ላይ ያለውን ስልክ ጠበቅ አድርገው በመያዝ ከፍለጋ መከላከል ይቻላል። በተጨማሪም ወደ ተቃውሞ ሰልፍ በሚወጡበት ወቅት አማራጭ ስልክ ይዘው ለመምጣት ማሰብ ይኖርብዎታል። ይህ አማራጭ ስልክ እጅግ አንገብጋቢ የኾኑ ውሂቦችን ያልያዘ እና የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎን በፍጹም ያልተጠቀሙበት እና ቢጠፋ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ከእርስዎ ቢርቅ ምንም ጉዳት የማያደርስ መኾኑን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። በርካታ ወይም አንገብጋቢ የኾነ መረጃን የያዘ ስልክ ይዞ ከመውጣት ይልቅ አማራጭ ስልክ ይዞ መውጣት የተሻለ ነው።

የማለፊያ ቃል መከላከያ እና የማመስጠሪያ አማራጮች፦ ሁልጊዜም ስልክዎትን በማለፊያ ቃል ይዝጉት። ነገር ግን ስልክዎን በማለፊያ ቃል መዝጋት ወይም መቆለፍ ከአባዲና ሞያዊ ትንተና ሊከላከል እንደማይችል ማወቅ ያስፈልግል። ምንም እንኳ ደህንነቱ የተረጋገጠው አማራጭ ስልክዎን ሌላ ቦታ መተው ቢኾንም አንድሮይድ እና አይፎን ሁለቱም በስርዓተ ክወናቸው ሙሉ በሙሉ የዲስክ ማመስጠር አገልግሎትን ስለሚሰጡ መጠቀም ይኖርብዎታል።

በአንድሮይድ ላይ የተንቀሳቃሽ ስልክን ማመስጠር ዋንኛ ችግር ዲስኩን ለማመስጠር እና ስክሪኑን ዘግቶ ለመክፈት የሚጠቀሙት ተመሳሳይ የማለፊያ ቃል መኾኑ ነው። ይህ የዲዛይን ችግር ነው ምክንያቱም ተጠቃሚዎች ለማመስጠር እጅግ ደካማ የኾነ የማለፊያ ቃል ወይም ለስክሪናቸው እጅግ የረዘመ እና አመቺ ያልኾነ የማለፊያ ቃል እንዲመርጡ ስለሚያስገድድ ነው። የተሻለው አማራጭ የሚኾነው በመሣሪያዎት ላይ በቀላሉ ለማስገባት አመቺ የኾኑ ከ8-12 ርዝመት ያለው የዘልማድ ምልክቶችን የያዘ የማለፊያ ቃል መጠቀም ነው። በተጨማሪም የአንድሮይድ ስልክዎ የሥር ግንኙነት ካለው እና ሼልን መጠቀም የሚያውቁ ከኾነ ለሙሉ ዲስክ ምስጠራ የተለየ (ረዥም) የማለፊያ ቃል ማዋቀር እንዴት እንደሚቻል ለበለጠ መመሪያ ይህንን ያንብቡ። (በተጨማሪም የጹሑፍ መልእክቶችን እና የድምጽ ጥሪዎችን እንዴት ማመስጠር እንደሚችሉ ጥልቀት ላለው መረጃ "ከሌሎች ጋር ስለሚደረግ ግንኙነት” የሚለውን ሞጁል ይመልከቱ።)

የውሂብዎትን መጠባበቂያ ማስቀመጥ፦ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ምናልባት ሊውል ስለሚችል በስልክዎ ላይ ያለን ውሂብ መጠባበቂያ ማስቀመጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። የእዚህም ጥቅም የተንቀሳቃሽ ስልክዎትን ለተወሰነ ጊዜ ላያገኙት ስለሚችሉ እና አውቀውም ኾነ ሳያውቁ በተንቀሻቃሽ ስልክዎት ውስጥ ያለ ይዘት ሊሰረዝ ወይም ሊያጠፋ ስለሚችል ነው።

በተመሳሳይ ምክንያት ስልክዎ ሊጠፋብዎት ስለሚችል እና ስልክ መደወል ሊፈጉ ስለሚችሉ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ግን የማያስወነጅል የስልክ ቁጥርን በማይጠፋ ማርከር ገላዎት ላይ መጻፍን ከግምት ውስጥ ያስገቡ።

የስልክ የሥፍራ መረጃ፦ የተንቀሳቃሽ ስልክዎትን የተቃውሞ ሰልፍ በሚካሄድበት ስፍራ ይዘው ቢሄዱ መንግሥት የት ሥፍራ እንዳሉ ለማወቅ ከአገልግሎት ሰጪው መረጃ በመጠየቅ ሊደርስብዎት ይችላል። (የሥፍራ መረጃን ለመውሰድ መንግሥትን የፍርድ ቤት ማዘዣ ማግኘት እንዳለበት ብናምንም አብዛኛውን ጊዜ መንግሥት በዚህ ጉዳይ አይስማማም)። በተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንደተሳተፉ መንግሥት እንዲያውቅብዎት ካልፈለጉ ስልክዎትን የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ይዘው መሄድ የለብዎትም። የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ መገኘት የግድ የሚኾን ከኾነ በስምዎ ያልተመዘገበ የተንቀሳቃሽ ስልክ ይጠቀሙ።

በሰላማዊ ሰልፍ ሂደት ውስጥ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የመዋል አደጋ ሊያጋጥምዎት እንደሚችል ፍርሃት ከገባዎት ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ላለ ለቅርብ ወዳጅዎ የሚልኩት መልዕክት ቀድሞ ማዘጋጀት ጥሩ ልምምድ ነው። የጽሑፍ መልእክቱን ቀድመው ይጻፉ እና መታሰርዎትን እንዲያውቁ አደጋ በሚያጋጥምዎት ወቅት ቶሎ መላክ እንዲመችዎት አድርገው ያስቀምጡት። በተመሳሳይ ኹኔታ ከሰላማዊ ሰልፍ በኋላ ቀድመው ያቀዱትን የስልክ ጥሪ ለጓደኛዎ ማድረግ ይፈልጉ ይኾናል። ይህንን ሳያደርጉ ቢቀሩ የሥራ ባልደረባዎ እና ጓደኛዎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሊያስቡ ይችላሉ።

የተንቀሳቃሽ ስልክዎ እንደተወሰደ እና እርስዎ የታሰሩ እንደኾነ ከማሳወቅዎ በተጨማሪ ይህ ታማኝ ጓደኛዎት የኢሜልዎትን እና የማህበራዊ ሚዲያ ድረ ገጽ መለያዎትን የማለፊያ ቃል ሊቀይር ይችላል። ይህም ምናልባት የመንግሥት አካላት የይለፍ ቃልዎን አሳልፈው እንዲሰጡ በጉልበት የሚያስገድድዎት ከኾነ ሊጠቅም ይችላል።

እባክዎን፤ በአንዳንድ የሕግ ስርዓቶች ኾን ብሎ ማስረጃን መደበቅ ወይም ማጥፋት በራሱ ሕገ ወጥ ድርጊት ኾኖ ሊወሰድ እንደሚችል ይወቁ (ይህ የተለያዩ ሶሻል ዲሞክራሲ አገሮችን ይጨምራል)።

እርስዎ እና ጓደኛዎ እንደዚህ ባለው እቅድ ውስጥ ከመሳተፋችሁ በፊት የአገሪቱን ሕግ እና ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መረዳታችሁን ማረጋገጥ አለባችሁ። ለምሳሌ የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ያሉት ዲሞክራሲ እና የሕግ የበላይነት በሚከበርበት እና የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ እንደ ወንጀል በማይቆጠርበት አገር ላይ ከኾነ የሕግ አስፈጻሚ አካላት መለያዎችዎን እንዳያገኟቸው መደበቅ ሕግ እንደጣሱ ሊያስቆጥርብዎት ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ የሕግ የበላይነት በሌለባቸው አገራት ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ እንደ ወንጀል የሚቆጠርባቸው ኹኔታዎች ስለሚኖሩ ወዳጆችዎን እና የሚቀርቡትን የስራ አጋርዎትን ሊደርስባቸው ከሚችል አካላዊ ጥቃት መጠበቅ ቀዳሚ አላማዎ ሊኾን ይገባል።

አሁን በተቃውሞ ሰልፍ ቦታ ላይ ነዎት ምን ማድረግ ይኖርብዎታል? anchor link

አንዴ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከኾኑ የሕግ አስፈጻሚ አካላት በአካባቢው ያለውን ግንኙነት እየተቆጣጠሩ ሊኾን እንደሚችል ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብዎት። ስለዚህ ቴክስት ሴኪዩርን በመጠቀም የጽሑፍ መልዕክትዎን ቻት ሴኪዩርን በመጠቀም የጽሁፍ ውይይትዎን ፣ ወይም ሬድ ፎንን፣ ወይም ሲግናልን በመጠቀም የስልክ ንግግርዎን ማመስጠር ይችላሉ።

እዚህ ጋር ልብ ይሉት ዘንድ የሚገባው የግንኙነት መስመርዎ የተመሰጠረ ቢኾንም እንኳን የመረጃ መረጃዎ ወይም ሜታ ዳታዎ የተመሰጠረ አይደለም። ይህም ማለት የተንቀሳቃሽ ስልክዎ ያሉበትን የሥፍራ አድራሻ እና የግንኙነትዎን ሜታ ዳታ ማለትም ከማን ጋር እና ለምን ያህል ሰዓት እንደተነጋገሩ የመሳሰሉትን መረጃዎች አሳልፈው ይሰጣሉ።

ማንነትዎን እና የስፍራ አድራሻዎን መደበቅ የሚፈልጉ ከኾነ ፎቶዎችን ከመለጠፍዎ በፊት ሜታ ዳታውን ከፎቶዎቹ ላይ ሙሉ በሙሉ ማጥፋትዎን ያረጋግጡ።

በሌላ ኹኔታዎች ውስጥ ደግሞ ሜታ ዳታዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ስለመሳተፍዎ እውነተኛነት ለማረገጋጥ እንደ ማስረጃ ሊጠቅሙ ይችላሉ። የዘ ጋርዲያን ፕሮጀክት ኢንፎርማካም የተሰኘ ሜታ ዳታዎችን ከተጠቃሚዎች መረጃ ማለትም የGPS ኮርድኔትን፣ ከፍታን፣ የኮምፓስ አቅጣጫን፣ የብርሃን መጠን ንባብን፣ በአካባቢው የነበሩ ሌሎች መሳሪያዎች ምልክትን፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ ምሶሶዎችን፣ እና የWiFi መረቦችን መመዝገብ የሚችል መሳሪያ ሰርቷል። ይህም የዲጂታል ፎቶው የተቀረጸበትን ኹኔታ እና አውድ በገሀድ ያሳያል።