Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ዲጂታል ፊርማ

የመረጃ ምንጩ ትክክል መሆኑን እና ከተጻፈበት ጊዜ ጀምሮ እንዳልተቀየረ ለማረጋገጥ ሂሳባዊ የቴክኒክ ዘዴን የመጠቀም ስልት ነው፡፡ የዲጂታል ፊርማዎች ሶፍትዌሮችን ከኢንተርኔት አውርደን ስንጭን እየጫንን ያለነው ሶፍትዌር ከትክክለኛው ስሪት ህትመት ጋር እኩል መሆኑን እና ማንም እንዳላዛባው እርግጠኛ ለመሆን ያገለግሉናል፡፡ እንዲሁም ለተመሰጠሩ ኢሜሎች እንዳልተቀየሩ ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ መረጃ በዲጂታል ፊርማ የማይጠበቅ ከሆነ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ወይም ሌላ የመገናኛ አውታር ሰው የተጻፈውን ወይም የታተመውን ይዘት ሊቀይር ይችላል፡፡ ይህ እንደተከሰተ ለማወቅ የሚያስችል ቴክኒካዊ ዘዴ አይኖርም፡፡