Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የአሜሪካን ድንበር ሲያቋርጡ ልብ ሊሏቸው የሚገቡ ነገሮች

Last Reviewed: October 29, 2018

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

በቅርቡ የአሜሪካንን ድንበር ማቋረጥ ያስባሉ? መንግሥት ያለ ምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ መንገደኛች አለም አቀፍ አውሮጵላን ጣቢያዎችን ጨምሮ በማንኛውም የአሜሪካ ድንበር ሲደርሱ የመፈተሽ ስልጣን እንዳለው ያውቃሉ? ይህ መንግስት በዝውውር ላይ ያሉ ነገሮችን የመቆጣጣር ተለምዷዊ ስልጣኑ አካል ነው። (ያስታውሱ ምንም እንኳ ሕጉ መንገደኞች ከአሜሪካ ወደ ሌላ አገር ሲሻገሩም በመውጫዎች ላይ እንደሚፈተሹ ቢደነግግም መንገደኞች ግን በብዛት ሲፈተሹ አይታይም።)

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በጥልቀት ለመረዳት ከፈለጉ የኢኤፍኤፍ መመሪያ የኾነውን ዲጂታል ግላዊነት በአሜሪካ ድንበር፣ በመሣሪያዎ ላይ ያለው ውሂብ መጠበቅ ይመልከቱ።

የአሜሪካን ድንበር ሲያቋርጡ ልብ ሊሏቸው የሚገቡ ነገሮችን እዚህ ይመልከቱ፦ anchor link

ድንበር ጠባቂዎች ዲጂታል ውሂብዎን ሊጠይቁዎ ይችላሉ፡፡ የግል የስጋት ትንተና ምክንያቶች ይመልከቱ፡፡ ምርጫዎን የስደት ሁኔታዎ፣ የጉዞ ታሪክዎ፣ ውሂብዎ የየዛቸው መረጃዎች አደገኛነት፣ እና ሌሎች ሁኔታዎች ምርጫዎን ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

ያልተለመዱ ጥንቃቄዎች አንዲጠራጠሩ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይገንዘቡ፡፡

  • በመሳሪያዎ ላይ ያለውን ሰነድ ምትክ ያስቀምጡ፡፡ እንዲህ ማድረጉ አንድ ወይም ከዚያ በላይ መሳሪያዎችዎ በቁጥጥር ስር ቢውሉ ይጠቅሞታል፡፡ የመስመር ላይ ምትክ ሰነድ ማስቀመጫ አገልግሎት ወይም ሌላ መሣርያ መጠቀም ይችላሉ፣ ነገር ግን ላፕቶፕዎንና ምትክ ሰነድ ማስቀመጫዎን በአንድ ላይ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ አንመክርም፡፡
  • ድንበር ላይ የሚይዙትን የውሂብ መጠን ይቀንሱ። ምንም መረጃ የሌለው ላፕቶፕ ይዘው መጓዝን ከግምት ውስጥ ያስገቡ። ነገር ግን ዝም ብሎ ሰነዶችን ከመሣሪያዎ መሰረዝ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ አያደርግም። ሰነድዎችዎን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማጥፋትዎን ያረጋግጡ። መደበኛ ተንቀሳቃሽ ስልክዎን ቤት ውስጥ በመተው ጊዜያዊ ስልክ በመግዛት ሲም ካርድዎን ማዘዋወርን ወይም መዳረሻዎ ላይ ሲሆኑ አዲስ ቁጥር መያዝን ከግምት ውስጥ ያስገቡ።
  • መሣሪያዎችዎን ይመስጥሩ። በመሣሪያዎችዎ ላይ (ላፕቶፕ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ወዘተ) የሙሉ መሳሪያ ምስጠራ   እንዲጠቀሙ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የማለፊያ ሐረግ መምረጥአንመክራለን፡፡
  • በድንበር ላይ የሚሠራ የመንግስት አካል የማለፊያ ቃልዎን ቢጠይቅ መስጠት የለብዎትም። እንደዚ ያለ መረጃን በማስገደድ መቀበል የሚችለው ዳኛ ብቻ ነው። ነገር ግን በድንበር ላይ ለሚሰራ የመንግስት አካል የማለፊያ ቃልዎን አለመስጠት ሊያስከትል የሚችለው ችግር ሊኖር ይችላል፡፡ የአሜሪካ ዜግነት የሌላችሁ - ወደ አሜሪካ እንዳትገቡ ልትከለከሉ ትችላላችሁ፣ የአሜሪካ ዜግነት ያላችሁ ደግሞ መሣርያችኹ መስራት እንዲያቆም ሊደረግ ወይም ለረጅም ሰዓታት በቁጥጥር ስር ልትውሉ ትችላላችሁ።
  • የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ጥቃቶችን ለመከላከል መሣርያዎችዎን ድንበር ከመድረስዎ በፊት ያጥፉ።
  • ከይለፍ ቃላት በባሰ ሁኔታ ደካማ ስለሆኑ በጣት አሻራዎችና የስነ-ተፈጥሮአዊ ልኬት ቁልፎች ላይ ዕምነትዎን አይጣሉ።
  • የድንበር ላይ ሠራተኞች በመሣሪያዎ ላይ ካሉ መተግበሪያዎች እና ማሰሻዎች በቀጥታ ወይም የተሸጎጡ የክላውድ ይዘቶች ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ከመለያዎ መውጣት፣ የተዘገቡ የይለፍ ቃላትን ማስወገድ ወይም ወይም ለአደጋ የሚያጋልጡ መተግበሪያዎችን ማጥፋትን ቢያስቡበት መልካም ነው፡፡
  • በድንበር ላይ ከሚሠራ የመንግሥት አካል ጋር ሲገናኙ እነዚህን ሦስት ዋና ዋና ነገሮችን ያስታውሱ፦ በትህትና ማናገር፣ አለመዋሸት እናየመንግሥት አካላት ፍተሻ በሚካሄድበት ወቅት ጣልቃ አለመግባት። በድንበር ላይ የሚሠሩ የመንግሥት አካላት የመሣሪያዎን የአካል ሁኔታ የመመልክት መብት ሊኖራቸው ይችላል(ለምሳሌ አደንዛዥ ዕጾች በላፕቶፑ የባትሪ ክፍል አለመቀመጣቸውን ለማረጋገጥ)።

እነዚህን ጥቆማዎች አንደሚያስታውሱ እርግጠኛ አይደሉምን? የኢኤፍኤፍን በጉዞ ላይ ሳሉ እንዲታተም፣ እንዲታጠፍ እና ኪስዎ ላይ እንዲገባ ሆኖ የተዘጋጀውን የድንበር ላይ ፍተሻ የኪስ መርጃ ጽሁፍ ይመልከቱ፡፡