Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ውግድ መላሽ ሶፍትዌር

አብዛኞቹ መሣሪያዎች ውሂቦትን እንዲያስወግዱ ይፈቅዳሉ። ለምሳሌ አንድን ሰነድ ጎትተው የውግድ ቅርጫት ውስጥ መክተት ወይም በፎቶ አልበም ውስጥ ዴሊት የሚለውን መጫን ይችላሉ። ነገር ግን ፋይልን ካለበት ሥፍራ ማስወገድ የፋይሉ ዋና ቅጂ ለዘላለሙ መሰረዝ ወይም ማጥፋት ማለት አይደለም። ውግድ መላሽ ፕሮግራሞች በመሣሪያው ባለቤት ወይም መሣሪያውን የመጠቀም አቅም ባላቸው ሌሎች ግለሰቦች አንዳንድ የተወገዱ ውሂቦችን ለማገገም የሚጠቀሟቸው መተግበሪያዎች ናቸው። ውግድ መላሽ ፕሮግራሞች ሳያውቁ በስህተት የራሳቸውን ውሂብ ለሚያስወግዱ ወይም ውሂባቸው ኾን ተብሎ ለተወገደባቸው (ለምሳሌ ከካሜራው ላይ ፎቶዎቹን እንዲያስወግድ የተገደደ ፎቶ አንሺ) ጠቃሚ ናቸው። ነገር ግን እነኚሁ ፕሮግራሞች ሚስጥራዊ ውሂቦችን ለዘላለሙ ማጥፋት ለሚፈልጉ ግለሰቦች ስጋት ናቸው። ውሂብን ስለመደምሰስ እንዲኹም ውግድ መላሽ ፕሮግራሞች በዘመናዊ መሣሪያዎች ላይ እንዴት እንሚሰሩ ለበለጠ መረጃ ውሂብዎን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማጥፋት የሚለውን ይመልከቱ።