Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የንግድ ቪፒኤን

የንግድ ምናባዊ የግል አውታረ መረብ የኢንተርኔት ግንኙነትዎን ደህንነቱ በተጠበቀ የግል አውታረ መረቡ የሚሰጥ የግል አገልግሎት አቅራቢ ነው፡፡ ጠቀሜታው የሚልኩትም ኾነ የሚቀበሉት ሁሉም ውሂብ ከአካባቢው ኔትወርክ የተደበቀ እንዲኾን ማድረግ ነው። በመኾኑም በአቅራቢያዎ ካሉ ወንጀለኖች፣ የማይታመኑ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ከማንኛውም የእርስዎን አከባቢ አውታረ መረብ ከሚሰልል አካል የሚጠብቅ የተሻለ አገልግሎት ያገኛሉ። የቪፒኤን አገልግሎቱ የሚከወነው ያለው በውጪ አገር ሊኾን ይችላል። ይህም ግንኙነትዎን ከመንግሥት ለመጠበቅ እና በሀገር ውስጥ የሚደረግ እገዳን ለማለፍ ይጠቅማል። የጎንዮሽ ጉዳቱ አብዛኞቹ የኢንተርኔት ግንኙነቶች በንግድ የቪፒኤን ሰጪው በኩል መታየት መቻላቸው ነው። ይህ ማለት የንግድ ቪፒኤን አቅራቢው (እና አገልግሎት ሰጪው የሚገኝበት ሀገር) የእርስዎን የኢንተርኔት ግንኙነት እንደማይሰልል ዕምነት ሊኖርዎ ይገባል።