Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የትዕዛዝ መስመር መሣሪያ

"የትዕዛዝ መስመር" ትንንሽ የተያያዙ እና ራሳቸውን የቻሉት ትዕዛዛትን ለኮምፒውተር ለኮምፕዩተር የሚሰጥበት መንገድ ነው። የትዕዛዝ መስመር መሣሪያን ለመጠቀም ተጠቃሚው የተለያዩ ትዕዛዛትን ተርሚናል ኢሙሌተር በሚባል መስኮት ላይ ጽፎ የኢንተር ወይም የሪተርን ቁልፍን ሲጫን በዛው መስኮት ላይ ለትዕዛዙ የጽሑፍ ምላሽ ያገኛል። አሁን ድረስ የዊንዶስ፣ የሊኒክስ እና የአፕል ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ይህንን የትእዛዝ መስመር ማስኬጃ ሶፍትዌር መጫን ይፈቅዳሉ። በተጨማሪም አንድ አንድ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ትክክለኛ መተግበሪያ ካገኙ የትዕዛዝ መስመርን ማስኬድ ይችላሉ። የትዕዛዝ መስመር ከኮምፒውተርዎት ስርዓተ ክውና ጋር አብረው ተጭነው የሚመጡ ሶፍትዌሮችን ለማሠራት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። አንዳንድ የሚወርዱ በተለይም ለቴክኒካዊ ነገሮች የሚጠቅሙ ፕሮግራሞች በልምድ በምንጠቀምባቸው አዶዎች እና ቁልፎች ምትክ የትዕዛዝ መስመርን ይጠቀማሉ። ተገቢውን ውጤት ለማግኘት ትክክለኛ የፊደሎችን እና የአሃዞችን ቅደም ተከተል በትክክል ማስገባት ግን ያስፈልጋል። አብዛኛውን ጊዜ የሚፈልጉትን ውጤት ካላገኙ ማድረግ የሚጠበቅብዎት ምን እንደኾነ ግልጽ አይደለም።