Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የኮርፖሬት የውስጥ አውታረ መረብ ወይም ኔትወርክ

አብዛኛውን ጊዜ ትላልቅ ተቋማት እና ኩባንያዎች ከራሳቸው የውስጥ አውታረ መረብ የሚገኙ አገልግሎቶችን (ለምሳሌ የኢሜል፣ የድር፣ እና የሰነዶች እና የፕሪንተር) ይሰጣሉ። ነገር ግን እነኚህ አገልግሎቶች ከውስጥ አውታር ወጪ በኢንተርኔት ላይ ማግኘት አይቻልም። አብዛኞቹ ተቋማት ይህ የውስጥ ሰነዶቻቸውን ለመከላከል በቂ እንደኾነ ያስባሉ። ነገር ግን ከውስጥ ኔትወርክ ጋር መገናኘት የሚችል ማንኘውም አጥቂ በአካባቢው ያሉ ሰነዶችን ማግኘት ወይም ጣልቃ በመግባት መጥለፍ ይችላል። አንድ ሰራተኛን በላፕቶፑ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌርን እንዲጭን ማታለል የእዚህ ዓይነት ጥቃት ምሳሌ ሊኾን ይችላል። ተቋማት ሰራተኞቻቸው ኢንተርኔትን ተጠቀመው ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የውስጥ ኔትወርክ ላይ ያሉ ሰነዶችን እንዲያገኙ ሃሳባዊ የግል ኔትወርክ (VPN) አገልግሎትን ያቀርባሉ። ይህም ለመስሪያቤቱ የውስጥ ኔትወርክ ጥበቃን ይሰጣል።