Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ

ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ እንድ መልዕክት በላኪው ወደ ሚስጥራዊ መልዕክት መቀየሩን እና በተቀባዩ ብቻ መፈታት መቻሉን የሚያረጋግጥ ስርዓት ነው። ሌሎች የምስጠራ ዓይነቶች በሦስተኛ ወገን የሚደረግ ምስጠራ ላይ የተመሰረቱ ሊኾኑ ይችላሉ። ይህ ማለት አመስጣሪዎቹ አካላት በዋናው መልዕክት መታመን አለባቸው ማለት ነው። ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ አብዛኛውን ጊዜ ደህንነቱ የተሻለ እንደኾነ ይታሰባል። ምክንያቱም ምስጠራውን መስበር ወይም ጣልቃ መግባት የሚችሉ አካላትን ቁጥር በመቀነሱ ነው።