ያልተማከለ አገልግሎትን የሚዘጋ ጥቃት
በተቀናጁ በርካታ ኮምፒውተሮች አማካኝነት የጥቃቱ ዒላማ ለኾነ ድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት ጥያቄ እና ዳታ በአንድ ግዜ ልኮ በማጨናነቅ ድረገጹን ከመስመር ውጪ እንዲኾን ማድረግ ነው። ለእንደዚህ ዓይነት አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒወተሮች አብዛኛውን ግዜ ከርቀት በወንጀለኞች ቁጥጥር ሥር ያሉ ናቸው። ወንጀለኞቹ እነዚህን ኮምፒውተሮች በቁጥጥር ሥር የሚያውሉት ሰብሮ በመግባት ወይም በሸረኛ ሶፍትዌሮች በመበከል ነው።