ጠንካራ የይለፍ ቃሎችን መፍጠር
Last Reviewed: February 02, 2021
የይለፍ ቃል አቀናባሪዎችን በመጠቀም ጠንካራ የይለፍ ቃል መፍጠር anchor link
የይለፍ ቃላትን ደጋግሞ መጠቀም በጣም መጥፎ የሚባል ደኅንነት ልማድ ነው። ምክንያቱም አጥቂው የተለያዩ አገልግሎቶች ላይ ደጋግመው የተጠቀሙትን አንድ የይለፍ ቃልን ካገኘ ብዙ መለያዎችዎን ሊያዳርስ ይችላል፡፡ ለዚህ ነው ብዙ፣ ጠንካራ፣ ልዩ የይለፍ ቃላትን ማግኘት በጣም አስፈላጊ የሆነው፡፡
እንደ መታደል ሆኖ የይለፍ ቃል አቀናባሪ ሊረዳዎ ይችላል፡ የይለፍ ቃል አቀናባሪ ለእርስዎ የይለፍ ቃላትን መፍጠር እና ማከማቸት የሚችል መሣሪያ ነው፡፡ ስለዚህ በርካታ የተለያዩ የይለፍ ቃላትን ማስታወስ ሳይጠበቅብዎ በተለያዩ መካነ ድሮች እና አገልግሎቶች መጠቀም ይችላሉ:
- የሰው ልጅ ሊገምተው የማይችል ጠንካራ የይለፍ ቃል ያመንጩ፡፡
-
በርካታ የይለፍ ቃላትን (እና ለደህንነት ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሾች) በጥንቃቄ ያከማቹ፡፡
-
ሁሉንም የይለፍ ቃላትዎን በአንድ ዐብይ የይለፍ ቃል (ወይም የይለፍ ሐረግ) ይጠብቁ፡፡
ኪፓስኤክስሲ ክፍት ምንጭ እና ነፃ የሆነ የይለፍ ቃል አቀናባሪ ምሳሌ ነው፡፡ ይህን መሣሪያ በዴስክቶፕዎ ላይ ማስቀመጥ ወይም በድር አሳሽዎ ውስጥ ሊያዋህዱት ይችላሉ፡፡ ኪፓስኤክስሲ ሲጠቀሙ የሚወስዷቸውን ለውጦች በቀጥታ አያስቀምጥም፡፡ ስለዚህ አንዳንድ የይለፍ ቃሎችን ካከሉ በኋላ አገልግሎቱን ካቋረጠ ለዘለቄታው ሊያጧቸው ይችላሉ፡፡ ይህንን በቅንብሮች ውስጥ መቀየር ይችላሉ፡፡
የይለፍ ቃል አቀናባሪ ለእርስዎ ትክክለኛ መሣሪያ ስለመሆኑ ጥርጣሬ ያድርብዎታል? እንደ መንግስት ኃይለኛ የሆነ ባለጋራ እርስዎን ለማጥቃት ካቀደ ምናልባት ላይሆን ይችላል፡፡
ያስታውሱ:
-
የይለፍ ቃል ማቀናበሪያን መጠቀም አንድ ክፍተትን ይፈጥራል::
-
የይለፍ ቃል ማቀናበሪያዎች የባለጋራዎች ግልጽ የሆኑ ኢላማዎች ናቸው.
-
ምርምሮች የይለፍ ቃል ማቀናበሪያዎች ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን ይጠቁማሉ፡፡
ውድ ስለሆኑ የዲጂታል ጥቃቶች ከተጨነቁ በቴክኒክ ብዙም ያልረቀቁ ነገሮች ለመጠቀም አብልጠው ያስቡ፡፡ በቀላሉ (ከታች << ዳይስን በመጠቀም ጠንካራ የይለፍ ቃላትን በመፍጠር >> የሚለውን ይመልከቱ) ጠንካራ የይለፍ ቃል መፍጠር ይችላሉ፡ ይፃፉት እና ደኀንነቱ የተጠበቀ ቦታ ላይ ያስቀምጧቸው፡፡
ይቆዩ፣ የይለፍ ቃላት በአእምሮ ብቻ የሚታወሱ ነገር ግን የማይጻፉ ናቸው ብለን እናስባለን? እርግጥ ነው በጽሑፍ ማኖር እና እንደ ኪስ ቦርሳዎ ያለ ቦታ ውስጥ ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው፡፡ ቢያንስ የጻፉት የይለፍ ቃላት የጠፉ ወይም የተሰረቁ እንደሆነ ማወቅ ይቻላሉ፡፡
ዳይስን በመጠቀም ጠንካራ የይለፍ ቃላትን መፍጠር anchor link
በጣም ጠንካራ መሆን የሚያስፈልጋቸው እና ማስታወስ የሚገባዎ ጥቂት የይለፍ ቃላት አሉ፡፡ እነዚህም:
- የመሣሪያዎ የይለፍ ቃላት
- የምስጠራ የይለፍ ቃላት (እንደ ሙሉ-ዲስክ ምስጠራ )
- የይለፍ ቃል ማቀናበሪያዎዐብይ የይለፍ ቃል, ወይም “የይለፍ ሀረግ”
- የኢሜይልዎ የይለፍ ቃል
ሰዎች የይለፍ ቃላትን ሲመርጡ ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች ውስጥ አንዱ ሊተነበቡ የማይችሉ ምርጫዎች በማድረግ በጣም ጥሩ አለመሆናቸው ነው፡፡ ጠንካራ እና የማይረሳ የይለፍ ቃል ለመፍጠር ውጤታማ መንገድ ዳይስን እና በዘፈቀደ የተመረጡ የቃላት ዝርዝርን መጠቀም ናቸው፡፡ እነዚህ ቃላት አንድ ላይ በመሆን "የይለፍ ሐረግ"ዎን ይመሰርታሉ፡፡ "የይለፍ ሐረግ" ለተጨማሪ ደህንነት ሲባል ረጅም የሚደረግ የይለፍ ቃል አይነት ነው፡፡ ለዲስክ ምስጠራ እና የይለፍ ቃል ማቀናበሪያዎ ቢያንስ ስድስት ቃላትን እንዲመርጡ እንመክራለን፡፡
ለምን በትንሹ ስድስት ቃላት እንዲጠቀሙ ይመከራሉ? በሀረግ ውስጥ ያሉትን ቃላት በዘፈቀደ ለመምረጥ ለምን ዳይስ እንጠቀማለን? የይለፍ ቃሉ የበለጠ በረዘመ ቁጥር እና በዘፈቀደ ሲመረጥ ለሰዎችም ሆነ ለኮምፕዮተሮች ለመገመት የበለጠ አስቸጋሪ ይሆናሉ፡፡ ለምን ለመገመት አስቸጋሪ የይለፍ ቃል እንሚያስፈልግዎ ለመረዳት የቪዲዮ ማብራሪያ rእዚህ ይገኛል፡፡
ከኢኤፍኤፍ የቃላት ዝርዝርመካከል የይለፍ ሀረግ ለመመስረት ይሞክሩ፡፡
ኮምፒውተርዎ ወይም መሣሪያዎ ጥቃት ከደረሰባቸው እና የስለላ ሶፍትዌር ከተጫነባቸው፣ የስለላ ሶፍትዌሩ የእርስዎን ዐብይ የይለፍ ቃል ሊመለከት እና የይለፍ ቃል ማቀናበሪያውን ይዘት ሊሰርቅ ይችላል፡፡ ስለዚህ የይለፍ ቃል ማቀናበሪያን ሲጠቀሙ ኮምፒውተርዎን እና ሌሎች መሣሪያዎችዎን ከሸረኛ ሶፍትዌር በጥንቃቄ መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
ጥቂት ስለ “ደህንነት ጥያቄዎች” anchor link
መካነ ድሮች ማንነትዎን ለማረጋገጥ የሚጠቀሙባቸው "የደህንነት ጥያቄዎች" ሲመልሱ ጥንቃቄ ያድርጉ:: ለእነዚህ ጥያቄዎች በቅንነት የሚሰጡ ምላሾች ብዙዉን ጊዜ በይፋ ሊታወቁ የሚችሉ እውነታዎች ሲሆኑ የቆረጠ ባለጋራ በቀላሉ ሊያገኛቸው እና የይለፍ ቃልዎን ሰብሮ በመግባት ሊጠቀምባቸው ይችላል ፡፡
ይልቁንስ ከእርሶ በቀር ማንም የሚያውቀው የውሸት መልሶች ይስጡ፡፡ ለምሳሌ የደህንነት ጥያቄው እንዲህ ከሆነ:
“የመጀመሪያው የቤት እንስሳዎ ስም ማን ነበር?”
የእርስዎ መልስ በይለፍ ቃል አቀናባሪዎ አማካኝነት በዘፈቀደ የተፈጠረ የይለፍ ቃል ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህን ሚስጥራዊ መልሶች በይለፍ ቃል አቀናባሪዎ ውስጥ ማከማቸት ይችላሉ፡፡
የደህንነት ጥያቄዎችን የተጠቀሙባቸው መካነ ድሮች እና የሰጡትን ምላሾች ያስቡ፡፡ በተለያዩ መካነ ድሮች ወይም አገልግሎቶች ላይ ለበርካታ መለያዎች የተመሳሳይ የይለፍ ቃሎች ወይም የደህንነት ጥያቄዎችን አይጠቀሙ፡፡
የይለፍ ቃላትዎን በበርካታ መሳሪያዎችዎ ላይ ማመሳሰል anchor link
ብዙዎቹ የይለፍ ቃላት አቀናባሪዎች የይለፍ ቃላትዎን በመሳሪያዎች በኩል በይለፍ ቃል ማመሳሰል አገልግሎት አማካኝነት እንዲደርሱባቸው ያስችላሉ፡፡ ይሄ ማለት አንድ የይለፍ ቃልዎን በአንድ መሣሪያ ላይ ሲያሻሽሉ በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ ይመሳሰላል፡፡
የይለፍ ቃል አቀናባሪዎች የይለፍ ቃልዎን «በደመና ውስጥ» ይህም ማለት በርቀት ሰርቨር ላይ አመስጥረው ሊያከማቹ ይችላሉ፡፡ የይለፍ ቃላትዎን ሲፈልጉ እነዚህ አቀናባሪዎች ወዲያውኑ የይለፍ ቃሉን መልሶ በማውጣት ምስጠራውን ፈተው ያቀርባሉ፡፡ የይለፍ ቃላትን ማመሳሰል እና ለማከማቸት የራሳቸውን ሰርቨር የሚጠቀሙ የይለፍ ቃል አቀናባሪዎች የበለጠ ምቹ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚያው መጠን ለጥቃቶች የተጋለጡ ናቸው፡፡የይለፍ ቃላትዎ በኮምፒተርዎ እና በደመና ውስጥ ከተከማቹ አንድ አጥቂ የይለፍ ቃላትዎን ለማግኘት ኮምፒተርዎን መውሰድ አይኖርበትም፡፡(ነገር ግን የይለፍ ቃል አቀናባሪዎን የይለፍ ሐረግ ሰብረው ማግባት አለባቸው፡፡)
ይሄ የሚያሳስብዎ ከሆነ የይለፍ ቃላትዎን ደመና ላይ እንዲከማች(እንዲመሰሳሰል) አይፍቀዱ፤ በእርስዎ መሣሪያዎች ላይ ማከማቸትን ይምረጡ፡፡
ለማንኛውም የይለፍ ቃል ውሂብዎን ምትክ ፋይል ያስቀምጡት፡፡ የመጠባበቂያ ቅጂው ጠቃሚ የሚሆነው የይለፍ ቃል ማጠራቀሚያው ቢበላሽ ወይም ምናልባት መሣሪያዎ ቢሰረቅ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የይለፍ ቃል አቀናባሪዎች ምትክ ፋይል የሚያስቀምጡበት መንገድ አላቸው፤ ወይም መደበኛ የመጠባበቂያ ፕሮግራምዎን መጠቀም ይችላሉ፡፡
ባለ ብዙ-ደረጃ ማረጋገጫ እና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃላት anchor link
ጠንካራ እና ልዩ የይለፍ ቃላት እኩይ አካላት የእርስዎን መለያዎች ጋር ለመድረስ የሚያረጉትን ጥረት ይበልጥ ከባድ ያደርጋሉ፡፡ መለያዎችዎን የበለጠ ለመከላከል ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ ይጠቀሙ፡፡
አንዳንድ አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ወደ መለያቸው መግባት እንዲችሉ ሁለት ደረጃ ያለው (የይለፍ ቃል እና ሁለተኛ ደረጃ) እንዲኖራቸው የሚያስችላቸው ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን (ሁለት እሴት፣ ባለብዙ-ማረጋገጫን ማረጋገጥ ወይም ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫን) ያቀርባሉ፡፡ ሁለተኛው ነገር በሞባይል መሳሪያ በሚንቀሳቀስ ፕሮግራም አማካኝነት የመነጨ የአንድ ጊዜ ብቻ የሆነ ሚስጢራዊ ኮድ ወይም ቁጥር ሊሆን ይችላል፡፡
ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ በሞባይል ስልክ አማካኝነት በሁለት መንገድ ሊከናወን ይችላል:
- በስልክዎ የደህንነት ኮዶችን የሚፈጥሩ (እንደ ጎግል አውተንቲከተር ወይም አዉቲ ) ያሉ ማረጋገጫ መተግበሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ ወይም ለብቻቸው ያሉ እንደ ዩቢኪይ ያሉ መሳሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ፤ ወይም
- አገልግሎቱ ወደመለያዎ መግባት በሚፈልጉበት ጊዜ የሚተይቡት ተጨማሪ የደህንነት ኮድ የያዘ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ሊልክልዎ ይችላል፡፡
የመምረጥ ዕድል ካልዎት ባለጋራ ወደስልኩ ሊያስተላለፈው ከሚችለው ከአጭር የጽሑፍ መልዕክት ይልቅ አልፎ ለመግባት አስቸጋሪ የሆነውን የማረጋገጫ መተግበሪያ ወይም ብቻውን ያለ መሣሪያን ይምረጡ፡፡
እንደ ጎግል ያሉ አንዳንድ አገልግሎቶች የአንድ-ጊዜ የይለፍ ቃላት መፍጠር ይፈቅዳሉ፡፡ እነዚህም በወረቀት ላይ አትመው ወይም ወይም ጽፈው ይዘዋቸው ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የይለፍ ቃሎት አንድ ጊዜ ብቻ ይሰራሉ፡፡ ስለዚህ ሰላይ ሶፍትዌሮችን ተጠቅሞ መስረቅ ቢችል እንኳን ሌባው ለወደፊቱ ሊጠቀምበት አይችልም፡፡
አንዳንድ ጊዜ የይለፍ ቃልዎን መግለጥ ይኖርብዎታል anchor link
የይለፍ ቃላትን ለመግለጽ የተደነገጉ ሕጎች ከቦታ ቦታ ይለያያሉ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ይለፍ ቃልን አልሰጥም ብለው በህግ መከራከር ይችሉ ይሆናል፡፡ በአንዳንድ አከባቢያዊ ህጎች ደግሞ መንግስት የይለፍ ቃልን የመጠየቅ መብት ይሰጣ፡፡ እንዲውም ቁልፍ ወይም የይለፍ ቃል እንደሚያውቁ ከጠረጠረ መንግስት እርስዎን ማሰር እንዲችል ይፈቅዳሉ፡፡ አካላዊ የማሰቃየት ተግባር እንደሰው የይለፍ ቃሉን እንዲሰጥ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ወይም እራስዎን ድንበር አቋርጠው ሲያልፉ የይለፍ ቃልዎን አልሰጥም በማለትዎ ባለስልጣናት መሣሪያዎን ሊወርሱ ወይም ሊያዘገዩ የሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሊገኙት ይቻላሉ፡፡
ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ወይም ከአሜሪካ ሲወጡ ማሣሪያዎን ከፍቶ ለመግባት የሚቀርብ ጥያቄን እንዴት ማስተናግድ እንደሚገባዎ የሚገልጽ የተለየ የዩናይትድ ስቴትስ ድንበሮችን ለሚያያቋርጡ መመሪያ አዘጋጅተናል፡፡ በሌሎች ሁኔታዎች አንድ ሰው እርስዎ ወይም ሌሎች ሰዎችን እንዴት የይለፍ ቃላትን እንዲሰጡ ያስገድዳል የሚለውን ማስብ እና መልሱን ተክትሎ የሚመጣውን ውጤት ማሰብ አለብዎት፡፡