Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የቶር አጠቃቀም ለማክኦኤስ

Last Reviewed: March 29, 2019

This page was translated from English. The English version may be more up-to-date.

ይህ መመሪያ የቶር ማሰሻን በማክኦኤስ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ያሳያል፡፡

ቅድመ ኹኔታዎች፦  የኢንተርኔት ግንኙነት፣ የመጨረሻው ማክኦኤስ ስሪት የተጫነበት ኮምፒውተር

በዚህ መመሪያ ላይ የተጠቀምናቸው ስሪቶች: ማክኦኤስ 10.14.4፣ቶር ማሰሻ: 8.0.8

ፈቃድ፦ ነጻ ሶፍትዌር፤ የተለያዩ ነጻ ፈቃድ ያላቸው ሶፍትዌሮች

ተጨማሪ ንባቦች:

ደረጃ: ከጀማሪ እስከ መካከለኛ

የሚወስደው ጊዜ: 15-30 ደቂቃ

ቶር ምንድን ነው? anchor link

ቶር መስመር ላይ ማን እንደኾኑ እና የት ሆነው ግንኙነት እንደሚያደርጉ፣ በመሸፈን ድብቅነትን እና ግላዊነትን የሚያስጠብቅ በበጎ ፈቃደኞች የሚሰጥ አገልግሎት ነው። ይህ አገልግሎት ከራሱ ከቶር አውታረ መረብ ጭምር ይከላከላል፤ ከሌሎች ቶር ተጠቃሚዎች የተሸሸጉ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡

መካነ ድሮችን በሚዳስሱበት አንዳንድ ጊዜ ድብቅነትን እና ግለኝነትን ለሚፈልጉ ሰዎች የቶር ማሰሻ ፈጣን እና ቀላል በሆነ መንገድ የቶር አውታረመረብን ያቀርባል፡፡

የቶር ማሰሻ የሚሰራው እንደማንኛውም ድር ማሰሻ ነው፡፡ ድር ማሰሻዎች መካነ ድሮችን ለማየት የምትጠቀሙባቸው ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደ ክሮም፣ ፋየርፎክስ፣ እና ሳፋሪ ሲሆን ከእነርሱ የሚለየው ቶር ማሰሻ የእርስዎን ግንኙነቶች የሚልከው በቶር ስለሆነ ነው፡፡ ይህም መስመር ላይ ምን እየሠሩ እንደኾነ ማወቅን እና እየተጠቀሙት ያለውን ድረ ገጽ ከየት ኾነው እንደከፈቱት በማወቅ እርስዎን ለሚቆጣጠሩ ሰዎች አዳጋች ያደርግባቸዋል።

ድብቅ የሚሆነው በቶር ማሰሻ ውስጥ ገብተው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብቻ እንደሆነ በህሊናዎ ያኑሩ። የቶር ብራውዘር በኮምፒውተርዎ ላይ ተጫነ ማለት በተመሳሳይ ኮምፒውተር ሌላ ሶፍትዌሮችን (ለምሳሌ መደበኛ የድር መዳሰሻዎን) በመጠቀም የሚሠሯቸውን ስራዎችን ድብቅ አያደርግም።

የቶር ማሰሻን ማግኘት anchor link

እንደ ፋየርፎክስ ወይም ሳፋሪ ያሉ የድር ማሰሻዎች መካከል ይክፈቱና ወደ:

https://www.torproject.org/download/ ይሂዱ፡፡

ቶር ማሰሻን ለማግኘት ድር ማሰሻ እየተጠቀሙ ከሆነ ዩአርኤሉን በትክክል መጻፍዎን ያረጋግጡ፡፡

ምንም አይነት ሌላ ምንጭ አይጠቀሙ አማራጭ ደኅንነት ፍቃዶችን HTTPS (SSL/TLS) እንዲቀበሉ ከተጠየቁ አይቀጥሉ፡፡

የ Apple አዶን ይምረጡ

ሳፋሪ የሚጠቀሙ ከሆነ የቶር ማሰሻን ማውረድ ይጀምራል፡፡ በፋይርፎክስ ፋይሉን መክፈት ወይስ ማስቀመጥ እንደሚፈልጉ ይጠየቃሉ፡፡ በማንኛውም ማሰሻ ከመቀጠልዎ በፊት ፋይሉን ማስቀመጥ እጅግ የተሻለ ነው፡፡ “Save” የሚለውን ይጫኑ፡፡

አሁን የምንጠቀመው ምሳሌ የሚያሳየው መመሪያ በሚጻፍበት ጊዜ የነበረው የቶር ማሰሻው ስሪት 8.0.8 ነው፡፡ ይህንን በሚያነቡበት ወቅት የበለጠ የተሻሻለ ቶር ማሰሻ ሊኖር ስለሚችል እባክዎን አሁን በስራ ላይ ያለውን እና የቶር ፕሮጀክት የሚያቀርበውን ስሪት ይጠቀሙ፡፡

ቶር ማሰሻን መጫን anchor link

ማውረዱ ከተጠናቀቀ በኋላ ፋይሉ ከወረደበት ቦታ ያለው ማህደር መክፈት ይችላሉ፡፡ በነባሪ የሚወርድበት ሥፍራ ዳውንሎድስ ማህደር ነው። “TorBrowser-8.0.8-osx64_en-US.dmg” የሚለው ፋይል ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ።

ማክኦኤስ ፋይሉ እንዳልተቀሰጠ ያረጋግጣል፡፡ ወደ Settings > Security & Privacy በመሄድ ሦስተኛ አካል የመጣን መተግበሪያ ለማውረድ ፍቃድ ይሰጣሉ፡፡

በመቀጠል አዲስ መስኮት ይከፈትና ወደ መተግበሪያ ማህደር በመጎተት ቶር ማሰሻን እንዲጭኑ ይጠይቅዎታል፡፡ እንዲዚያም ያደርጋሉ፡፡

 

አሁን ቶር ማሰሻ በመታግቢያ ማህደርዎ ውስጥ ተጭኗል፡፡

ቶር ማሰሻን መጠቀም anchor link

ቶር ማሰሻን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመክፈት የመተግበሪያ ማህደር ውስጥ ወይም ላውንችፓድ ውስጥ ይፈጉት፡፡

የቶር ማሰሻን ምልክት ከተጫኑ በኋላ ስለ ሶፍትዌሩ ምንጭ የሚያስጠነቅቅ መልዕክት የያዘ መስኮት ይከፈታል። ሁልጊዜም እንዲህ ዓይነቱን ማስጠንቀቂያ ከቁም ነገር መውሰድ እና መጫን የፈለጉትን ሶፍትዌር እውነተኛ ቅጂውን ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት በመጠቀም ከኦፊሴላዊ መካነ ድሩ ላይ እንዳገኙት ማረጋገጥ ይገባዎታል። የሚፈልጉት ምን እንደኾነ፣ ሶፍትዌሩን የት እንደሚያገኙት ስለሚያውቁ እና ያወረዱት ደህንነቱ ከተመሰከረለት የቶር ፕሮጀክትስ HTTPS መካነ ድር ላይ እስከኾነ ድረስ ይቀጥሉ እና " Open" የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

ቶር ማሰሻን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጀምር አስፈላጊ ነው ብለው ካመኑ አንዳንድ ቅንብሮች ማድረግ የሚያስችል መስኮት ያገኛሉ፡፡ እንደገና ተመለሰው አንዳንድ ቅንብሮችን ማስተካከል ይችላሉ፡፡ አሁን ግን “Connect” የሚለውን በመጫን ከቶር አውታረመረብ ጋር ለመገናኘት ይሞክሩ፡፡

ግራጫ አሞሌ ያለበት ቶር ማሰሻ ከቶር አውታረመረብ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ አዲስ መስኮት ይከፈታል፡፡

የቶር ማሰሻ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጀምር ከተለመደው ትንሽ ሊዘገይ ይችላል። ነገር ግን ትዕግስተኛ ይሁኑ። ከአንድ ወይም ሁለት ደቂቃ በኋላ ቶር ማሰሻ ይከፍት እና እንኳን ደስ አለዎት ይልዎታል፡፡

በእንኳን ደህና መጡ ሠሌዳ አቀባበል ይደረግልዎታል፡፡

ቶር እንዴት እንደሚሰራ የሚያሳይ መልመጃ ለመግኘት በግራ በኩል ከላይ የምትገኘውን ሉል ቅርጽ ይጫኑ፡፡

መልመጃው ቶር ሰርኪዩት እንዴት እንደሚሰራ እና በመስመር ላይ የሐሰሳዎን ግለኝነት እንዴት እንደሚፈቅድ ይገልጻል፡፡

አንዳንድ መደበኛ የድር ማሰሻ አገልግሎቶች በመሃከል ያለ ሦስተኛ ሰው ጥቃት ተጋላጭ ያደርጋሉ። ቀድሞ ሳንካ የነበራቸው ሌሎች አገልግሎቶች ደግሞ የተጠቃሚዎችን ማንነት ይገልጣሉ፡፡ የደኀንነት ተንሸራታቹን ወደ ከፍተኛ ቅንብር ማብራት እነዚህ አገልግሎቶች እንዳይሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ በከፍተኛ መጠን ባለው ገንዘብ ከሚደጎሙ አጥቂዎች፣ የኢንተርኔት ግንኙነትዎን ሰብረው ከሚገቡ ወይም በእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ ያሉ ያልታወቁ አዳዲስ ሳንካዎች ከሚጠቀሙ ጥቃት ይከላከልዎታል፡፡ አለመታደል ሆኑ እነዚህን አገልግሎትች ማጥፋት አንዳንድ መካነ ድሮችን እንዳይሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ነባሪው ዝቅተኛ ቅንበር ለዕለት ተዕለት ግለኝነት ጥበቃ ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ውስብስብ ጥቃቶችን ከፈሩ ወይም አንዳንድ መካነ ድሮች በትክክል አለማሳየታቸው ግድ ካልሰጥዎት ከፍተኛ ቅንብርን ማብራት ይችላሉ፡፡

በመጨረሻም በቶር ማሰስ በአንዳንድ መንገዶች ከተለመደው የማሰስ ልማድ ይለያል፡፡ ቶርን ተጠቅመው በአግባቡ ለማሰስ እና ድብቅ ሆነው ለመቆየት እነዚህን ጥቆማዎች እንዲያነቡ እንመክራለን፡፡

አሁን በሽሽግነት ኢንተርኔትን በቶር ማሰሻ ለመጠቀም ዝግጁ ነዎት፡፡