Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የአደባባይ ቁልፍ ምስጠራ

የተለምዶ የማመስጠሪያ ስርዓቶች መልዕክትን ለማመስጠር እና ለመፍታት ተመሳሳይ ምስጠራን ወይም ቁልፍን ይጠቀማሉ። ስለዚህ "bluetonicmonster" በሚል የማለፊያ ቃል ሰነድን ከተመሰጠረ እርስዎ ይህንን ለመፍታት ሰነዱን እና "bluetonicmonster" የሚለውን ምስጢር ማግኘት ይኖርብዎታል። የአደባባይ ቁልፍ ምስጠራ ሁለት ቁልፎችን ይጠቀማል።አንዱ ለማመስጠር የሚያገለግል ሲኾን ሌላኛው ደግሞ ምስጢሩን ለመፍታት ነው። ይህ በርካታ ጥቅሞች አሉት። አንደኛው ጥቅም ሰዎች የሚልኩልዎትን መልዕክቶች የሚያመሰጥሩበትን ቁልፍ መስጠት ይችላሉ (ሌላኛውን ቁልፍ በሚስጥር እስካቆዩ ድረስ)። እናም ይህ ቁልፍ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ከእርስዎ ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላል። ለሰዎች የሚሰጡት ቁልፍ "የአደባባይ ቁልፍ" ይባላል። የዚህም ዘዴ ስያሜ የመጣው ከዚህ ነው። የአደባባይ ቁልፍ ምስጠራ ኢሜሎች እና ፋይሎችን ለማመስጠር እጅግ መልካም የኾነ ግላዊነትን (PGP or Pretty Good Privacy)፣ ፈጣን የጽሁፍ መልዕክትን ለማመስጠር OTRን እና ለድር መዳሰሻዎች SSL/TLSን ይጠቀማል።