ሙሉ ዲስክ ምስጠራ
በኮምፒውተርዎ ላይ ያለ ውሂብን ደህንነት የመጠበቅ ዕቅድ ካለዎት ጥቂት ቁልፍ ፋይሎችን መርጠው ማመስጠር ወይም በኮምፒውተርዎ የሚገኙትን ሁሉንም ፋይሎች ማመስጠር ይችላሉ። “የሙሉ ዲስክ ምስጠራ” በኮምፒውተር ላይ የሚገኝ ሁሉንም ነገር በምናመስጥርበት ወቅት የምንጠቀመው ቃል ነው። አብዛኛውን ጊዜ ሙሉ ዲስክ ምስጠራን መጠቀም ጥቂት የተመሰጠሩ ፋይሎችን ከማስተዳደር ይልቅ ደህንነቱ የተጠበቀ (እና ብዙውን ጊዜ ቀላል) ነው። ነጠላ ፋይሎችን ለማመስጠር ቢሞክሩ ኮምፒውተርዎ ያለ እርስዎ ዕውቅና ጊዜያዊ ያልተመሰጠረ የፋይሎቹን ቅጂ ሊያስቀምጥ ይችላል። በተጨማሪም አንዳንድ ሶፍትዌሮች ስለ ከምፒውተር አጠቃቀምዎ ያልተመሰጠሩ መረጃዎችን ሊያስቀምጡ ይችላሉ። የአፕል OS X፣ ሊኒክስ እና የዊንዶውስ ከፍ ያሉ ሥሪቶች አብሮ ገነብ የኾነ የሙሉ ዲስክ ምስጠራ አገልግሎት ቢኖራቸውም አብዛኛውን ጊዜ ግን በነባሪ የሚሠሩ አይደሉም።