Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የዋትስአፕ አጠቃቀም በአንድሮይድ

Last Reviewed: May 09, 2018

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

የዋትስአፕ ግንኙትዎን ደኅንነት የበለጠ እንዲጠበቅ  ከዚህ በታች እንደተገለጸው ቅንብሮችዎን እንዲቀይሩ(እንዲሁም እውቂያዎችዎ ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ እንዲጠይቁ!) አጥብቀን እናበረታታለን፡፡

በተለይ በነሐሴ 2008 ዓ.ም. ይፋ የተደረገው ለእናት ድርጅቱ ፌስቡክ መረጃ ማጋራትን የሚፈቅደው አዲሱ የግለኝነት ፖሊሲው ያሳስበናል፡፡ ይህ ፌስቡክን በርካታ የተጠቃሚዎችን መረጃ፣ የዋትስአፕ ስልክ ቁጥር እና ዋትስአፕ በመጠቀም ሂደት ያከማቸውን መረጃ ጨምሮ እንዲያገኝ ይፈቅዳል፡፡

ቀድመው ዋትስአፕን መጠቀም ለጀመሩ ተጠቃሚዎች የግለኝነት ፖሊሲው ፌስቡክ ከዋትስአፕ ባገኘው መረጃ መሠረት ጓደኛ እንዳይጠቁም ወይም የማስታወቂያ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚከልክል ቅንብር የሚያደራጁበት ጊዜ ይሰጣል፡፡ አዲስ ተጠቃሚዎች ግን እንዲዚህ አይነቱን የተለጠጠ የራሳቸው መረጃ ካለፈቃዳቸው መጠቀምን አንፈልግም የሚሉበት ዕድል የላቸውም ፡፡ ለአዲስ ተጠቃሚ ያለው ብቸኛ አማራጭ የመረጃ ማጋራትን በሚፈቅደው አዲሱ የግለኝነት ፖሊስ ስር ዋትስአፕን መቀላቀል ነው፡፡ ምንም እንኳን ኩባንያው መረጃውን በቀጥታ ለማስተዋወቂያ አገልግሎት እንደማያጋራ ለተጠቃሚዎች ቢገልጽም ይህ ሂደት ግን በግልጽ አስጊ ነው፡፡ ስጋት ለተጠቃሚዎች የዋትስአፕ መረጃቸው እንዴት እንደሚጋራ እና ጥቅም ላይ እንደሚውል፡፡

በተጨማሪ የሚያሳስበን የዋትስአፕ ድር መተግበሪያ ነው፡፡ ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች መልዕክቶች መላክ እና መቀበል የሚስችል HTTPSደኅንነቱ የተጠበቀ የድር በይነገጽ አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ነገር ግን በሁሉም ድረገጾች እንደተለመደው መተግበሪያውን ለመጫን የሚያስፈልጉ ነገሮች ገጹን በጎበኙ ቁጥር ይወርዳሉ፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ድረገጹ የምስጠራ ድጋፍ ቢኖረውም በማንኛውም የገጽ ጭነት የመካነ ድሩ መተግበሪያ በቀላሉ ወደ ጎጂነት ያለው የመተግበሪያ አይነት ይቀየራል፤ ይህም ሁሉንም መልዕክቶች ወደ ሦስተኛ አካል ለማቅረብ ያስችለዋል፡፡

ዋትስአፕ በመጀመሪያ ላኪው መልዕክቱን ወደሚስጥራዊ መልዕክት የሚቀየርበት፣ በመጨረሻ በተቀባዩ ብቻ የሚፈታ፣ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አገልግሎት እስካሁን ይሰጣል፡፡ ይህ ምስጠራ በሚካሄድበት መንገድ ላይ ምንም የምንለው የለንም፡፡የሚጠቀመው የምስጠራ ፕሮቶኮል፣ ሲግናል ፕሮቶኮል ወደፊት የበለጠ ይስፋፋል ብንል ተስፋ እናደርጋለን፡፡.ነገር ግን የሲግናል ፕሮቶኮል ምርጥ ጥረት እንዳለ ሆኖ የዋትስአፕ ደኅንነት ግን ያሳስበናል፡፡

ካሁን በኋላም ዋትስአፕን መጠቀም ከወደዱ ከዚህ በታች ያለውን የአጠቃቀም መመሪያ ይመልከቱ፡፡ እናም በርቀት ምትክ ሰነድ ማስቀመጫን ያጥፉ፤ ጣት አሻራ ለውጥ ማሳወቂያዎችም እንዲደርስዎት ያድርጉ (ተጨማሪ የደኅንነት ጥንቃቄዎች ቅንበር ክፍልን ይመልከቱ)፡፡

የማውረጃ ስፍራ: መተግበሪያውን ከጎግል ፕለይ ግምጃ ማውረድ ይቻላል፡፡

አስፈላጊ ቅድመ ኹኔታዎች: አንድሮይድ 2.1 ወይም ከዚያ በላይ፣ ታብሌት መገልገያዎች ይህን አገልግሎት አይሰጡም፡፡

በዚህ መርጃ ጽሑፍ የተጠቀምነው ዝርያ: 2.16.13

ፈቃድ: ንብረትነቱ

ተጨማሪ ንባብ:

ደረጃ: ጀማሪ-መካከለኛ

የሚወስደው ጊዜ: ከ15-20 ደቂቃ

ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ ግንኙነት እንዲያደርጉ የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡ ተጠቃሚዎች ይህንን ተጠቅመው ደኅንነታቸው ተጠብቆ መደዋወል እና መጻጻፍ እንዲችሉ፣ ሰነድ እንዲላላኩ እና በቡድን ውይይት እንዲሳተፉ ያስችላል፡፡ ምንም እንኳን ዋትስአፕ የስልክ ቁጥሮችን እንደ እውቂያዎች ቢጠቀምም ስልኮች የሚደወሉት እና መልዕክቶች የሚላኩት የውሂብ ግንኙነት በመጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም በንግግሩ የሚሳተፉ አካላት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡በዚህ ምክንያት የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ለዚህ አይነት ንግግሮች፣ የአጭር የጽሑፍ መልዕክቶች እና የህብር ሚዲያ መልዕክቶች ክፍያዎች አይጠየቁም፡፡

ዋትስአፕ ንብረትነቱ የፌስቡክ ነው፡፡ መተግበሪያው ራሱ ምንጨ-ዝግ ሶፍትዌር ነው፡፡ ያ ማለት ከኩባንያው ውጭ ለሚገኝ ባለሙያ ኩባንያው ምስጠራውን ደኅንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማድረጉን ማረጋገጥ እጅግ አስቸጋሪ ነው ማለት ነው፡፡ ይሁንና ዋትስአፕ የተመሰጠሩ መልዕክቶችን ለመላክ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ለህዝብ ግልጽ የሆነ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡

በአንድሮይድ ስልክዎ ዋትስአፕ መጫን anchor link

ቅደም ተከተል 1: ዋትስአፕን በማውረድ ስልክዎ ላይ መጫን anchor link

በአንድሮይድ ስልክዎ ጎግልፕለይ ግምጃ በመግባት "WhatsApp." የሚለውን ይፈልጉ፡፡ ዋትስአፕ ሜሰንጀር በዋትስአፕ አይኤንሲ የሚለውን መተግበሪያ ይምረጡ፡፡

"Install," የሚለውን ከተጫኑ በኋላ ዋትስአፕ ሥራውን ለመጀመር መጠቀም የሚፈልጋቸው አንድሮይድ ክንውኖች ዝርዝር ይመለከታሉ፡፡ "Accept." የሚለውን ይጫኑ፡፡

ዋትስአፕ ወርዶ ሲጨርስ መተግበሪያውን ለማስጀመር "Open" የሚለውን ይንኩ፡፡

ቅደም ተከተል 2: ስልክ ቁጥርዎን ያስመዝግቡ እና ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ anchor link

በመጀመርያ የዋትስአፕን የአገልግሎት ውል እና የግለኝነት ፖሊሲ መቀበል ይኖርብዎታል፡፡

ዋትስአፕ በእርስዎ ስልክ የተመዘገቡ ወዳጆችዎን መረጃ ለማግኘት ይጠይቃል፡፡ እርስዎ ይህንን ከፈቀዱ ዋትስአፕ የእውቂያዎችዎን ዝርዝር በሙሉ ይወስዳል፡፡ ካልፈቀዱ ደግሞ ወዳጅዎችዎን አንድ ባንድ በማስገባት በጽሑፍ መወያየት ይችላሉ ነገር ግን ዋትስአፕ የወዳጆችዎን ዝርዘር እንዲያገኝ ሳይፈቅዱ አዲስ ጥሪ ማድረግ አይችሉም፡፡ ፎቶዎችን፣ የሚዲያ ውጤቶችን ወይም ሰነዶችንም መላክ ከፈለጉ ዋትስአፕ እነዚህን ፋይሎች ለማግኘት ፍቃድ ይጠይቃል፡፡

ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው መፍቀድ ከፈለጉ "Continue,"ከዚያም "Allow" የሚለውን ይንኩ፡፡

ይህንን የሚመስል ሠሌዳ ይመለከታሉ:

ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡና ወደቀኝ የተቀሰረውን ቀስት ይጫኑ፡፡ ከዚያም የማረጋገጫ ጽሑፍ ይመለከታሉ:

ስልክ ቁጥርዎን ለማረጋገጥ "OK." የሚለውን ይጫኑ፤ ስድስት አሃዞች ያሉት ኮድ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ይላክልዎታል፡፡ በዚህ ሰዓት ዋትስአፕ የአጭር የጽሑፍ መልዕክቶችዎን ማግኘት እንደሚፈልግ የሚገልጽ መልዕክት ይመለከታሉ፡፡ "Allow," የሚለውን ከተጫኑ ዋትስአፕ ወዲያውኑ በራሱ የተቀበሉትን ኮድ ያነባል ምዝገባውም ይፈጸማል፡፡ "Deny," የሚለውን ከተጫኑ ደግሞ በራስዎ የተላከልዎትን ኮድ ማግኘት ከዚያም ይህን በሚመስል ቦታ ላይ ማስገባት ይጠበቅብዎታል:

በሚቀጥሉት ሠሌዳዎች ምትክ ሰነዶችን በጎግል ድራይቭ ማስቀመጥ እንደሚፈልጉ ይጠየቃሉ፡፡ ያልተመሰጠሩ ምትክ ሰነዶች ወደ ጎግል አለመላካቸውን እርግጠኛ ለመሆን "Never" የሚለውን ይምረጡ ከዚያም "Done." የሚለውን ይጫኑ፡፡

የዋትስአፕ አጠቃቀም anchor link

ዋትስአፕን ለመጠቀም መልዕክት የሚልኩለት ወይም የሚደውሉለት ሰው ዋትስአፕ መተግበሪያን እንደእርስዎ በስልኩ ላይ መጫን አለበት፡፡

አዲስ የተመሰጠረ ንግግር ሲጀመር የሚከተለውን ማሳወቂያ ይመለከታሉ: "Messages you send to this chat and calls are now secured with end-to-end encryption. Tap for more info." በዚህ ጊዜ መተግበሪያው ሲወርድ ( ቁልፍ ማረጋገጫ የተባለ ሂደት) እንዳልተቀየጠ ወይም ከሌላ ሰው ቁልፍ ጋር እንዳልተቀያየረ በመረዳት እየተነጋገሩት ያለው ሰው በትክክል ራሱ መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ማረጋገጫው እየተነጋገሩ ያለው ሰው በአካል ሲኖር የሚደረግ የማረጋገጥ ሂደት ነው፡፡ ይህንን ማሳወቂያ [1] መጫን ይችላሉ ወይም ራስዎ ከሠሌዳው አናት ላይ ያለውን (በቁመት የተደረደሩ ሦስት ነጥቦች) [2] ሜኑ በመጫን እውቂያዎን ማየት ይችላሉ፤ ከዚያም "view contact"[3] የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል ቀጥሎ በሚመጣው ሠሌዳ ላይ የሚገኘውን አረንጓዴ ቁልፍ[4] ይጫኑ:

ወዳጅዎም በስልካቸው በተመሳሳይ ተመሳሳይ ሂደት ሲከተሉ የሚከተለው ሠሌዳ ይመለከታሉ "Verify security code":

የስልሳ አሃዞች ቅጥልጥል ይመለከታሉ፡፡ እነዚህን ቁጥሮች አንድ በአንድ በመናበብ እና ከወዳጅዎ ቁጥሮች ጋር በተጓዳኝ በማስተያየት ወይም በዚህ ሠሌዳ ላይ ያለውን ኪው አር ኮድ በመቅረጽ ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

ለሌላኛው ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ማረጋገጫ መንገድ ቁጥሮቹን ፎቶ በመንሳት በሌላ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደ ባለ መንገድ ማጋራት ነው፡፡

አንዴ እንደዚህ ካደረጉ በኋላ ከዚህ ወዳጅዎ ጋር የሚያርጉት የተመሰጠረ ግንኙነት የሚታየው በእርስዎ እና በወዳጅዎ ብቻ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡ ይህ ለዋትስአፕ የጽሑፍ መልዕክቶች እና ለዋትስአፕ የድምጽ ደውሎች ለሁለቱም ይሰራል፡፡

ተጨማሪ የደኅንነት ቅንብሮች anchor link

ደኅንነት ማሳወቂያዎችን አሳይ anchor link

ከላይ እንደተገለጸው በማንኛውም ምክንያት የወዳጅዎችዎን የምስጠራ ቁልፍ ከተለወጠ ስለዚህ ለውጥ ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል፡፡

በመደበኛነት የቁልፍ መለዋወጥ እንደችግር የሚታይ አይደለም፤ ይህ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተው መተግበሪያው እንደገና ሲጫን ወይም የስልኮች መቀያየር ሲኖር ነው፡፡ ነገር ግን በመሃከል ያለ ሦስተኛ ሰው በተንኮል ቁልፍ ሊቀይር የሚችልበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ በዚህ ምክንያት የወዳጅዎችዎ ቁልፍ ሲቀየር እንደገና ማረጋገጥ (ከላይ እንደተገለጸው) ጥሩ ልምድ ነው፡፡ በዋናነት ዋትስአፕ የዕውቂያዎች ቁልፍ ለውጥ ሲኖር አያሳይም፡፡ ይህንን ለማስጀመር ወደ ቀንብር ይግቡና ይህንን ሂደት ይከተሉ Settings → Account → Security እና 'Show security notifications' የሚለውን ወደቀኝ ያንሸራትቱ:

ጎግል ድራይቭ ምትክ ሰነድ anchor link

በተጨማሪም ከላይ እንደተገለጸው ምናልባትም ያልተመሰጠሩ ምትክ ሰነዶች ወደ ጎግል አለመላካቸውን እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ፡፡

ክላውድ ምትክ ሰነድ አለማስቀመጡን እርግጠኛ ለመሆን ቅንበር ወስጥ Settings → Chats → Chat Backup ብለው ይፈልጉ፡፡ "Back Up to Google Drive" በሚለው ስር "Never"ን ይምረጡ: