Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ጸረ ቫይረስ

አንድ መሣሪያ በሸረኛ ሶፍትዌር (ወይም ማልዌር) ቁጥጥር ሥር እንዳይውል የሚከላከል ሶፍትዌር ነው። "ቫይረሶች" የመጀመሪያዎቹ እና በብዛት የሚገኙ የሸረኛ ሶፍትዌር ዓይነቶች ሲኾኑ ስያሜያቸው ከአንድ መሣሪያ ወደ ሌላ መሣሪያ የሚዘዋወሩበት መንገድን ያንጸባርቃል። በአሁኑ ሰዓት ያሉት ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ከሌላ ምንጭ የሚያወርዷቸውን ሰነዶች ከራሳቸው የሸረኛ ሶፍትዌር ጽንሰ ሃሳብ ጋር እያወዳደሩ እና እየገመገሙ ማስጠንቀቂያ የሚሰጡ ናቸው።

የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ሸረኛ ሶፍትዌሮችን የሚያውቁት ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሩን ያበለጸገው ግለሰብ ሲሰራቸው ሸረኛ ሶፍትዌሩን እንዲያውቁት የሚያደርግ የትንተና አቅም ሲፈጥርላቸው ነው። ይህም የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች አንድን ግለሰብ ወይም የተወሰኑ የማህበረሰብ አባላትን ለማጥቃት ኾን ተብሎ ታቅዶ የተሰራን ሸረኛ ሶፍትዌርን የመከላከል ውጤታማነታቸውን ይቀንሰዋል። አንድ አንድ በሳል ሸረኛ ሶፍትዌሮች የሚያጠቁት በንቃት ሲኾን ራሣቸውንም ከጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች መከላከል ይችላሉ።