የጋዜጠኝነት ትምህርት ተማሪ ነዎት?
በጋዜጠኝነት ትምህርት ቤትዎ ያልተማሯቸው የመስመር ላይ ደህንነት ትምህርቶች።
በጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ውስጥ በርካታ ቁም ነገሮችን የተማሩ ቢኾኑም ራስን ከስለላ እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ትምህርቱ ላያካትት ይችል ይኾናል። ለስለላ ተጋላጭነትን ለመመዘን እና ራስዎን እንዴት መከላከል እንዳለብዎት ለመማር ይህንን የጫኑ። ይህ ስብስብ ስጋትዎትን እንዲረዱ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት እንዲያደርጉ ፣ የመስመር ላይ ማንነትዎን እና መረጃዎችዎን እንዲጠብቁ እንምዲሁም የበይነ መረብ እገዳዎችን እንዴት ማለፍ እንደሚችሉ ያስተምርዎታል።