Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

HTTPS

በዚህ “http://www.example.com/” መልክ የተጻፈ የድር አድራሻን አይተው ከኾነ “http” የሚለውን ቅንጥብ ውሂብ ያስተውላሉ። HTTP (hypertext transfer protocol) ማለት በኮምፒውተርዎ ላይ ያለው የድር መዳሰሻ በርቀት ካለው የድር አገልጋይ ጋር የሚነጋገርበት ቋንቋ ነው። እንደ አለመታደል ኾኖ መደበኛው http በኢንተርኔት ላይ መልዕክትን የሚያስተላልፈው ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ነው። HTTPS (S የምትለዋ በእንግሊዘኛው “ሴኪዩር” የሚለውን ይወክላል ይህም ደህንነቱ የተረጋገጠ ለማለት ነው) ደግሞ ለድረ ገጾች የሚልኩትን ውሂብ እና ከእነርሱ የሚቀበሉትን መረጃ ከሰላዮች ለመከላከል ምስጠራን ይጠቀማል።