Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የተጋላጭነት አዝማሚያ ትንተና

በኮምፒውተር ደህንነት ቋንቋ ለአደጋ የተጋላጭነት አዝማሚያ ትንተና ስጋቶች የመከሰት ዕዳላቸው ምን ያህል እንደኾነ ማስላት ሲኾን ለመከላከልም ምን ያህል ጥረት እንደሚያስፈልግ መረጃን ይሰጣሉ። በውሂብዎ ላይ ያለዎትን ቁጥጥር ወይም የመጠቀም ችሎታ ሊያጡ የሚችሉባቸው ብዙ የተለያዩ መንገዶች ቢኖሩም አንዱ ከሌላኛው የመከሰት ዕድሉ የተለያየ ነው። ተጋላጭነትን መገምገም ማለት የትኞቹን ስጋቶች የምር መውሰድ እንዳለብዎት እና ጊዜ ወስዶ ለማሰብ የትኖቹ ስጋቶች ብዙም ጉዳት የማያደርሱ (ወይም ለመከላከል በጣም አዳጋች እንደኾኑ) ወይም የመከሰት ዕድላቸው አናሳ እንደኾነ መወሰን ማለት ነው። የስጋት ሞዴልን ይመልከቱ።