Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

PGP ወይም እጅግ መልካም የኾነ ግላዊነት

PGP ወይም እጅግ መልካም የኾነ ግላዊነት በተግባር ከዋሉት የመጀመሪያዎቹ የአደባባይ ቁልፍ ስነመሰውር ትግበራዎች አንዱ ነው። የPGP ፈጣሪ የኾነው ፊል ዚመርማን በ1991 ፕሮግራሙን ሲጽፈው አራማጆችን እና ሌሎች ሰዎችን ግንኙነቶቻቸውን ለማመስጠር እንዲረዳቸው በማሰብ ነው። ፕሮግራሙ ወደ ሌሎች ሀገራት ሲሰራጭ ፊል ዚመርማን በአሜሪካ መንግሥት ተመርምሯል። በወቅቱ ጠንካራ የአደባባይ ቁልፍ ምስጠራን ጨምሮ ሌሎች መሣሪያዎችን ወደ ውጪ መላክ የአሜሪካን ሕግ የሚተላለፍ ድርጊት ነበር።

PGP እንደ የንግድ ሶፍትዌር ምርትነት በገበያ ላይ አለ። በነጻ በተግባር ላይ ለማዋል ከPGP ጋር ተመሳሳይ መርሆችን የሚጠቀመውን GnuPG (ወይም GPG) የተባለው ሶፍትዌርን ማግኘት ይቻላል። ሁለቱም ተመሳሳይ እና ተተካኪ ስነ ዘዴን ስለሚጠቀሙ ሰዎች GnuPGን እየተጠቀሙ ስያሜውን ግን የ“PGP ቁልፍ” ወይም የ“PGP መልእክት” መላክ ብለው ሲጠቅሱት ይስተዋላሉ።