ደህንነታቸው የተጠበቀ ሶኬቶች ድርብርብ (SSL)
በኮምፒተርዎ እና አንዳንድ ከሚጎበኟቸው መካነ ድሮች እና የበይነ መረብ አገልግሎቶች ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተመሰጠረ ግንንኙነትን ለመጠበቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከአንድ መካነ ድር ጋር ሲገናኙ የመካነ ድሩ አድራሻ ከ HTTP ይልቅ በ HTTPS ይጀምራል፡፡ እንደ ኤ.አ.አ በ1999 ስሙ በይፋ ወደ ትራንስፖርት ሽፋን ደኅንነት (TLS) ተቀይሯል፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች አሁንም የድሮውን ስም ይጠቀማሉ፡፡