Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ምናባዊ የግል አውታረ መረብ

ምናባዊ የግል አውታረ መረብ ወይም VPN ኮምፒውተርዎን ድህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በአንድ ድርጅት ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የማገናኛ መንገድ ነው። VPNን ሲጠቀሙ ሁሉም በኮምፒውተርዎ ላይ የሚያደጉት የኢንተርኔት ግንኙነትዎ በአንድ ጥቅል ይመሰጠር እና ለሌላኛው ድርጅት ይተላለፋል። በዚህ ድርጅት ምስጠራው እና ጥቅሉ ከተፈታ በኋላ ወደ ተቀባዩ ይተላለፋል። ለእዚህ ድርጅት አውታረ መረብ ወይም በኢንተርኔት ላይ ለሚገኝ ለማንኛውም ኮምፒውተር ከእርስዎ ኮምፒውተር የመጣው ጥያቄ ከእርስዎ ሥፍራ ሳይኾን ከድርጅቱ እንደመጣ መስሎ ይታያል።

በተቋማት ውስጥ VPN ደህንነቱ የተጠበቀ የውስጥ ሀብት አገልግሎትን (ለምሳሌ እንደ የፋይል አገልጋዮች እና ፕሪንተሮች) ለማቅረብ ይውላል። በተጨማሪም በአካባቢ የሚደረግ የኢንተርኔት እገዳን ለማለፍ፣ ወይም በአካባቢ የሚደረግ ስለላን ለማሸነፍ በግለሰቦች ጥቅም ላይ ይውላል።