ክፍት ምንጭ ሶፍትዌር
ክፍት ምንጨ ኮድ ሶፍትዌር ወይም ነጻ ሶፍትዌር ተጠቃሚዎች ኮዱን ሊያሻሽሉት እና እንደ አዲስ ደግመው ሊሰሩት በሚችል መንገድ በነጻ የሚሰራጭ ሶፍትዌር ነው። እንደ "ነጻ ሶፍትዌር" የሚታወቅ ቢኾንም ያለ ምንም ዋጋ በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው ማለት ላይኾን ይችላል። የFLOSS ፕሮግራመሮች ልገሳን፣ ወይም ለአገልግሎት ድጋፍ ወይም ለቅጂ ክፍያን ሊጠይቁ ይችላሉ። ሊኑክስ እንደ ፋየርፎክስ እና ቶር ሁሉ ነጻ እና ክፍት ምንጨ ኮድ የኾነ ፕርግራም ምሳሌ ነው።