Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

ደንብ (ፕሮቶኮል)

የግንኙነት ፕሮቶኮል በፕሮግራሞች ወይም በኮምፒውተሮች መካከል ውሂብን የማስተላለፊያ ዘዴ ነው። ተመሳሳይ ደንብ (ፕሮቶኮል) የሚጠቀሙ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች እርስ በእርሳቸው መግባባት ይችላሉ። የድር መዳሰሻዎች እና የድር አገልጋዮች በተመሳሳይ ደንብ ይግባባሉ። እርሱም "http" ይባላል። አንዳንድ ደንቦች ይዘታቸው እንዳይታይ ለመከላከል ምስጠራን ይጠቀማሉ። የhttp ደንብ ደህንነቱ የተጠበቀው ሥሪት "https" በመባል ይታወቃል። ሌላኛው በበርካታ ፕሮግራሞች ጥቅም ላይ የሚውለው የምስጠራ ደንብ ምሳሌ OTR (Off-the-Record) ነው። ይህ ለፈጣን መልዕክት የምንጠቀመው ደንብ ነው።