Skip to main content
Surveillance
Self-Defense

የማሰሻ ጣት አሻራ

መካነ ድር በሚጎበኙበት ጊዜ መካነ ድሩ ስለ መካነ ድር ማሰሻዎ ወይም የኮምፒዩተር ባህሪያት ሊያውቅ ይችላል፡፡ ምናልባት በመካነ ድሮች እና ኮምፒዩተሮች መጠነኛ ልዩነት ቢኖርም እርስዎ ምንም ወደ መለያ ባይገቡም እንኳን ኮምፒተርዎ ኩኪዎችን እንዲያስቀምጥ ባይፈቀዱም ወይም ከተለየ አውታረ መረብ ጋር ከበይነመረቡ ጋር ቢገናኙም እንኳን እርስዎ መሆነንዎን ለመለየት የሚያስችል መንገድ ሊኖር ይችላል፡፡ለምሳሌ እርስዎ በተለየ አንድ ቋንቋ በተሰናዳ መሣሪያ፣ በተለየ የስክሪን መጠን፣ በተወሰነ የድር ማሰሻ ስሪት የተወሰነ መካነ ድርን የሚጎበኝ ብቸኛ ሰው ሊሆኑ ይቻላሉ እንበል፡፡ ከዚያም መካነ ድሩ እርስዎ ማንነትዎን ለማሳየት ምንም ነገር ባያደርጉም እርስዎ በሚጎበኙበት ጊዜ ሁሉ እርስዎ መሆንዎን ሊገነዘቡት ይችላሉ፡፡