የቶር አጠቃቀም ለሊኒክስ
Last Reviewed: November 29, 2018
ይህ መመሪያ የቶር ማሰሻን በሊኒክስ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ያሳያል፡፡
ቅድመ ኹኔታዎች፦ የኢንተርኔት ግንኙነት፣ ምርጫዎ የሆነው ሊኒክስ የተጫነበት ኮምፒውተር
በዚህ መመሪያ ላይ የተጠቀምናቸው ስሪቶች:ኡቡንቱ 18.04.1 LTS፣ ቶር ማሰሻ: 8.0.8
ፈቃድ፦ ነጻ ሶፍትዌር፤ የተለያዩ ነጻ ፈቃድ ያላቸው ሶፍትዌሮች
ተጨማሪ ንባቦች:
- https://2019.www.torproject.org/docs/documentation.html.en
- https://tor.stackexchange.com/
- https://www.eff.org/pages/tor-and-https
- https://www.youtube.com/playlist?list=PLwyU2dZ3LJErtu3GGElIa7VyORE2B6H1H
ደረጃ: ከጀማሪ እስከ መካከለኛ
የሚወስደው ጊዜ: 15-30 ደቂቃ
ቶር ምንድን ነው? anchor link
ቶር መስመር ላይ ማን እንደኾኑ እና የት ሆነው ግንኙነት እንደሚያደርጉ፣ በመሸፈን ድብቅነትን እና ግላዊነትን የሚያስጠብቅ በበጎ ፈቃደኞች የሚሰጥ አገልግሎት ነው። ይህ አገልግሎት ከራሱ ከቶር አውታረ መረብ ጭምር ይከላከላል፤ ከሌሎች ቶር ተጠቃሚዎች የተሸሸጉ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ይችላሉ፡፡
መካነ ድሮችን በሚዳስሱበት አንዳንድ ጊዜ ድብቅነትን እና ግለኝነትን ለሚፈልጉ ሰዎች የቶር ማሰሻ ፈጣን እና ቀላል በሆነ መንገድ የቶር አውታረመረብን ያቀርባል፡፡
የቶር ማሰሻ የሚሰራው እንደማንኛውም ድር ማሰሻ ነው፡፡ ድር ማሰሻዎች መካነ ድሮችን ለማየት የምትጠቀሙባቸው ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደ ክሮም፣ ፋየርፎክስ፣ እና ሳፋሪ ሲሆን ከእነርሱ የሚለየው ቶር ማሰሻ የእርስዎን ግንኙነቶች የሚልከው በቶር ስለሆነ ነው፡፡ ይህም መስመር ላይ ምን እየሠሩ እንደኾነ ማወቅን እና እየተጠቀሙት ያለውን ድረ ገጽ ከየት ኾነው እንደከፈቱት በማወቅ እርስዎን ለሚቆጣጠሩ ሰዎች አዳጋች ያደርግባቸዋል።
ድብቅ የሚሆነው በቶር ማሰሻ ውስጥ ገብተው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብቻ እንደሆነ በህሊናዎ ያኑሩ። የቶር ብራውዘር በኮምፒውተርዎ ላይ ተጫነ ማለት በተመሳሳይ ኮምፒውተር ሌላ ሶፍትዌሮችን (ለምሳሌ መደበኛ የድር መዳሰሻዎን) በመጠቀም የሚሠሯቸውን ስራዎችን ድብቅ አያደርግም።
የቶር ማሰሻን ማግኘት anchor link
እንደ ፋየርፎክስ ወይም ክሮም ያሉ የድር ማሰሻዎች መካከል ይክፈቱና ወደ:
https://www.torproject.org/download/ ይሂዱ፡፡
ቶር ማሰሻን ለማግኘት ድር ማሰሻ እየተጠቀሙ ከሆነ ዩአርኤሉን በትክክል መጻፍዎን ያረጋግጡ፡፡
ምንም አይነት ሌላ ምንጭ አይጠቀሙ አማራጭ ደኅንነት ፍቃዶችን HTTPS (SSL/TLS) እንዲቀበሉ ከተጠየቁ አይቀጥሉ፡፡
የ Linux አዶን ይምረጡ
አንዳንድ የድር ማሰሻዎች ይህንን ሰነድ ማውረድ እንደሚፈልጉ ማረጋገጫ ይጠይቅዎታል። ፋየርፎክስ በድር መዳሰሻው ገጽ መካከለኛ ክፍል ላይ ብቅ ባይ ሳጥን ያሳያል። በማንኛውም ማሰሻ ከመቀጠልዎ በፊት ፋይሉን ማስቀመጥ ይኖርብዎታል፡፡
አሁን የምንጠቀመው ምሳሌ የሚያሳየው መመሪያ በሚጻፍበት ጊዜ የነበረው የቶር ማሰሻው ስሪት 8.0.8 ነው፡፡ ይህንን በሚያነቡበት ወቅት የበለጠ የተሻሻለ ቶር ማሰሻ ሊኖር ስለሚችል እባክዎን አሁን በስራ ላይ ያለውን እና የቶር ፕሮጀክት የሚያቀርበውን ስሪት ይጠቀሙ፡፡
ቶር ማሰሻን መጫን anchor link
ማውረዱ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ዳውንሎድስ ማህደር ይሂዱ፡፡ ሁልጊዜም መጫን የፈለጉትን ሶፍትዌር እውነተኛ ቅጂውን ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት በመጠቀም ከኦፊሴላዊ መካነ ድሩ ላይ እንዳገኙት ማረጋገጥ ይገባዎታል። የሚፈልጉት ምን እንደኾነ፣ ሶፍትዌሩን የት እንደሚያገኙት ስለሚያውቁ እና ያወረዱት ደህንነቱ ከተመሰከረለት የቶር ፕሮጀክትስ HTTPS መካነ ድር ላይ እስከኾነ ድረስ ይቀጥሉ እና “tor-browser-linux64-8.0.8_en-US.tar.xz” የሚለውን ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ።
የቶር ማሰሻ ፋይል ሁለቴ ጠቅ ካደረጉ በኋላ እስኪጭን ድረስ ይጠብቁት፡፡ ከዚያም በውስጡ ያለውን ይዘት የት ማሰቀመጥ እንደሚፈልጉ ይምረጡ፡፡
የማውጣት ሂደቱ ካለቀ በኋላ “tor-browser_en-US” የሚለውን ማህደር በመክፈት “Tor Browser Setup” የሚለውን ፋይል ይጫኑ፡፡
ቶር ማሰሻን መጠቀም anchor link
ቶር ማሰሻን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጀምር አስፈላጊ ነው ብለው ካመኑ አንዳንድ ቅንብሮች ማድረግ የሚያስችል መስኮት ያገኛሉ፡፡ እንደገና ተመለሰው አንዳንድ ቅንብሮችን ማስተካከል ይችላሉ፡፡ አሁን ግን “Connect” የሚለውን በመጫን ከቶር አውታረመረብ ጋር ለመገናኘት ይሞክሩ፡፡
ብርቱካናማ አሞሌ ያለበት ቶር ማሰሻ ከቶር አውታረመረብ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ አዲስ መስኮት ይከፈታል፡፡
የቶር ማሰሻ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጀምር ከተለመደው ትንሽ ሊዘገይ ይችላል። ነገር ግን ትዕግስተኛ ይሁኑ። ከአንድ ወይም ሁለት ደቂቃ በኋላ ቶር ማሰሻ ይከፍት እና እንኳን ደስ አለዎት ይልዎታል፡፡
በእንኳን ደህና መጡ ሠሌዳ አቀባበል ይደረግልዎታል፡፡
ቶር እንዴት እንደሚሰራ የሚያሳይ መልመጃ ለመግኘት በግራ በኩል ከላይ የምትገኘውን ሉል ቅርጽ ይጫኑ፡፡
መልመጃው ቶር ሰርኪዩት እንዴት እንደሚሰራ እና በመስመር ላይ የሐሰሳዎን ግለኝነት እንዴት እንደሚፈቅድ ይገልጻል፡፡
አንዳንድ መደበኛ የድር ማሰሻ አገልግሎቶች በመሃከል ያለ ሦስተኛ ሰው ጥቃት ተጋላጭ ያደርጋሉ። ቀድሞ ሳንካ የነበራቸው ሌሎች አገልግሎቶች ደግሞ የተጠቃሚዎችን ማንነት ይገልጣሉ፡፡ የደኀንነት ተንሸራታቹን ወደ ከፍተኛ ቅንብር ማብራት እነዚህ አገልግሎቶች እንዳይሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ በከፍተኛ መጠን ባለው ገንዘብ ከሚደጎሙ አጥቂዎች፣ የኢንተርኔት ግንኙነትዎን ሰብረው ከሚገቡ ወይም በእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ ያሉ ያልታወቁ አዳዲስ ሳንካዎች ከሚጠቀሙ ጥቃት ይከላከልዎታል፡፡ አለመታደል ሆኑ እነዚህን አገልግሎትች ማጥፋት አንዳንድ መካነ ድሮችን እንዳይሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ነባሪው ዝቅተኛ ቅንበር ለዕለት ተዕለት ግለኝነት ጥበቃ ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ውስብስብ ጥቃቶችን ከፈሩ ወይም አንዳንድ መካነ ድሮች በትክክል አለማሳየታቸው ግድ ካልሰጥዎት ከፍተኛ ቅንብርን ማብራት ይችላሉ፡፡
በመጨረሻም በቶር ማሰስ በአንዳንድ መንገዶች ከተለመደው የማሰስ ልማድ ይለያል፡፡ ቶርን ተጠቅመው በአግባቡ ለማሰስ እና ድብቅ ሆነው ለመቆየት እነዚህን ጥቆማዎች እንዲያነቡ እንመክራለን፡፡
አሁን በሽሽግነት ኢንተርኔትን በቶር ማሰሻ ለመጠቀም ዝግጁ ነዎት፡፡