Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የቁልፍ ማረጋገጫ

በአደባባይ ቁልፍ ስነመሰውር እያንዳንዱ ግለሰብ የቁልፎች ስብስብ አለው። ደህንነቱ የተጠበቀ መልዕክት ለመላክ የሚላክለትን ሰው ቁልፍ በመጠቀም መልእክቱን ያመሰጥሩታል። አጥቂዎች የእነርሱን ቁልፍ እንዲጠቀሙ ሊያታልሉዎት ይችላሉ። ይህ ማለት በታቀደለት ተቀባይ ፋንታ የላኩትን መልዕክት አጭበርባሪዎች ማንበብ ይችላሉ ማለት ነው። ይህ እንዳይከሰት የኾነ ቁልፍ በአንድ ግለሰብ ጥቅም ላይ እንደሚውል ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። የቁልፍ ማረጋገጫ አንድ ቁልፍን ከአንድ ግለሰብ ጋር የሚያዛምዱበት ማንኛውም ዓይነት መንገድ ነው።