Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የደህንነት ጥያቄ

የማለፊያ ቃሎችን ለማጠናከር አንዳንድ ስርዓቶች "የደህንነት ጥያቄዎችን" ይጠቀማሉ። እነዚህም እርስዎ ብቻ መልሳቸውል ሊያውቋቸው የተገቡ ጥያቄዎች ናቸው። የደህንነት ጥያቄዎች ችግር በጣም ሊገመት የሚችል መልስ ያላቸው ልክ እንደ ተጨማሪ የማለፊያ ቃሎች መኾናቸው ነው። የደህንነት ጥያቄዎችን እንደ ማንኛውም የማለፊያ ቃል እንዲቆጥሯቸው እንመክራለን። ጥያቄዎቹን ለመመለስ ረዥም፣ አዲስ፣ በዘፈቀደ የተፈጠረ ሐረግን ይፍጠሩ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ያስቀምጡት። ስለዚህ ባንክዎ የእናትዎን አባት ስም ሲጠይቅዎት ከ"ፈረስ ቤት ባትሪ ወንዝ" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ የኾነ በዘፈቀደ የፈጠሩትን መልስ ለመመለስ ይችላሉ።