ከመስመር ውጪ ማራጋገጫ
"ከመስመር ውጪ" ማለት እየተጠቀሙት ካለው የመገናኛ መንገድ ውጪ የኾነ የመገናኛ መንገድ ነው። ደህንነቱ ያልተጠበቀ ስርዓትን ተጠቅመው እየተነጋገሩት ያለውን ሰው ማንነት ለማረጋገጥ አብዛኛውን ጊዜ አነስተኛ ተመሳሳይ የጥቃት ተጋላጭነት ባለው ሌላ የመገናኛ መንገድ አማካኝነት መገናኘትን ይጠይቃል። ለምሳሌ የአንድን ሰው ትክክለኛ የአደባባይ ቁልፍ እንደሚጠቀሙ ለማረጋገጥ ቁልፉን ተጠቅመው ምስጢራዊ መልዕክትን ከመላክዎት በፊት በአካል ተገናኝተው ቁልፉን ማረጋገጥ ይችላሉ።