Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ዌር ለቨሊንግ ወይም ንትበትን አመጣጣኝ

የፍላሽ ዲስክ፣ የሶሊድ ስቴት አንጻፊዎች (SSD) እና ሌሎች የዲጂታል ማጠራቀሚያዎች በተደጋጋሚ ቢጻፍባቸው ሊነትቡ እና ሊያልቁ ይችላሉ። ንትበትን አመጣጣኝ የሚባለው ንትብትን ለመከላከል ውሂብን በተመጣጣኝ መልኩ በሁሉም ሥፍራ ላይ እንዲሰራጭ የሚያደርግ ዘዴ ነው። ዋናው ጥቅሙ የመሣሪያዎች የአገልግሎት ዘመን እንዲራዘም ማድረግ ነው። ለድህንነታቸው የሚጠነቀቁ ሰዎች የንትበት አመጣጣኝ መሣሪያ ውሂባቸውን ለዘላለሙ ለማጥፊያነት ከሚጠቀሙበት መሣሪያ አሰራር ጋር ጣልቃ በመግባት እንዳይረብሽ ያሳስባቸዋል። በፍላሽ ዲስክ ወይም በሶሊድ ስቴት አንጻፊዎች (SSD) ላይ ያሉ ሰነዶችን ደህንነቱ የተረጋገጠ የፋይል ማጥፋት ሂደትን ከማመን ይልቅ የሙሉ ዲስክ ምስጠራን መጠቀም የተሻለ ጥበቃ ሊያደርግ ይችላል። ምስጠራ ከትክክለኛው የማለፊያ ሐረግ ውጪ በአንጻፊው ላይ ማንኛውንም ፋይል ለማገገም (መልሶ ለማምጣት) የሚከወነውን ጥረት አዳጋች በማድረግ ደህንነቱ የተረጋገጠ ስረዛን በሚያደርጉበት ወቅት የሚያጋጥሞትን ችግር ይቀርፋል።