Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የቁልፍ መለዋወጫ ድግስ

የአደባባይ ቁልፍ ምሰጠራን ሲጠቀሙ መልዕክቱን ለማመስጠር የሚጠቀሙት ቁልፍ ባለቤትነቱ የመልዕክቱ ተቃባይ መኾኑን እርግጠኛ መኾን ይኖርብዎታል (የቁልፍ ማረጋገጫን ይመልከቱ)። ለእዚህ ሂደት PGP የማቃለያ መንገድ አለው። ይህም ‘ይህ ቁልፍ ባለቤትነቱ የእዚህ ግለሰብ ነው ብዬ አምናለሁ እና እርስዎ የሚያምኑኝ ከኾነ እርስዎም ይህንኑ ይቀበሉ’። የአንድን ግለሰብ ቁልፍ ይህ ነው ብሎ በአደባባይ ማወጅ ‘ቁልፋቸውን መፈረም’ ይባላል። ይህ ማለት ማንኛውም ቁልፉን የሚጠቀም ሰው እርስዎ ስለቁልፉ ያወጁትን ይመለከታል ማለት ነው። ሁሉም ሰው እርስ በእርሱ ቁልፉን እንዲያረጋግጥ ለማበረታት የ PGP ተጠቃሚዎች የቁልፍ መፈረሚያ ድግሶች ያዘጋጃሉ። ድግሶቹ ድግስ ቢኾኑም እንደ ስማቸው የሚያስደስቱ አይደሉም።