Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የIP አድራሻ

አንድ መኖሪያ ቤት ወይም ተቋም ድብዳቤን ለመቀበል የፓስታ አድራሻ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት ያለው መሣሪያ እንዲሁ ወሂብን ለመቀበል የራሱ አድራሻ ያስፈልገዋል ። ይህ አድራሻው የIP (Internet Protocol) አድራሻ ይባላል። ከአንድ ድረገጽ ወይም ከመስመር ላይ ካለ አገልጋይ ጋር ሲገናኙ የራስዎን የIP አድራሻ ይገልጻሉ። ይህ እውነተኛ ማንነትዎን ይገልጻሉ ማለት ላይኾን ይችላል ( የIP አድራሻን ተጠቅሞ ግንኙነት እየተደረገበት ያለውን አድራሻ ወይም ኮምፒውተሩ የማን እንደኾነ ማመልከት አዳጋች ነው)። የIP አድራሻ ስለ እርስዎ አንዳንድ መረጃዎችን ለምሳሌ ግምታዊ የኾነን የመኖሪያ ክልልዎን ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎን ስም አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል። እንደ ቶር ያሉ አገልግሎቶች የIP አድራሻዎን በመደበቅ የመስመር ላይ ድብቅነትን ያጎናጽፍዎታል።