ልዕለ መረጃ
ልዕለ መረጃ (ወይም "ስለ ውሂብ ያለ ውሂብ") ከመረጃው ባሻገር ያለ ስለመረጃው የሚናገርር ቅንብር መረጃ ነው። የመልዕክቱ ይዘት ልዕለ መረጃ አይደለም። ነገር ግን መልዕክቱን ማን ላከው፣ መቼ ተላከ፣ ከየት ተላከ እና ለማን ተላከ የሚሉት የልዕለ መረጃ ምሳሌዎች ናቸው። የሕግ ስርዓቶች ከልዕለ መረጃዎች ይልቅ የመረጃውን ይዘት ይከላከላሉ። ለምሳሌ በአሜሪካን ሀገር የሕግ አስፈጻሚ አካላት የግለሰቦችን የስልክ ውይይት ለማዳመጥ የፍርድ ቤት ማዘዣ ማግኘት አለባቸው ነገር ግን ስልክ የደወሉላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝርን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ የልዕለ መረጃ በርካታ ነገሮችን ሊገልጽ ስለሚችል እንደ መረጃው ሁሉ በጥንቃቄ መጠበቅ አለበት።