የጣት አሻራ
የአደባባይ ቁልፍ ስነመሰውር ቁልፎች በጣም ረዥም ናቸው። አልፎ አልፎ በሺዎች የሚቆጠሩ ወይም የላቀ ርዝመት ያላቸው ሊኾኑ ይችላሉ። ከዚህ አንፃር የጣት አሻራ አነስተኛ ወይም የተወሰኑ የቁጥሮች እና የፊደሎች ስብስብን የያዘ ሲኾን የቁልፉን አሃዞች ሳይዘረዝሩ እንደ ተለየ የቁልፍ መጠሪያነት ሊያገለግል ይችላል። ለምሳሌ እርስዎ እና ጓደኛዎ ተመሳሳይ ቁልፍ እንዳላችሁ ለማረጋገጥ ብትፈልጉ በቁልፉ የሚገኙትን በሺዎች የሚቆጠሩ አሃዞች በማንበብ ብዙ ጊዜ ማጥፋትን ወይም በምትኩ ሁለታችሁም የቁልፉ የጣት አሻራን በማስላት የማነጻጸር ምርጫ አላችሁ። አብዛኛውን ጊዜ በስነመሰውር ሶፍትዌር የሚቀርቡ የጣት አሻራዎች ወደ 40 የሚጠጉ የፊደሎች እና የአሃዞች ስብስብን የያዘ ነው። የጣት አሻራው ተመሳሳይ እንደኾነ በጥንቃቄ ለማጣራት ከሞከሩ በመሃል ገብቶ በማስመሰል ሊያታልል ከሚሞክር አካል የተጠበቁ ኖዎት። አንዳንድ ሶፍትዌሮች የጓደኛን ቁልፍ ለማረጋገጥ እጅግ ምቹ የኾኑ አማራጮችን ሊሰጡ ይችላሉ። ነገር ግን የግንኙነት አገልግሎት አቅራቢዎች በቀላሉ ግንኙነቱን እንዳይሰሙ አንዳንድ የማረጋገጫ ዓይነቶች ይህን ስለላ መከላከል የሚችሉ መኾን ይኖርባቸዋል።