Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ባለ ሁለት ማትሪያ ማመሳከሪያ

"የኾነ የሚያዉቁት እና ያለዎት ጉዳይ።" የተጠቃሚ ስምን እና የማለፊያ ቃልን ብቻ የሚጠይቁ የመግቢያ ስርዓቶች ክፍተት አላቸው። አንድ ግለሰብ እነዚህን ቅንጥብ መረጃዎች ቢያገኝ (ወይም መገመት ቢችል) መረጃዎች አደጋ ላይ ይወድቃሉ። ባለ ሁለት ማትሪያ ማመሳከሪያን የሚሰጡ አገልግሎቶች ትክክለኛ ማንነትዎን የሚያረጋግጡበት ተጨማሪ የተለየ ማስረጃ እንዲሰጡ ይጠይቅዎታል። ሁለተኛው ማትሪያ አንድ የሚስጥራዊ ኮድ፣ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ ባለ ፕሮግራም የመነጨ ቁጥር፣ ወይም እርስዎ የያዙት እና ማን እንደኾኑ የእርስዎን ማንነት ለማረገገጥ የሚጠቀሙበት መሣሪያ ሊኾን ይችላል። እንደ ባንክ ያሉ ኩባንያዎች እና እንደ ጎግል፣ ፔይፓል እና ትዊተር ያሉ ዋና ዋና የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎች ባለ ሁለት ማትሪያ ማመሳከሪያ አገልግሎትን ይሰጣሉ።