Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የድር ማሰሻ ማጥለያ ቅጥያ

አንድ ድረ ገጽን በሚጎበኙበት ወቅት የድር ማሰሻዎ ለድረ ገጹ አስተዳዳሪ አንዳንድ መረጃዎችን ይልካል። ለምሳሌ IP አድራሻን፣ ስለ ኮምፒውተርዎ አንዳንድ መረጃዎችን እና ይህንን የድር መዳሰሻ ተጠቅመው ያደረጓቸውን የቀድሞ ዳሰሳዎች የሚያያይዙ ኩኪዎችን ሊይዝ ይችላል። ድረ ገጹ ከሌላ የድር አገልጋይ የተወሰዱ ስእሎችን እና ይዘቶችን የሚጨምር ከኾነ ከእነዚህ ድረ ገጾች ላይ የኾነ ይዘትን እንዳወረዱ ወይም እንደጎበኙ የሚናገር ተመሳሳይ መረጃ ለእነዚህ ድረ ገጾች ይላካል። የማስታወቂያ መረቦች፣ ትንተና አቅራቢዎች እና ሌሎች ውሂብ ሰብሳቢዎች መረጃዎችን ከእርስዎ የሚሰበስቡት በዚህ መልክ ሊኾን ይችላል።

ከድር መዳሰሻዎ ጋር ጎን ለጎን የሚሠራ ተጨማሪ ሶፍትዌርን መጫን እና በዚህ መንገድ ለሶስተኛ ወገን የሚሾልከውን የመረጃ መጠን መቀነስ ይችላሉ። እጅግ በጣም ታዋቂ ምሳሌዎች ማስታወቂያን የሚያገዱ ፕሮግራሞች ናቸው። EFF ፕራይቬሲ ባጀር የተሰኘውን ሌላ የትራፊክ ማገጃ ቅጥያ መሣሪያን ይሰጣል።