Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የአደባባይ ቁልፍ አገልጋይ

እንደ PGP ያለ የአደባባይ ቁልፍ ስነመሰውርን ለሚጠቀም ግለሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ መልዕክትን ለመላክ ቢያቅዱ፤ መልዕክቱን ለማመስጠር መጠቀም ያለብዎትን ቁልፍ ማወቅ ይኖርብዎታል። የአደባባይ ቁልፍ አገልጋይ ለእነዚህ ቁልፎች እንደ ስልክ ቁጥር መዝገብ በመኾን ያገለግላል። ይህም ሶፍትዌሩ የኢሜል አድራሻን፣ ስምን፣ ወይም የጣት አሻራ ቁልፍን በመጠቀም ሙሉ ቁልፉን ፈልጎ ለማውረድ ይፈቅዳል። ብዙ የPGP የአደባባይ ቁልፍ አገልጋዮች ቢኖሩም አብዛኛውን ጊዜ የቁልፍ ስብስባቸውን የሚጋሩት ግን እርስ በእርሳቸው ነው። የቁልፍ አገልጋዮች የሚያትሟቸው ቁልፎች እውነተኛ ወይም ሀሰተኛ እንደኾኑ አያረጋግጡም ። የአደባባይ ቁልፍ አገልጋይ ላይ ማንም ሰው በሌላ ሰው ስም ቁልፍን ሊጭን ይችላል። ይህ ማለት በቁልፍ አገልጋይ ላይ ከአንድ ሰው ስም ወይም ኢሜል ጋር የተያያዘ ቁልፍ የዛ ሰው እውነተኛ ቁልፍ ላይኾን ይችላል ማለት ነው። የቁልፉን እውነተኛነት ለማጣራት ፊርማውን ማጣራት ወይም በሚታመን መንገድ የጣት አሻራውን ከዋናው ተጠቃሚ ጋር ማረጋገጥ ይኖርብዎታል።

PGP የሌሎች ሰዎችን ቁልፍ እንዲፈርሙ ይፈቅዳል። ይህም የእርስዎን ቁልፍ በመጠቀም አንድ ቁልፍ የኾነን ግለሰብን ለማግኘት ትክክለኛው ቁልፍ እንደኾነ የሚያረጋግጡበት መንገድ ነው። ይህም እውነተኛውን ከሀሰተኛ ቁልፍ ለመለየት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ተጠቃሚዎች የሚያውቋቸውን እና ግንኙነት የሚያደርጓቸውን ግለስቦች ትክክለኛ ቁልፍ ከፈረሙ ሌሎች ሰዎች በእነኚህ ፊርማዎች አማካኝነት ቁልፎቹ እውነተኛ እንደኾኑ ማረጋገጥ ይችላሉ። ከቁልፍ አገልጋይ ቁልፍ ሲያወርዱ የቁልፉን እውነተኝነት የሚያረጋገጥ የሌሎች ሰዎች ፊርማን አብረው ሊያወርዱ ይችላሉ። እነዚህን ሰዎች በእርግጥም ከአወቋቸው እና የእነርሱ እውነተኛ ቁልፍ ካለዎት አዲስ በአወረዱት ቁልፍ ተጨማሪ መተማመኛ ይኖርዎታል። ይህ የማረጋገጫ ሂደት የመተማመኛ ድር ይባላል። የእዚህ የማረጋገጫ ሂደት ጥቅሙ ያልተማከለ እና በአንድ ባለ ስልጣን ቁጥጥር ስር አለመኾኑ ነው። ስለዚህ ለአዲስ አንድ ቁልፍን ተጠቅመው ለግለሰብ መልዕክት ሲጽፉ የኾነ ኩባንያን ወይም መንግሥትን ማመን አይጠበቅብዎትም። በምትኩ የራስዎን ማኅበራዊ መረብን ማመን ይችላሉ። የመተማመኛ ድር ዋነኛ የጎንዮሽ ጉዳቱ የሌሎች ሰዎችን ቁልፍ ሲፈርሙ እውቂያዎት እነማን እንደኾኑ ለመላው ዓለም ማሳበቁ ነው። ይህም በግል የሚያገኟቸው ሰዎችን ዝርዝር እና ማንነት አደባባይ ያወጣዋል። በተጨማሪም መተማመኛ ድርን በትክክል ለመጠቀም ሠፊ ጊዜ እና ትኩረት የሚፈልግ ሲኾን አንዳንድ የማኅበረሰቡ አባላት በጥቂቱ ወይም ጭራሽኑ አጠቀሙትም።